በሶማሌያ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ከ200በላይ ደረሰ

በወንድወሰን ተክሉ

በሞቃዲሾ ከተማ ትናንት በደረሰ ሁለት ተከታታይ ፍንዳታ የሞቱት ሶማሊያዊያን ቁጥር ከ200 በላይ መሆኑን ፕሬዚዳንት ፋርማጁ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ፋርማጆ ትናንት ማታ ከዛሬ ጀምሮ የ3ቀን ብሔራዊ ሀዘን ያወጁ ሲሆን ዜጎች ደም እንዲለግሱ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን የቱርክ መንግስትም አስቸካይ የአምቡላንስና ህክምና ባለሙያዎችን እርዳታ ልከዋል።
በትናንትናው ዘገባችን በተከታታይ ሁለት ፈንጂ ፍንዳታዎች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ30በላይ መሆኑንና ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል የገለጽን ሲሆን ዛሬ ከሞቃዲሾ መንግስት መግለጫና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ገለጻ የማቾቹ ቁጥር ወደ 220 እንደደረሰ የተገለጸ ሲሆን በሞቶ የሚቆጠሩት ደግሞ እንደቆሰሉ ተገልጻል።
በሞቃዲሾው እጅግ በርካታ ሰዎች የንግድ ልውውጥ በሚያካሄዱበት ወሳኝ የገበያ ቦታ በመኪና ላይ የተጠመዱ ሁለት የቦምብ/ፈንጂ ፍንዳታዎች በተከታታይ በመፈንዳታቸው የማቹች ቁጥር ሊያሻቅብ መቻሉን ለማወቅ ተችላል።

በፍንዳታው በርካታ የንግድ ተቃማች፣መኖሪያ ቤቶችና ተሸከርካሪዎች እንዳልነበረ ሆነዋል።

በጠንካራ ማእከላዊ መንግስት እጦት ፍዳዋን እያየች ያለችው ሶማሊያ አልሸባብ የተባለ ሀገር በቀል ጽንፈኛና አሸባሪ ቡድንን ጥቃት ላለፉት ዓመታት ስታስተናግድ ያለች ሀገር ስትሆን የትናትናውን አሰቃቂ እልቂትን ያስከተለ የቦብም ጥቃት በዋና ከተማዋ ስታስተናግድ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በሃይለኝነቱ የመጀመሪያው ነው።
በሶማሊያ ለሚደርሰው የቦምብ ጥቃት ፈጥኖ ሃላፊነቱን በመውሰድ የሚታወቀው አልሸባብ በዛሬው አደጋ እስከ አሁን ሃላፊነትን ሲወስድ አልተደመጠም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.