የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይፈታም አሉ – ታሪኩ ደሳለኝ

 

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይፈታም የዝዋይ እስር ቤት
ሀላፊዎች መንግስት የፈረደውን የፍርድ ቤት ሙሉ የ3 አመት እስር ያለ አመክሮ ዛሬ የጨረሰው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝበእራሳቸው ፍርድ አሰጣጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዛሬ መፈታት ሲኖርበት የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አልፈታም በወሏል። ይህ ሁኔታ ቀድሞም የተመስገን እስር ፖለቲካ እንደነበር ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው።

ትላንት ጥቅምት 2/2010ዓም ተሜን ጠይቄው ስወጣ እግረ መንገዲን እስረኛ አስተዳደር ገብቼ እስሩን ስለሚጨርስ ሰው ላናግራችሁ ነበር ስል አንዱ ሰው “ላጣራልህ” ብሎ ሲነሳ “ስሙን ልንገርህ” ስለው “አቃለሁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይደል” ብሎኝ ወጣ አይ ያውቀዋል ያቁኝል ማለት ነው ብዬ አጣርቱ እስኪመጣ ጠበኩት። ይህ ሰው የስራ ሀላፊነቱን የማላውቀው ጊጡ የተባለ ሰው ነው። እንደመጣ እያየኝ ተመስገን ነገ ነው የሚፈታው አለኝ ሰምቼው ወጣሁ።
ለነገሩ ባይለኝም ቢለኝም የተፈረደበትን ሙሉ 3 አመት የሚጨርሰው ነገ ጥቅምት 3 ነው አለኝ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንግስት በፍርድ ቤቱ የወሰነበትን እስር ቢጨርስም አሁን ደግሞ የእስር ቤቱን ሌላ እስር ጀምሯል።

እንግዲህ የተመስገን ህይወት በተመለከተ የዝዋይ እስር ቤት አስተዳደሮች ሀለፊነቱን ይወስዳል ነው። ተመስገን ላይ የሚደርሰው ነገርስ ሁሉ ያሳስበናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.