የማለዳ ወግ … ለሁሉም ጊዜ አለው ” ጊዜ ለኩሉ ”  – ነቢዩ ሲራክ

* የተሜ እናት አንገቷን ቀና የምታደርግበት ቀን ሩቅ አይደለም

ጥበበኛው ሰሎሞን ” ቦ ጊዜ ለኩሉ ” ለሁሉም ጊዜ አለው አንዳለው ይህች የትንታጉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት አንገቷን ቀና የምታደርግበት ቀን ሩቅ አይደለም … እናት በግፍ ፍርድ ፣ በግፍ እስር ድፍን ሶስት አመታትን በጽናት ካሳለፈ ጎልማሳ ልጇ ባላነሰ በአብራኳ ክፋይ ስቃይ ተሸማቃ ፣ የልጅ ወዳጇን ፍቅር ተነጥቃ ፣ በገዛ ሀገሯ ፣ ለገዛ ሀገሯና ለገዛ ወገኗ መብት የቆመ ልጇን ስቃይ እያየች በሰቀቀን ተደቁሳ ያሳለፈቻቸው የጽናት ሶስት አመታት በተወሰነው የእስር ፍርድ ወቅት ካከተመ ዛሬ ተመስገን ከእስር ነጻ ወጥቶ እናየዋለን !

ህገ መንግስቱ ተድጦ ተሜ ያሳለፈው ፈተና ዛሬ ለማብቃቱ “የቅጣት ጊዜውን ጨርሶ ይፈታል” የሚለው ህግ ሲተገበር ስናይ ይሆናል ። በእርግጥም ዛሬ ሌላ ምክንያት ካልተፈጠረ ተሜን በጊዜ ለኩሉ እንቀበለው ዘንድ የአመታት ሰራዎቹ ” ጊዜ ለኩሉ ” መድበል ተበርክቶልናል ። እናትም የሚወዱት ልጃች ተፈትቶ የቋጠሩትን ስለት ያስገቡና ስለሆነው ሁሉ ፈጣሪያቸውን ያመሰግኑ የደፉት አንገታቸውን ቀና ጊዜ ለኩሉ አንዲሉ ጊዜው አሁን ይሆን ዘንድ የቀረው ሰአታት ብቻ ነው !

ለሁሉም ጊዜ አለው ” ቦ ጊዜ ለኩሉ ”

ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.