የጎንደር ዩንቨርሲቲው አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 14 ሰወች በከፈተኛ ሕክምና ላይ ናቸው – ሙሉቀን ተስፋው

ጉዳቱ የደረሰው ሕንፃው ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ እንደሆነ አረጋግጠናል፤ በጠቅላላው የተጎዱት 15 ሰዎች ሲሆኑ የአንደኛዋ ሴት ሕይወት ወዲያውኑ ነው ያለፈው፡፡ 14ቱ ጎንደር ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ በቦታው የነበሩ ሰዎች እንደነገሩን ከሆነ የደረሰው አደጋ እጅግ ሰቅጣጭ እንደሆነና ከተጎጂዎች መካከል እጃቸውና እግራቸው የተቆሩ ሰዎችም አሉበት፡፡
ግንባታውን የሚያካሒደው ዛምራ ኮንስትራክሽን የተባለ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ሲሆን ከዩንቨርሲቲው አመራሮ ጋር ባለው የጠበቀ የሙስና ሰንሰለት የተነሳ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ በመሆኑ ለንጹሓን ሰዎች መጎዳትና መሞት ምክንያት ሆኗል፡፡ ከፍተኛ ፎቆች ሲሠሩ የእንጨት መረባረብ መጠቀም እንደማይቻል አዋጅ ቢወጣም በዐማራው አካባቢ የሚገነቡ ዩንቨርሲቲዎች በሙሉ በዚህ መልኩ ነው የሚገነቡት፡፡ ከዓመታት በፊትም ዮቴክ የተባለው ሌላው የሕወሓቶች ንብረት ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቢሮን ሲገነባ ከ30 በላይ ሰዎችን በተመሣሣይ አደጋ ጨርሷል፡፡

 

ተጨማሪ መረጃ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴወድሮስ ካምፓስ ውስጥ ባለስምንት ፎቅ ህንፃ ስራ ላይ ስለ ደረሰው አደጋ አዲስ መረጃ ከተቋሙ ሰራተኞች ደርሶናል። ለልስን ስራ መወጣጫ የሰሩት እንጨት ተደርምሶ 13 ሰዎች ወድቀው ነበር። በሰዉ ከፍተኛ እርብርብ የወጡ ሲሆን 1ሴት ወድያው ስትሞት 1ወንድ የቀዶ ጥገና ቢደረግለተም መትረፍ አልቻለም። 11ሰዎች ግን ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። የህንፃ ተቋራጩ Unity Engineering ነው የሚል አዲስ መረጃም ደርሶናል። ማጣራቱን እንቀጥላለን።
AsnakewAbebe

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.