ድምፃዊ ኃብተሚካኤል ደምሴ ባጋጠመው የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ – (ወንድሙ ኃይሉ)

ድምፃዊ ኃብተሚካኤል ደምሴ ባጋጠመው የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ - (ወንድሙ ኃይሉ) 1ድምፃዊ ኃብተሚካኤል ደምሴ ባጋጠመው የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ…
በበገናና በክራር መሣሪያ በመጫወት የሚታወቀው ድምፃዊው ኃብተሚካኤል ደምሴ ዛሬ ባጋጠመው የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ሰምተናል፡፡
ሸገር ለድምፃዊው ቤተሰቦችና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
(ወንድሙ ኃይሉ)

 

Haregeweyn Abeje Iwnetu

አሳዛኝ ዜና እረፍት
አንጋፋው የባህል ሙዚቃ ዘፋኝ #አርቲስት#ሃብተሚካኤል_ደምሴ ከዚ አለም በሞት ተለይ

ዛሬ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፤ (ወረዳ 8) መኪናውን አቁሞ ይሻገራል አርቲስት ሀብተሚካኤል ደምሴ፡፡ ድንገት፤ እየተሸገረ ሳለ አውቶብስ ገጭቶት ይወድቃል፡፡ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች እና ሁለት ፖሊሶች አፋፍሰው ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ይዘው ይሮጣሉ፡፡ … እንደገና ከጳውሎስ ወደ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ጀርባ የሚገኘው አቤት ሆስፒታል ሕይወት ለማትረፍ ይከንፋሉ፡፡ የአቤት ሆስፒታል ሐኪሞች በጭንቅላቱ፤ በአፍንጫው እና በጆሮው ደም እየፈሰሰው የነበረውን የባህል አምባሰደሩን ለማትረፍ የተደረገው እርብርብ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ … ነፍስ ይማር!›› ሲሉ አቶ ልዑልሰገድ ቀፀላ በስልክ ባደረግነው ቆይታ የዓይን እማኝነታቸውን ነግረውኛል፡፡ RIP

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.