የ BBC የአማርኛ ስርጭት ተደራሽነቱ ለማን እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም – ቨሮኒካ መላኩ

BBC የተባለው የእንግሊዝ አለም አቀፍ ሚዲያ በሶስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞና ትግሪኛ ስርጭት መጀመሩ ይታወቃል ።
በአፋን ኦሮሞና በትግሪኛ ቋንቋ በድረገፅ የሚሰራጩት ዜናዎችና ትንታኔዎች ቋንቋውን የሚናገሩትን ማህበረሰቦች ማለትም የኦሮሞና የትግሬ ህዝብን ባህል ፣ፖለቲካ ፣ታሪክና ሌሎች ጉዳዮች በደንብ እየዳሰሰ ይገኛል።

የ BBC የአማርኛ ስርጭት ግን ተደራሽነቱ ለማን እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም ። ከወር በፊት ቢቢሲ አማርኛ ገና ሀ ብሎ ስርጭት ሲጀምር ትግራይ አካባቢ ያሉትን ታሪካዊ ቦታዎችና ባህሎች በማስተዋወቅ ስርጭቱን ጀመረ ። ቢቢሲ አማርኛ እስካሁን ከዳሰሳቸው ጉዳዮች የሚበዛው ስለትግራይና ትግሬ የሚያሰራጨው ጉዳይ ነው ።
ቢቢሲ አማርኛ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ የሚያወራው ስለትግሬ ትግራይ ብቻ ነው።
ልብ በሉ ቢቢሲ ስለ ትግሬና ትግራይ ለብቻው የሚያወራበት የትግሪኛ ፕሮግራም እያለ የአማርኛውንም ትግሬዎቹ ተቆጣጥረውታል። ይሄ በጣም ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ነው። BBC የአማርኛ ፕሮግራም ለአማርኛ ቋንቋ ባለቤቶች ስለሆኑት የአማራ ህዝብና ሌሎች ቋንቋውን ስለሚናገሩት ብሄር ብሄረሰቦች አንድም ዘገባ ሰርቶ አያውቅም ።

ለመሆኑ ቢቢሲ ለአማርኛ ፕሮግራሙ የቀጠረው ጋዜጠኛ ማነው? ለአማርኛ ፕሮግራሙ የቀጠረው ጋዜጠኛ የትግራይ ተወላጅ ነውን። BBC ለትግርኛ ፕሮግራሙ ትግሬዎችን ለአፋን ኦሮሞ ኦሮሞዎችን ሲቀጥር ለአማርኛ ፕሮግራሙ የቀጠረው ጋዜጠኛ ከቋንቋው ባለቤት ህዝቦች ለምን አልመረጠም ? Amhara Mass media ውስጥ የሚሰሩ የኢትዮጵያን የጋዜጠኝነት ሙያ እስካሁን ባልታየ መልኩ ከፍ ያደረጉ እንደ የሺሐሳብ አበራ ያሉነ ሌሎች ጋዜጠኞች ለምን አልተወዳደሩም?
BBC ገና ስርጭት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ልጀምር ነው ሲል አላማረኝም ነበር ። አሁን ይሄው ስጋቴ እውን እየሆነ ነው። የእነ ድምፀ ወያኔ ፣ ዋልታ እና ፋና ስለአንድ ህዝብ የሚያቀረሹብን አንሶ ቢቢሲ አማርኛም ስለትግሬና ትግራይ በራሳችን ቋንቋ እየጋተን ይገኛል።
ማንኛውም የአማራ ተወላጅና የአማራ ወዳጅ ቢቢሲ አማርኛ የጀመረውን ጠማማ እና አጥፊ መንገድ ማሳወቅና ማስተካከል መጀመረን አለብን።
በመጨረሻ ለቢቢሲ አማርኛ የተቀጠሩት ጋዜጠኞች ጣቢያውን የራሳቸው ስውር አጀንዳ ማራመጃ ማድረጋቸውን እንድያቆሙ እንጠይቃለን ነገር ግን በዚሁ ከገፉበት ለዋናው ማሰራጫ ጣቢያ የቅሬታ ማመልከቻችንን ከነማስረጃው የምናቀርብ መሆኑን ይታወቅልን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.