የህወሓት መሪዎች ዛሬ መቀሌ ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል – ከኣስገደ ገብረስላሴ 

ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ አንጃዎች

ትግራይና ህወሓት በኣረንጓዴ ልማት ስንመለከት
ትግራይ ተቀይራለች ወይ ? ኣረንጓዴ ለማቱ በ26 ኣመት የኣገዛዝ ዘመናቸው ሃቅና ውሼት ገጽ ለገጽ ሲተያዩ!!
————————————————————
ባለፉት ሳምንታት እነ የህወሓት መሪዎች ትግራይ በኣረንጓዴ ልማት ከኣለም ኣንደኛ በመሆን ተሸልማ በማለት 98% የትግራይ የመሬት የቆዳ ስፋት የማይገኝ የውሼት ኣረንጓዴ ለማች ትግራይ ተቀይራለች እያሉ በሁሉም ዞኖች ወረዳዎች እስከ ቀበሌ ወርደው የውሼት የወርቅ ሽልማታቸው መልእክት ሲያስተላልፉ ሰንብተዋል ።
ሌላ ቀርቶ በጥምቀት ክቡር የሀይማኖት በኣልም ሽልማቱ ከጳጳሳት ቀሳውስት ቃለቡራኬ በፊት የህወሓት ሊቀመንበር ኣባይ ወልዱ እና በሁሉም የትግራይ ክልል ወረዳዎች የሚገኙ ካድሬዎች ከቀሳውስት ጳጳሳት ቃለቡራኬ በፊት በውሼት ፕሮፕጋንዳ ሲባርኩትና ሲኑጡት ሰንብተዋል ።
የትግራይ ጳጳሳትና ቀሳውስቶች ከሀይማኖት ተሉኡኳቸው ማሰረጽ ኣስቀድመው በመሬት የለለ የኣረንጓዴ ሊማት ከቃለ እግዛኣቢሄር በመቀላቀል ሲያጅቡት ሰንብተዋለ ።

ለመሆኑ እነዚህ መሪዎች ከ30 ኣመት በፊት በኣብዛኛው የትግራይ የመሬቱ የቆዳ ስፋት በኣንድ እስኬር ሜትር ከ3 እስከ 5 ብርቅዬ ለእንድስትሪ ስራ የሚውሉ እንደ እጣን ፡ ቀርቀሃ ፣ ጥድ ፣ዌራ ፣ ዋንዛ ፣ ሕሞር ፡ ደቁማ ፣ ዓዬ ፣ ወይቦ ፣፣ዘግባ ፡ ግራር ፡ ወ ዘ ተ የነበሩበት በነዚህ ለመግብነት ሰውም እንስሳ ዘገዳም ይመገቡባቸው የነበሩ በውስጣቸው ኣእላፍ የዱር እንስሳት ተጠልለውበት የሚኖሩበት። እንደ ኣንበሳ ፣ ነብር ፣ ከርከሮ ፣ጅብ ፣ዝሆን ፣ኣሳማ ፣ ኣጋዜን ፣የሜዳ ፍዬል፣ ጉሬዛ ፣ዘንጀሮ ፣ ቀይ ቀቦሮና ተራው ቀበሮ ፣ጦጣ ፣ጉሬዛ ፣ድኩላ ፣ሰሳሓ ፣ ወ ዘ ተ ከክልላቸው ሸሽተው የጠፉበት እያለ ፣ እነዚህና እጽዋቶት ጠፍተውና የባደሙና ለሙዜም እንኳን ኣንዲት እጽዋት ወይ እንስሳ ዘገዳም የማይታይባቸው ኣካባቢዎች እንዳሉ ያውቃሉን?
እነዚህ ፍጡራን ለመሆኑ ከሰቆጣ ተከዜን ተከትሎ እስከተ ሱዳን የወደሙ እጣን ፣ቅርቃሃ ፣ ከጫፍ የመረብ ወንዝ መነሻ ወንዙን ተከትሎ እስከ ሱዳን ግራና ቀኝ ተራራዎች ሸንተረር ። የሽሬ ኣውራጃ በኣድያቦ ኣራት ወረዳዎች ፣ በኣስገደ ፣በጽንብላ ፣ በዓዴት ፣በናዕደር ፣ በማይቅነጣል ፣በእንባስነይቲ በዛና ፣በተንቤን ቆላማ ወረዳዎች ፣ የኣድዋ እና የኣክሱም ወረዳዎች እነ ወርዒ ፣እገላ ፣ዓዲ ኣርባዕተ ፣ በመደባይ ኣንከረ ወ ዘ ተ ከላይ የጠቀስኳቸው እጽዋት እና ሌሎች ያልጠቀስካቸው በኣስር ሽዎች የሚቆጠሩ ትላልቅና ጥቃቅን የነበሩበት የሚያበቅሉ ኣብቃይ ኣካባቢዎች የሚኖሩና ተጠቃሚ የሆኑ ወገኖች ይሰሙናል ብለው ኣይገሙቱም? እነዚህ ኣካባቢዎች ከ26 ኣመታት በፊት በኣስር ሽዎች የሚቆጠሩ የእጣን ሰራተኛ የነበሩበት ፣ሌላስ ከኣላጣ እስከስንቃጣ ፣ኣጽበደራ ፣ተነቤን ፣ገርዓልታ የነበረው በለስ በትግራይ እርሻና ተፈጥሮ ሓፍት ቢሮ እና በመቀሌ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች ፣በትግራይ ክልል እርሻ ምርምር ያማይታወቀው ቫይረስ ኣስገብተው ከ 2 , 5 ሚሊዮን ህዝብ ከ6 ወር በላይ ለምግብነትየሚጠቀምበት ፣ ወደ መላው የኢትዮጱያ ክልሎች በመሸጥ ገንዘብ የሚያስገቡበት ፣በቡዙሚሊዮን የሚቆጠሩ እንስሳ ዘቤት እንስሳ ዘገዳም ኣመቱሙሉ ይመገቡት የነበረ የበለስ ተፈጥራዊ ተክል ዘር በግብታውነት ደንቆሮ ምርምራቸው ያወደሙት ኣሁንም ወደ ዋናዎቹ የበለስ ኣብቃይ ኣውራጃዎች በሁሉም ኣይነት የኣማጋገብ ዜቤ የሚጠቀሙበት በድሮ ኣጋሜ ኣውራጃ ኢሮብ ኤርትራ በለሱ ሊያወድም ቫይረሱ እየገሰገሰ ያለው ቫይረስ ኣስገብተው ማውደማቸው ኣልበቃም ብሎ በመሬት የለለ የኣረንጓዴ ልማት መዝሙር እየዘመሩ እዝብ ማደናገራቸው ነው ትልቁ ወንጀላቸው ። የተከበራቹ ኣንባብያን የበለስ ውድመት እንዴት እየወደመ እንዳለ በመጨረሻ በስእሉ ተመልከቱ።
እጅጉን ሚያሳዝነው የመንግስት እና የህወሃት ሚዲያዎች እነሱ በመሰረታዊ ድርጅት ያዳራጁዋቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች እንኳ የህወሓት መሪዎች ውሼት ከማስ ተጋባት እና ወደህዝብ ውሼት እየፈበረኩ ከማሰራጨት ከመበረዝ ውጭ ሌላ ኣንጠብቅም ።

ሌላ ባገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ የግል ጋዜጦች ሬድዮጣብያዎች ፣መጽሄቶች ፣አብዛኛዎቹ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ኣሁን ያለው ግራዚያኒ ስርኣት የሚያደርሰው ኣፈና ፣እስራት ፣ ግድያ የውሼት ልማት ሽልማት በሚመለከት ፣ ስራ ኣጥነት ስደት ከመዘገብ ተቆጥበዋል ። በተለይ እውቁዎቹ የኣመሪካ ድምጽ ሬዴዮ ፣የጀርመን ደችበለ ጣብያዎች በትግራይ ክልል የሚገኜው ችግር ከመግለጽ ይቆጠባሉ ። ኣለፍ ኣለፍ ብለው የሚያሰራጩት ቢኖርም እንደሚፈለገው ጠለቅ ብለው ኣገልጹትም ። በተለይ ትግርኛ ቋንቋ የሚያሰራጩት ኣብዛኛው ጊዜ የድምጽ ወያነ ሬድዮጣብያ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ናቸው ። ኣንድ ኣንድ በቴለብዥንና በሬድዮ ጣብያዎች ደግሞ ለትግራይ ህዝብ ለመነጠል ሌት ተቀን ስለትግራይ ክልል የሚያሰራጩት ደግሞ
ዘረኝነት እየቆሰቆሱ ይታያሉ።

በሌላ በኩል የዓይጋ ፎሮም የተባለው ዌቭ ሳይት የድምጽ ወያኔና የሬድዮ ፋና ፣የዋልታ ተቀጥያ እና የህወሓት መሪዎች በሚሰጡት መመሪያ የሚነዳ ቅጥረኛ ሚዲያ በትግራይ የለለ የልማት ስእል እያሳራጨ የሚኖር ውሼታም ሚድያ ኣለን ።
ከኣስገደ ገብረስላሴ
መቀሌ
21 / 01 / 2010

 

Zewude Tadesse added 2 new photos.

እንዲህ ሰብሰብ ብለው ስለሀገራችን መፃኢ እድል እየወሰኑልን ይገኛል ። ከሁሉም እሚያሳዝነው እነዚህ ጥቂቶች የ95% ህዝቡን እድል እንዲወስኑ ፍቃድ መስጠታችን ብቻ ነው ። ያው አነሰም በዛ እንዴት አድርገን እንግዛቸው እንዴትስ እንቀጥቅጣቸው ማነው የእኛን አመራር አልቀበል ያለው ኦህዴድ ነው ወይስ ብአዴን ውስጥ ነው የአመራር መክዳት እየታየ ያለው በሚሉ ጉዳዬች ላይ እንደሚወያዩ ግልፅ ነው ።የህውሓት ማዕከላዊ ኮ/ሚ የወሰነው ትግርኛ ግልባጭ ለሁሉም አጋር ድርጅቶች በእየቋንቋቸው ይገለበጥ እና እስከ መጋቢቱ ድረስ ይወያዩበታል ከዛም #የኢህአዴግ አቋም ሆኖ ሀይለማርያም ድምፅ ያሰጥበታል ።

እንዲህ ሰብሰብ ብለው ስለሀገራችን መፃኢ እድል እየወሰኑልን ይገኛል ። ከሁሉም እሚያሳዝነው እነዚህ ጥቂቶች የ95% ህዝቡን እድል እንዲወስኑ ፍቃድ መስጠታችን ብቻ ነው ። ያው አነሰም በዛ እንዴት አድርገን እንግዛቸው እንዴትስ እንቀጥቅጣቸው ማነው የእኛን አመራር አልቀበል ያለው ኦህዴድ ነው ወይስ ብአዴን ውስጥ ነው የአመራር መክዳት እየታየ ያለው በሚሉ ጉዳዬች ላይ እንደሚወያዩ ግልፅ ነው ።የህውሓት ማዕከላዊ ኮ/ሚ የወሰነው ትግርኛ ግልባጭ ለሁሉም አጋር ድርጅቶች በእየቋንቋቸው ይገለበጥ እና እስከ መጋቢቱ ድረስ ይወያዩበታል ከዛም #የኢህአዴግ አቋም ሆኖ ሀይለማርያም ድምፅ ያሰጥበታል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.