የአሜሪካ ሬዲዮ ቪኦኤ የአማርኛው ክፍል የማህበረ ቅዱሳን ድምፅ መሆኑን በድጋሚ አረጋገጠ – ዘማርያም

 

ማህበረ ቅዱሳኖች ህጋዊውንና  ስደተኛውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተሃድሶ ብለው በመፈረጅና የአትላንታ ቅድስት ማርያም ካቴድራልን አባላት በመከፋፈል በሰሩት ስራ ጭምር ምዕምናን በሁለት ተከፈሉ።የገንዘብ ዝርፊያን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ችግሮች አሉ። በአቡነ መርቆርዮስ የሚመራውን ስደተኛውንና ህጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ አንቀበልም የሚለው ዘራፊው ሃይል የካቴድራሏን ሊቀ ጳጳስ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት በድፍረት ከግቢያችን በ24 ሰአት ለቀው ይውጡ የሚል የፅሁፍ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ለዚሁም የዲካልብ ካውንቲን ፖሊስ አቆመ።

አብዛኛው የቤተክርስትያኗ አባላት የተላላኪውን የቦርድ ቡድን ውሳኔ በመቃወም በነበረው ግርግር ልክ የዛሬ አመት ላይ ካቴድራሏ ታወከች።ዘራፊዎቹም ለማምለጫነት ማህበረ ቅዱሳንን ሙጢኝ በማለት የሃይማኖት ልዩነት እንዳለ ለማሳየት ሞከሩ።ሊቀ ጳጳሱን ያባረሩት ስምንት የቦርድ አባላትንና ሌሎች ሰላሳ የሚሆኑ በስም ያልተለዩ ምዕምናንን በቤተክርስትያኗ ቅጥር ግቢ አይድረሱብኝ የሚል የህግ ማገጃ አወጡ። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ተመልክቶ በሁለት የተከፈሉ ምዕምናን እሁድን በፈረቃ ማለትም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ እንዲጠቀሙ አዘዘ።

የቤተክርስትያናችን ሊቀ ጳጳስ ላይ ክስ ያላቸው ክሳቸውን ለማህበረ ምዕምናን ጉባኤ ማቅረብ፤ማህበረ ምዕምናኑም ከሲኖዶስ ጋር በመሆን የቀረበውን ክስ ተመልክቶ የመጨርሻ ውሳኔ መስጠት ነበረበት።አመፀኞቹ አስር የቦርድ አባላትና የቁጥጥር ኮሚቴው የማህበረ ምዕምናን ጉባኤውን ስብሰባ በአመት አንድ ጊዜ መጥራት ነበረባቸው። በሃሳባቸው አብዛኛው አባላት እንደማይስማሙ ስለገባቸው ሁለት አመት ሙሉ አንድም የማህበረ ምዕምናን ስብሰባ ሳይጠራ በተወሰደው አምባገነናዊ ውሳኔ ሊቀ ጳጳሱ ታገዱ።

አባታችን በቤተክርስትያኗ ያላቸው በስርአት የመዳኘት መብታቸው ተረገጠ ፤የአባላት መብት ተረገጠ፤በመነጋገር ሊፈታ ይችል የነበረው ችግር ተካሮ ወንድምና እህት፤እናትና ልጅ ፤ባልና ሚስት፤ህፃናት ከጓደኞቻቸው፤ማህበርተኛ ከማህበርተኛ ፤ዘመድ ከዘመድ ፤ወገን ከወገን ተለያየ።ለምን ስንል የቤተክርስትያኗ መተዳደርያ ደንብ ባለመከበሩ ወይም በመጣሱ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወንድማችን ሃብታሙ አያሌውና አምባገነናዊውን ቡድን በስውር የሚመራው ዳንኤል ክብረት የአትላንታን ማህበረሰብ ትኩረት በሳበ መንገድ እጅግ ተቃራኒ በሆኑት በነዚህ ሁለት ጎራዎች ቆመው ሃይማኖታዊ ትንታኔ ሲሰጡ ተመለከትን።

  1. ብርቅየውና በወርቅ የተፈተነው ወንድማችን አቶ ሃብታሙ አያሌው ሴፕቴምበር 30 የሚከተለውን መልዕክት አስተላለፈ። የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አሁን ያለችበት ቀውስ ውስጥ እንድትገባ ሆን ብሎ ሌት ተቀን የሰራው ህወሃት መሆኑን አስረዳን።የሊቃውንት ጉባኤ መፍረሱን በዚህም ተጠቅመው ግለሰቦችና ማህበሮች የፈለጉትን እየፃፉ በቤተክርስትያኗ ስም መፅሃፍ እያተሙ መቸብቸባቸውን ነገረን።ከዚህ በፊት መዝሙር እንኳን ሲወጣ በሲኖዶሱ ይታይ እንደነበረና ያም በመቅረቱ የፈለገው ዘማሪ የፈለገውን በመዘመሩ ፤ጭቅጭቁ ወደምዕምናን መግባቱንና ይህም የትልቁ ህዝብን የመከፋፈል አጀንዳ አካል መሆኑን አስተማረን።አስደመመን።

የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንደማትታደስ፤እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እራሷ ጌታችንና መድሃኒታችንን እየሱስ ክርስቶስን ይዛ መሰደዷንና ታምራት ላይኔ እራሱ ቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ በመንግስት ጫና ከሃገር ውጪ እንዲወጡ መደረጉን እየነገረን ለምን ተሰደዱ ማለት ትክክል አለመሆኑንና፤ ሁላችንም ስደት ላይ ያሉ አባቶችን ተረባርበን ስደት ላይ ባሉበት ሃገር እየደረሰባቸው ካለው ጥቃት መከላከል እንዳለብን አስረዳን መከረን።ስለሃገራችንም ጉዳይ ዝም እንዳንል ቃል አስገባን።

  1. ዳንኤል ክብረት በሳምንቱ ኦክቶበር 7. ስደት ላይ ያሉ አባቶች ላይ ካመፀውና የማህበረ ቅዱሳንን ጎራ ተቀላቅሎ ስደት ላይ ባሉ አባቶች ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ጥቃት እያደረገ ባለው የከሳሹ ወገን የክብር እንግዳ ሆኖ አውደ ምህረት ላይ ከሃብታሙ አያሌው ትምህርት ፍፁም ተቃራኒ የሆነ መልዕክቱን በዛው በአትላንታ ሰአሊተ ቅድስት ማርያም ካቴድራል አውደ ምህረት ላይ አስተላለፈ።ተደምሮ ተቀንሶ ሲያልቅ ዋና ግቡ ካቴድራሏን ከህጋዊውና ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ቀምቶ ለአቡነ ፋኑኤል ማስረከብ ነው።ዳንኤል ባሁን ሰአት እዚህ አትላንታ ቁጭ ብሎ ስደት ላይ ያሉትን አባቶች ለማጥቃት አስፈላጊውን ነገር ለማድረግ እየዶለተ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ነው።

ይህ ታድያ በብዙ ሰዎች ህሊና ጥያቄን የሚጭር ነው።ዳንኤል ክብረት እይሰራ ያለው ለማነው? በእውነት ተሃድሶ በካቴድራሏ አለ? ቢኖርስ አንድ ዲያቆን ሊቀ ጳጳስ ድረስ ተንጠራርቶ ተሃድሶ ማለት ይችላል? የቅንድቡ ያማረው የሰለሞን ተካልኝ ሬድዮ ለምን የከሳሹ ቡድን ድጋፍ ሰጪ ሆነ? የሚሉት የማህበረ ቅዱሳንን ድብቅ አላማ ገልፀው ማሳየት ጀመሩ።

ስለዚህ በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ክፍል  ሬድዮ ጣብያ ተሰግስገው ያሉ ፀረ ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስና ማህበረ ቅዱሳኖች አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው።ይህም ዳንኤል ክብረት የህዝብ ወገን ነው የሚለውን ስዕል በተቻለ መጠን መሳል ነው።እነደተለመደው ዲያቆን ነኝ እያለ ከሶማሊያው ክልል ፕሬዜዳንት ባልተናነሰ ማህበረሰብ የሚያውከውንና የሚያምሰውን ዳንኤል ክብረትን ተንታኝ ፤የህዝብ ተቆርቋሪ አድርገው አቀረቡልን።ያ ሳያንስ ደግሞ የአትላንታው ሁኔታ ዋናው ችግራቸው ስለሆነ ከአቶ ሃብታሙ አያሌውጋር በሃገር ጉዳይ ላይ አንድ ሃሳብ እንዳላቸው ሊያሳዩን ሞከሩ። ዳንኤል የማያምንበትን ግን ትክክለኛ ነገር መጀመርያ እንዲናገር ይደረጋል ፤ከሃብታሙ የሚጠበቀው መስማማት ብቻ ነው።ነገሩ ድብቅ ይዘት ያለው የስነ ልቦና ጦርነት ነው። ህግ ይከበር በማለቱ የተገረፈንና በፅንፈኛ ማህበር ተደራጅቶ ህግ እየጣሰ አባቶችን በተሰደዱበት ሃገር እየተከታተለ በስርአት አልበኝነት የሚያሳድድን በአንድ መድረክ በማሳየት በግና ተኩላ አንድ እንደሆኑ እንድናይ የሚያደርግ የስነ ልቦና ጦርነት ።from VOA – Amharic Service

እንደተለመደው በአሜሪካ ሬድዮ ጣብያ ቀርቦ ፤የሚናገራትን አንዷን እንኳን በተግባር የማይሆነው ዳንኤል ስለሲቪክ ማህበራት መዳከምና መፈራረስ ሰበከን።ሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ እንዳያደርጉ ሌት ተቀን የሚሰራው ዳንኤል ክብረት ስለብሄራዊ እርቅም አስፈላጊነትም የሽርደዳ ዲስኩሩን በነአሉላ አቀነባባሪነት አቀረበልን፤ሸረደደን። አይ የኢትዮጲያ ሃዝብ ።ቅዱስ ሲኖዶስን በማዳከምና በማፈራረስ አላማ የተወጠረው እራሱ ዳንኤል ክብረት ። ደቡብ አፍሪካ፤ዲሲ፤ካናዳ፤ቴኔሲ፤ሎስ አንጀለስ ወዘተ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያናት ውስጥ በታዩ ብልግናዎችና ነውሮች፤ ዋና አስተባባሪና መሪ የሆነው ፤በየፌስ ቡኩ አባቶችን የሚሳደቡ የሚያዋርዱና የሚያንጓጥጡ እራሱ ፌስዳቢ ብሎ ስም ያወጣላቸው አባታቸው ዳንኤል ክብረት ስለ ሲቪክ ማህበራት ስለ ኢትዮጲያዊ ጨዋነት በአሜሪካን ሬድዮ ጣብያ የሃሰት ፍልስፍናውን ተፈላሰፈ።

አቶ አዲሱና አቶ አሉላ ፤ዳንኤል ክብረትን እቅርባችሁ ስለ ሲቪክ ማህበርሰብ መጠናከር መስበክ አትችሉም።ዳንኤል ክብረት ፅንፈኛ የሆነውና በአሁን ሰአት የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን እያወከ ያለው የማህበረ ቅዱሳን ዋና ግን ድብቅ አመራር ነው።ዳንኤል ክብረት አትላንታ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ቁጭ ብሎ ሊቀ ጳጳሳትን እየተሳደበ እያዋረደና አየባለገ ስለመቻቻል ሰለሰለጠነ ህዝብና ስላልሰለጠነ ህዝብ ሊሰብከን አይችልም።ሀገሪቱ ወደ ምስቅልቅል እየሄደች ነው ግን ለዚህ ጥፋት በተለይ በመንፈሳዊው አለም አንዱ ከፍተኛ ተዋናይ ዳንኤል ክብረትና ማህበረ ቅዱሳን ናቸው።

  1. ከማውረድ እንውርድ አለን – ከዚህ በታች የኢትዮጲያ ህዝብ የት ይውረድ?
  2. መፍትሄው ላይ የበኩላችንን እናድርግ አለን – ዳንኤል አሁን አትላንታ እየሰራ ያለው መፍትሄ ነው?
  • ተቋማዊ ኪሳራ ላይ ነን፤ተው ብሎ ሊል የሚችል የሚሰማ አካል የለም አለን – አባቶችን ሁሉ ተሃድሶ እያለ ሌት ተቀን የሚሳደብ ፤ይህን ታላቅ ተቋም ቅዱስ ሲኖዶሱን እያዳከመ ያለ ማነው?

 

ቪኦኤዎች ተጠየቁ።ህግ ይከበር ብሎ የተገረፈንና ፤ሺህ አውርቶ እንዱንም የማይሆነውን ሃሰተኛ ፈላስፋ ዳንኤልን አንድ ላይ ማቅረብና ፤ሁለቱን ተቃራኒ ሰዎች በእኩል ለሃገር አሳቢ አድርጎ ማሳየት፤ አትላንታ ውስጥ አሁን እየሆነ ያለውን እያወቅን ፤ለምን አስፈለገ? የሃገር ጉዳይ ቀዳሚ መሆኑ እንድለ ሆኖ ፤እውነተኞች ብትሆኑ ፤ሁለቱ በህዝብ ፊት ቀርበው መጠየቅ ያለባቸው በቀጥታ ማህበረ ቅዱሳን ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ላይ እያደረሰ ስላለው ጥቃት ነበር።የሰራችሁት ኢንተርቪው ከተራ ማጭበርበር በምንም አይለይም።

አዲሱና አሉላ ፤ማህበረ ቅዱሳኖች ስለሰላም ፤ስለፍቅር ፤ስለመከባበር ሊሰብኩን የሚችሉ ከሆነ ፤አንደኛችሁን ለምን የአይሲሱን አቡበከር አልባግዳዲ በሬዲዮ ጣቢያችሁ እቅርባችሁ ስለሃይማኖት መቻቻል አይሸረድደንም? አዲስ ነገር የሚባል የሬድዮ ጣቢያ ከአዲስ አበባ፤ የምናከብራቸውን የሃይማኖት አባታችንን በማያውቀው በማይመለከትውና ባልተረዳው ጉዳይ የመንግስትን ትዕዛዝ ተቀብሎ ጴንጤው ጳጳስ ብሎ የቱቲዩብ ቪዲዮ ተኮሰ።እናንተም እዚህ ቁጭ ብላችሁ ለስርአተ አልበኞቹ ለፅንፈኞቹና ለአሳዳጆቹ ለማህበረ ቅዱሳን የሚዲያ ድጋፍ ትሰጣላችሁ።

ስለዚህ በድጋሚ ልጠይቃችሁ የአይሲሱን አቡበከር አልባግዳዲ እቅርቡትና ስለሴቶች መብት ፤ስለ ሃይማኖት እኩልነት ይሸርድደን።ዳንኤልና አልባግዳዲ የሚለያዩት በመግደልና ባለመግደል ነው።ሁለቱም ስለሲቪክ ማህበራት ደንታ የማይሰጣቸው ፅንፈኛ የሃይማኖት አሸባሪዎች ናቸው።

ይህን የተሸበረ ቤተሰቡ የታመሰ አይስተውም።

ዘማርያም

ከአትላንታ

(like me on Facebook – Ze Mariam)

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.