“ጠላቶቻችን ወገናችንን መግደል ሳያስፈራቸው እኛም አማራ እየሞተ መኖሩን መናገርና መታገል አይሰለቸንም!” አዴአን ከኤርትራ

በኢትዮጵያ ቀድሞ በነበሩ ስርዓቶች አንድ ማህበረሰብ ለብቻው ከሌሎች ተለይቶ ከስርዓቱ የተጠቀመውም ሆነ ለብቻው ተለይቶ የተበደለም ብሔረሰብ የለም፡፡ሁሉም የሚጠቀሙትንም ሆነ የሚጎዱትን በጋራ ነበር ሚጋሩት፡፡ባለንበት ዘመን በዛሬው በዘመነ ወያኔ ህወሃት ግን ከሌሎች ተለይቶ የሚጠቀም ብሔረሰብም ሆነ ከሌሎች ተለይቶ የሚበደል ፣እንዲጠፋ የተፈረደበት ብሔረሰብ መኖሩን በማረጋገጥ መናገር ስለማይሰለቸን አሁንም አድምቀን እንናገራለን፡፡አዎ አማራ እንዲጠፋ በስርዓቱ ቀመር የተቀመረለት ህዝብ ነው፡፡መቼም ጠላቶቻችን ወገናችንን መግደል ሳያስፈራቸው እኛም አማራ እየሞተ መኖሩን መናገርና መታገል ይሰለቻቸዋል ማለት ሞኝነት ነው፡፡አማራ የሚታገለው ያለፉት ስርዓቶችን ለመመለስ ሳይሆን እራሱን እንደ ሰብአዊ ፍጡር ለመታደግ የሚያደርገው ትንቅንቅ ነው፤ይህን ካሳካ በኋላም እንደ ህዝብ ሁሉም በእኩልነት የሚታይበት ፣የሚዳኝበትና የሚጠቀምበት ዘመኑ(ጊዜው) የሚመጥነውን ስርዓት ከሌሎች አንድነትን(ኢትዮጵያዊነትን) ግባቸው ካደረጉ እውነተኛ ሀገር ወዳዶች ጋር በመሆን በጋራ የነበረችንን ትልቅ ሀገር መልሰን መገንባት መቻል እምነታችን ነው፡፡

 

“አናብስት የራሳቸውን ታሪክን መፃፍ እስካልቻሉ ወይም እስካልጀመሩ ድረስ የአደን ታሪክ ሁሌም አዳኞችን ያወድሳል” እንደተባለ ሁሉ የአማራ ህዝብ ቅድሚያ የአንተ መኖር ነው ምትመኛትን ወይም እንድትኖር የምትፈልጋት ሀገር መገንባት የምትችለው አለበለዚያ ግን በአንተ ደካማ አደረጃጀትና ደካማ ጎን ትገነባለች የምትባል ሀገር ብትኖር ከዘለቄታዊ የመጥፊያ አቅጣጫ የሚታደግህ ምንም ማረጋገጫ የለህም፡፡ለምን ብለህ ብትጠይቅ?ባለፉት 40 እና 50 አመታት የነበሩ አደረጃጀቶች እና ፖለቲከኞች ሲማማሉብህና ሲቀጣጠሩብህ የት እንዳደረሱህ መረዳት የምትችልበት ወቅት ላይ ነህ፡፡የዘመናችንም ፖለቲካ መሃላና ቲፎዞ ለምዷልና ንቃ ወገኔ፡፡ያለፈው ለመጪው ድልድይ ነውና የተከበሩ የፕሮፌሰር አስራት ተዋድቆ መሰላልህ አድርገህ ቀጥልበት፡፡”የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ” ነውና ከፕሮፌሰር አስራት በላይ ምሁርነትና ኢትዮጵያዊነት ላሳር ነው፡፡

አማራ ወገኔ ሆይ ጠላቶችህ ሊያጠፉህ ወደ ኋላ ሳይሉ አንተም መኖር የፈቀዱልህ መስሎህ ከመታገል ወደ ኋላ አትበል፡፡ከጥቃቱ የምትተርፍ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል የፊትና የኋላ መሆን እንጅ አላመለጥክም፡፡ሀገርን በመልቀቅ ፣ከሌላ ጋር በመዋለድ በመጋባት ፣ተገዢ በመሆን ፣አማራነትን በመካድ(በመደበቅ)፣ያልተወከልክበት ህብረትን በመደገፍ ከጥቃቱ ማምለጥ አይቻልም፡፡ብቸኛው መፍትሄ አንገትህን ቀና አድርገህ በአማራነትህ ተደራጅተህ መታገል ስትችል ብቻ ነው ሰውኛ ዑደትህ የሚቀጥለውም ሆነ አንተ በነፃነት ከሌሎች ወገኖችህ ጋር የምትኖርባት ሀገር የምትኖርህ፡፡የታገለ ሁሉ አይሞትም የተተኮሰ ጥይት ሁሉ አይገልም፡፡ባለመታገልም ሞትን ማምለጥ አይቻልምና ጠንክረህ ሳትሰለች ታገል፡፡
እኛ እንላለን ጠላቶቻችን ወገናችንን መግደል ሳያስፈራቸው እኛም አማራ እየሞተ መኖሩን መናገርና መታገል አይሰለቸንም፡፡

አበቃው!!!
የህዝብ ትግል ሁሌም አሸናፊ ነው!፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.