‘ከኤሊባቡር ንፁሃን አማሮች ጭፍጨፋ በስተጀርባ’ 

 

ፀጋዬ አራርሳ
ፀጋዬ አራርሳ

ፀጋዬ አራርሳ በኢሊባቡር በተፈፀመው ዘግናኝ ዘር ተኮር ግድያ ጀርባ ያለውን እውነት እንድንመረምር ፍንጭ ሠጥቶናል::

እንዲህም ብሏል:-
“ኦነግ እኛ ከኦህዴድ ጋር ያደረግነውን የስልጣን ክፍፍል ስምምነት ኦነግ በቅናት ዓይን እየተመለከተው ነው:: የተቃውሞ ሠልፉንም የጠራው የኦነግ ክንፍ የሆነው ‘OLF-Shanee’ነው “ሲል ይፈርጃል::
(ጥቅምት 11/2017)

“በ1992 ላይ እኦህዴድ ኦነግን ለመደምሰስ ከህወሃት ጋር ሰርቷል::በ2017 ኦነግ ኦህዴድን ለማጥፋት ከህወሃት ጋር ወግኗል::ወዳጅ ጠላት ጠላትም ወዳጅ እየሆነ ነው…”ይለናል::
(ጥቅምት 12/2017)
ኦነግ የህወሃት አጋር ኦህዴድም የኦሮሞ አክቲቪስቶች ስልጣን ተጋሪና ተባባሪ ነው ከተባልን ጉዳዩ ወደ ኤሊባቡር ንፁሃን አማሮች ጭፍጨፋ ላይ የማን እጅ እንዳለበት ሁለት ምክንያታዊ ግምቶችን እንድናጤን ግድ ይለናል::

1. “ሠልፉን የጠራውና ያደራጀው ኦነግ ነው:: ግድያው የተፈፀመው በዚህ ሰልፍ ባለበት አካባቢ ነው:: ኦነግ ከህወሃት ጋር ወግኗል”ከተባልን ግድያውን ሊያቀነባብሩት የሚችሉት ኦነግና ህወሃት በጋራ ነው ማለት ነው::
2. እነ ፀጋዬ አርአርሳና አክቲቪስቶች በኦነግ የተጠራውን ሠልፍ እንደማይደግፉት በመግለፅ ከኦህዴድ ጋር ያደረጉት የስልጣን ክፍፍል ስምምነት ካለ ‘ኦነግና ህወሃት’ በአንድ ጎራ ‘ኦህዴድና አክቲቪስቶቹ’ በሌላ ጎራ ሆነው የኦሮሞ ወገኖችን ድጋፍ ለማግኘት እየተናጩ ነው ማለት ነው::

ስለዚህ የኤሊባቡር ንፁሃን አማሮች ጭፍጨፋ የተከናወነው በዚህ የስልጣን ሽኩቻ መሃል በመሆኑ

ሀ) አንድም ‘ኦነግና ህወሃት’ ከእጃቸው የወጣውን ተቀባይነት ለመመለስ ሲሉ በጋራ ማለትም ከዚህ በፊት በአርባጉጉ አማሮች ላይ በጋራ እንዳደረጉት ጭፍጨፋ,ወይም

ለ) ‘ኦህዴድና አክቲቪስቶቹ’ የኦነግና የህወሃትን ጥምረት ሚዛን ለማሣጣትና እቅዳቸውን ለማክሸፍ/political Sabotage/ በሚስጥር እጃቸውን ከተዋል እርምጃውን ወስደዋል ማለት ነው::
ሁሉም ግምቶች ወደዚህ ያመራሉ:: ለማንኛውም ሁሉም ክስተት እነዚህ አራት ተዋናይ ሃይሎች ያራግቡ የነበረውና እያራገቡም ያለው የጎሣ ፖለቲካና ጥላቻ መራር ውጤት ነው:: በበደኖ ጉራፈርዳ ወ.ዘ.ተ የታየም ነው:: ለዚህ ነው እነዚህ ሃይሎች አንድም አራትም ናቸው ማለት የምንደፍረው:: 


LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.