ነቀምቴና ጊምቢ ላይ ዛሬም የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ – ሰሎሞን አባተ(VOA)

 

በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴና በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ከተሞች ከትናንት ምሽት አንስቶ ዛሬም የተካሄዱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በሰላም መጠናቀቃቸው ታውቋል።

በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴና በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ከተሞች ከትናንት ምሽት አንስቶ ዛሬም የተካሄዱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በሰላም መጠናቀቃቸው ታውቋል።በሁለቱም ከተሞች ውስጥ ሰልፎቹ ሲካሄዱ በክልሉ ፖሊስ አባላት የታጀቡና ሰላማዊ እንደነበሩ ለደኅንነታቸው በመስጋት ስሞቻቸው እንዳይነገር የጠየቁ የተቃውሞው ተሣታፊዎች ለአሜሪካ ድምፅ የኦሮምኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች ገልፀዋል።

ሰልፎቹ በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መፈናቀላቸው እንዲቆም፣ ወደ ቤት ንብረታቸው እንዲመለሱ፣ ሕዝብን ያፈናቀሉና ሕይወት ያጠፉ ለሕግ እንዲቀርቡ የጠየቁና በሁለቱም ከተሞች የተሰሙ መፈክሮች ተመሣሣይ እንደነበሩ ታውቋል።

በሌሎችም የወለጋ ወረዳዎች በኖሌ ካባና አላባም ተመሣሣይ የተቃውሞ ሰልፎች መካሄዳቸው ታውቋል።

ሰሞኑን ተመሣሣይ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ሻሸመኔ፣ አምቦና ወሊሶ ውስጥም የተካሄዱ ሲሆን በተለይ ከትናንት በስተያና ትናንት በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማና በቦረና ዞን ሶዳ ቀበሌ ላይ በመከላከያ አባላት በተከፈቱ ተኩሶች ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ምሥራቅ ሃረርጌ ዞን ውስጥ በምትገኘው ጨለንቆ ከተማ ደግሞ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች መገደሉ መዘገቡ ይታወሣል።

የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱባቸው አብዛኞቹ ከተሞች ዛሬ ሰላማዊ መሆናቸው ታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

[jwplayer mediaid=”39217″]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.