በራያ አከባቢ እየተደረገ ባለው ግጭት ሶስት የራያ ገበሬዎች ቆስለው መሆኒ ከተማ እንደገቡ ተነግሯል – አማረ ጉበን

ዳንደ ተብሎ የሚጠራ የራያ ቦርደር አከባቢ እየተደረገ ባለው ግጭት ትናንት መስከረም 30፣2010 ሶስት የራያ ገበሬዎች ቆስለው መሆኒ ከተማ እንደገቡ ተነግሯል:: ከቆሰሉት ሶስት ሰዎች አንደኛውን ሂወቱ እንዳለፈም እየተሰማ ነው:: በዓፋር ወገንም የቆሰሉ እና የሞቱ አሉ ተብሏል:: ያሳዝናል::

በአሁኑ ስዓት አይደለም መሳርያ እና የእንጨት በትር እንኳን ይዞ እንዳይንቀሳቀስ የተከለከለው የራያ ገበሬ ከባድ መሳርያ ከታጠቁት የዓፋር ጎረቤቶቹ ጋር ሲኔጻጸር ትልቅ ልዩነት ተፈጥራል እየተባለ ነው:: የዓፋር ህዝብ የራሱ ክልል ተሰጥቶት፣ በራሱ ልጆች እየተዳደረ ፖሊሱም፣አስተዳዳሪውም ዓፋር ነው:: የራያ ህዝብ በቅኝ ግዛት ስር ያለ ህዝብ ነው:: ለ25 ዓመት ያስተዳደሩት ሰዎች አከባቢውን ምንም የማያውቁ ከመካከለኛ ትግራይ የመጡ ሰዎች ናቸው:: በዚህም ምክንያት የራያ ህዝብ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል:: የተወሰኑት ለመጥቀስ:
1) የተፈጥሮ ሃብቱን ጠፍቷል
2) ልጆቹ በገፍ ለስደት ተዳርገዋል
3) ለማንነት ቀውስ ተዳርጓል
4) ህዝቡን ሳያማክሩ እንደ ጨርጨር ያሉ ነባር የአከባቢ አስተዳደሮች ጠፍተዋል
5) ለከፋ ኢኮኖምያዊ ችግር ተጋልጧል

የራያ ችግር ጎረቤቶቻችን ዓፋር አይደሉም:: የኛ ችግር ምን እንደሆነ ፣ ማን እዚህ ደረጃ እንዳደረሰን ራሳችን እናውቀዋለን::ትንሽ ከስደት የተረፉት ወንድሞቻችን በዚህ ትርጉም በሌለው ግጭት ምክንያት ሂወታቸው ማለፍ የለበትም:: የራያ እና የዓፋር ህዝቦች ለዘመናት አብረው ኑረዋል:: ለወደፊቱም አብረው ይኖራሉ:: መታረቃችን እና አብረን መኖራችን ላይቀር ብዙ ጉዳት ሳይደርስ ግጭቱ እንዲቆም የሚመለከተው ሁሉ የቻለውን ማድረግ አለበት::

Amare Guben

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.