የትምህርት ነጋዴዎችን ማን ይቆጣጠራቸው – ታዛቢዋ ፍሬ


ትምህርት የአንድ አገር ልማትና የስልጣኔ መሰረት ነው። ስለትምህርት ሲታሰብ ስለ አገር ልማትና ዕድገት ይታሰባል። የአገር ልማትና እድገት ደግሞ በዜጎች ዕውቀት አቅምና ጉልበት የሚፈጠር ነው። የአገር ልማትና ብልፅግና ሲታሰብ ደግሞ ዜጎች በትምህርትና በዕውቀት መታነፅና መሰልጠን የግድ ይላል። ትምህርት በግለሰብ ማንነት ጀምሮ ሁሉንም ዜጎች ይገነባል። ስለዚህ አንድ አገር ለትምህርት በሰጠችው ትኩረት መጠን ዕድገቷና ስልጣኔዋ ይለካል ቢባል ስህተት አይሆንም።

ስለትምህርት ሲነሳ የዓለም ስልጣኔ በአብዛኛው ዕውን የሆነው በትምህርትና በትምህርት ብቻ ነው ብሎ መናገር ይቻላል። ለዚህም ነው በየትኛውም አለም ዜጎች ዕድሜያቸው ለትምህርት ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ እውቅትና ልዩ ችሎታ \skill\ ለማግኘት ጥረት የሚያደርጉት። በአገራችንም የትምህርትን ፋይዳን በመረዳት መንግስት ከሚያከናውናቸው የራሱ ተግባራት ባሻገር ወላጆችም ልጆቻቸው በትምህርት የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናሉ። በተለይም የተሻለ ትምህርት አለ ብለው በሚያምኑባቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለማስተማር ከገቢያቸውም በላይ ሲቸገሩ ይታያሉ። በአንጻሩ የግል ትምህርት ቤቶች ወላጆች የሚፈልጉትን አይነት ዜጋ የማፍራት ስራቸው እንከን አልባ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። ዛሬ በዚህ ጽሁፍ ለመዳሰስ የፈለኩትም በአማራ ክልል መዲና በግል ባለሀብት ስለተመሠረተው የባህር ዳር አካዳሚ የትምህርት አሰጣጥና የውስጥ ገበና ነው።

ትምህርት ቤቶች ብቁ ዜጋ ከሙስና የፀዳ የሀገር ፍቅር ያለው ተወዳዳሪ ምክንያታዊ ትውልድ የመቅረፅ \ የመፍጠር \ ሀገራዊ ግዴታ አለባቸው። ከዚህ አንፃር የግል ትምህርት ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎት ሲመዘን ሀገራዊ ራዕይ ያለውን የትምህርት ፖሊሲ ሙሉ በመሉ የሚፃረር ተግባር ሲፈጽሙ ይታያል።

ይኸው አካዳሚ በመማር ማስተማሩ ሂደት ያለው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ከመምጣቱ በላይ በዚህ ዓመት ሁለተኛ ቅርንጫፉን ዓባይ ማዶ አዲስ ዓለም ካምፓስ መክፈቱና ሥራ መጀመሩ አነጋጋሪ ቢሆንም በዋናው የባህርዳር አካዳሚ ካምፓስ እየተሰጠ ያለው ትምህርት የትውልድ መቅረጻ ሳይሆን የትውልድ ማምከኛ መሆኑን በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡አካዳሚውን በበላይ ኃላፊነት የምትመራው ባለቤቷ ሳትሆን አንዲት ኤርትራዊት የሻቢያ ተላላኪ ዘውዲቱ ኅሩይ የምትባል የጃጀች አሮጊት ነው፡፡ ግለሰቧ ከነግብረ አበሮቿ ማለትም ከሁለቱ መሠረቶች፣ ትግዕስት፣ ሰላም እና አዜብ ከሚባሉ የየክፍል ደረጃ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ተቋሙን ከመማሪያ ወደ መማረሪያ እየቀየሩት ነው፡፡

ወላጆች ልጆቻችን ይማራሉ ብለው ያስመዘገቧቸውን ተማሪዎች ተገቢውን ዕውቀት እንዲያገኙ ከማድረግ ይልቅ በአካዳሚው የተመደቡ መምህራን፣ ረዳት መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በሻቢያ ተላላኪዋ ዘውዲቱ አጋፋሪነት በሃይማኖት፣ በመኖሪያ አካባቢና በጓደኝነት በመከፋፈል የመማር ማስተማሩን ተግባር ወደ ጎን በመተው የቅራኔ መፍጠሪያ መድረክ እየከፈቱ መነታረክ የዘወትር ተግባራቸው ሆኗል፡፡

የባህር ዳር አካዳሚ ዋናው ካምባስ

ትምህርት የአንድ ቀን እወቁልኝ አልያምአአአአለ የአንድ ቀን እንኳን ደስ አላችሁ! ደስ ብሎናል የሚባልበት ሥራ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ እውቀትም ጧት ታይቶ ማታ የሚጠፋ አይደለም። ትምህርት በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ የሚኖር ዘላለማዊ ተግባር ነው። ከሌብነት ሁሉ የከፋ ሌብነት ከማጭበርበር ሁሉ የከፋ ማጭበርበር በእውቀት ላይ የሚፈፀም ሌብነትና ማጭበርበር ነው። በትምህርት ቤቱ ያለውን ከመጠን በላይ የሆነ ንትርክና ከልክ ያለፈ ህገወጥ የማስተማር ተግባር መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል። ለዚህም በአካዳሚው ግዴታቸው በመወጣት ነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች ትክክለኛ ትምህርት እንዲያገኙ መስራት አለባቸው። በአካዳሚው የተመደቡ የትምህርት ባለሙያዎች የሙያ ስነምግባርና ሰብዕና የተላበሱ እንዲሁም የአካዳሚው ባለቤት በመምህር ስም ተመድበው የተቋሙን ህልውና የሚፈታተኑ ነገር አመላላሾችን በማጽዳት የመማር ማስተማሩን ተግባር ማስተካከል ቀዳሚው ተግባር ሲሆን በበበበየሚመለከተው የክልሉ ትምህርት ቢሮ በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት በየጊዜው በመከታተል የትምህርት ፖሊሲውን በተገቢው እንዲተገበር ሃይ ሊላቸው ይገባል፡፡ በግል ትምህርት ቤቶች ወላጆች ችግራቸውን ችለው እንጂጥሪታቸውን በማፍሰስ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት ነገ የተሻለ ነገር ያገኛል በማለት እንጂ ከመንግስት ጋር ድብብቆሽ የሚጫወት አጭበርባሪ ትውልድ ለመፍጠር አይደለም። በትምህርት ላይ ለሚነግዱት ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት ገደብ ሊያበጅለት ይገባል ባይ ነኝ፡፡

ታዛቢዋ ፍሬ ነኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.