በረከት ስሞን እንደተባለዉ ገዱ አባሮት ሳይሆን የራሱ frustration ፤የድካም ስሜትና ኩርፊያ ከቦታዉ ገለል እንዲል አድርገዋል

 በርግጥ ከሁለት አመት በፊት ባህርዳር ላይ አንተ ፌደራል ላይ ሆነህ ጫና እየፈጠርክብን ነዉ ብለዉ በግልጽ የብአዴን አባላት ጥያቄ አቅርበዉለት ነበር፡፡ እንደዛ እማ ከሆነ አመስግናለዉ ተሰናብቻለዉ፡፡ እኔም ደክሞኛል ባልቴቤቴም ከፖለቲካዉ ገለል እንድል ትፈልጋለች ብሎ በልመና ቢያንስ የብአዴን ማእከላዊ አባላችን ሁነህ ትቀጥላለህ ተብሎ አንድ ቀን ሙሉ ሲጀበጀብ ነበር፡፡ እጅግ አኩራፊ ከመሆኑ የተነሳ የብአዴን የኮሚቴ አባል አልሆንም በማለቱ ስብሰባዉ ለአንድ ቀን ተራዝሞ በልመና ነበር የገባዉ፡፡ እንዴት ተናገሩኝ በሚል ነበር አባል አልሆንም ያለዉ፡፡

ሌላዉ ባለፈዉ አመት ጎንደር ከተማና ወደ አርማጭሆ ወረድ ብሎ ስብሰባ ሰብስቦ ነበር፡፡ በተለይ ጎንደር ላይ የእናትህን አጽም ከባታ ማሪያም አዉጥተን አስፓልት ላይ አንከሰክሳለን ሲሉት፡፡ በተመሳሳይ ስብሰባ ትልቅ የጎንደር ሽማግሌ ስብሰባዉ ላይ ቆመዉ እያለቀሱ ልጅ አይዉጣልህ፤ አብልተንህ፤አጠጥተንህ፤አሳድገነህ እንዴት ካለልጅ ታስቀረናለህ ብለዉ ረግመዉት ስብሰባዉን ጥለዉ ሄዱ፡፡ በሁለተኛዉ ቀን ስብሰባ አንድ ዘመዱ የተገደለበት ወጣት በረከትን አንተ ደም መጣጭ የዘመዶቸን ደም የመጠጥክ ብሎ ዘሎ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞበት ስብሰባዉ እንደፈረሰ እናስታዉሳለን፡፡
በረከትም ይሄ ሁሉ በየስብሰባዉ ሲነገረዉ እንዲህ አዳምጦ ይሄዉ ሁለት ደብተር ሙሉ የነገራችሁኝን ነገ ፌዴራል ላይ ሳልጨምር ሳልቀንስ አቀርባለዉ፡፡ ወታደሩ ከጎንደር እንዲወጣ ለመንገር እሞክራለዉ፡፡ ነገር ግን ወታደሮች ከእኛ ትዛዝ ዉጭ ሆነዋል፡፡ ነጋዴ ሆነዋል አልሰማ ብለዉናል ነበር ያለዉ፡፡ ስለወልቃይትም ሲጠየቅ ሁሉንም አቀርባለዉ ቢያንስ እንኳን የነዳንሻ ጉዳይ አንደገና መታየት ያለበት ይመስለኛል ብሎ ነበር የሄደዉ፡፡

ከዚህ ሁሉ ነገር ግን አንድም ያሰፈጸመዉ ነገር የለም፡፡ ህወሃት በረከትን አይሰማዉም፡፡ በረከትን ሚሰሙትና ሚፈልጉት ብአዴን ዉስጥ ወይም አማራ ክልል ዉስጥ የሆነ ነገር ማድረግ ሲፈልጉ ብቻ ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት በረከት በህወሃት ተስፋ እየቆረጠ እንደመጣ ያሳያል፡፡ በርግጥ ሰሞኑን ባህርዳር ላይ በነበዉ ስብሰባም በረከትን ተጠያቂ ያደረጉ አንዳንድ የብአዴን አባላት ነበሩ፡፡ በረከት እንዲህ አድርገሃል ተብሎ ሲገመገም የማይወድ ሰዉ ነዉ፡፡ እሱ ሌላዉን መገምገም ብቻ ነዉ ደስ የሚለዉ፡፡ በነዚህ ምክንያቶች በረከት እረፍት መዉስድ የፈለገ ይመስላል፡፡ በተለይም ግን የህወሃት ግትርነት፤ የሃይለማሪያም ድንዙዝነትና የብአዴን መዝረክረክ እያበሳጨዉ ከዚህ ቢፊት የነበረበትን የሳይኮሎጂካል ችግር (neurosis) አሁን ካለዉ ብስጭትና frustration ጋር ተደማምሮ ወደ ፊዚካላዊ የጤና ችግር እየተለወጠበት ስለሆነ ስራዉን ትቶ እድሜዉን ማራዘም ፈልጓል፡፡ ዞሮ ዞሮ በረከት የለቀቀዉ የኔን ሃሳብ የሚያደምጥ ጠፋ፡፡ አልሰማኝ አሉ እንዲሁም ለጊዜዉም ቢሆን irrelevant ሆንኩ የሚል ስሜት ስለተሰማዉ ነዉ፡፡ ድርጅቱን ከቀድሞ አለቃዉ ጋር ሆኖ ቀጥቅጦ እንደሰራዉ የሚያስበዉ በረከትም እሱ እዛዉ ዉስጥ እያለ ሲፈራርስ ማየት የፈለገ አይመስልም፡፡ የበረከት መልቀቅ ጫናዉ ህወሃት ላይ ብቻ ሳይሆን ሃይለማሪያም ደሳለኝ ላይም ነዉ፡፡ ሃይለማሪያም እራሱ ስለ ስልጣኑ እንዲያስብና እራሱን እንዲጠይቅ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የብአዴን የበታችኛዉ ካድሬ ላይ ዉዥንብርና ፍርሃት የመፍጠር ስሜት ይኖረዋል፡፡ ባጠቃላይ በረከት የለቀቀዉ ደስተኛ ባለመሆኑ ነዉ፡፡ ዶክተር ስንታየዉ ከንግድ ባንክ አባረረዉ ሚለዉ እራሱ አስቂኝ ነዉ፡፡ አማራ ክልል ዉስጥ እንደ ዶክተር ስንታየዉ የሚናቅ የብአዴን አባል የለም፡፡ እንኳን በረከትን ሊያባርር ዉሻ አያባርም፡፡ በረከት በራሱ ብቻ የወሰነዉና ግጥም እየጻፈ ከተፈራ ዋልዋ ጋር ማይክሮስኮፑን ቀና እያደረገ አብሪ ኮከብ ሲቆጥር መዋል ነዉ የፈለገዉ፡፡

በረከት ነገም ከብአዴን ማእከላዊ አባልነቱ ጠቅልሎ መዉጣተቱ አይቀርም፡፡ የበረከትን ሚና ለመጫወት ብአዴን ዉስጥ ትልቅ ፍትጊያ እንደሚኖር መገንዘብ ይቻላል (ደመቀ መኮነን የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆኑ የአንድ ቡድን ማለትም የብአዴን public face መሆን ሊከብደዉ ይችላል)፡፡ የበረከትን ጥላ ፈርተዉ ይኖሩ የነበሩ የብአዴን አባላትም emboldened የሚሆኑበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ የነአለምነዉ ቡድን በበረከት መልቀቅ ትልቁ ተጎጂ መሆኑ አይቀርም፡፡ አለምነዉ አሁንም እራሱ ከነባር የብአዴን አመራሮች ጋር የተካረረ ጠብ ዉስጥ ነዉ፡፡ ልክ እንደ ህወሃት አማራ ክልል ላይ ያለዉን ደህንነት ስለያዘ ብቻ ነዉ ጎልብቶ የታየዉ፡፡

(Miky Amhara)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.