በስም መመሳሰል በቀይ ሽብር ክስ ተፈርዶብኛል ያሉት ግለሰብ አቤቱታ አቀረቡ (በጌታቸው ሺፈራው)

 

በስም መመሳሰል ባልፈፀምኩት ተግባር በቀይ ሽብር ክስ ተፈርዶብኛል ያሉት ግለሰብ ዛሬ ጥቅምት 14/2010 ዓም አቤቱታቸውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት አቅርበዋል።

አቤቱታቸውን ያቀረቡት አቶ አለማየሁ ገበየሁ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የህግ ባለሙያ እንደነበሩና ፈፀሙት ተብሎ ለፍርድ ምክንያት ከሆነው ድርጊት ጋር ግንኙነት እንዳልነበራቸው በአቤቱታው ተገልፆአል። ጠበቆቻቸው ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት አቶ አለማየሁ ገበያው ምንዳ የተከሰሱት የስም መመሳሰል ሊያቀል በሚችልበት መንገድ ወንጀሉን ፈፀመ የተባለው ግለሰብ ስሙ እስከአያቱ ባልተፃፈበት ሁኔታ እንደተፈረደባቸው ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል።

አቶ አለማየለሁ በሌሉበት እንደተፈረደባቸው የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከአራት በላይ በሽታ ያለባቸውና ምግብ እንኳ በራሳቸው መመገብ እንደማይችሉ ጠበቆቻቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ራሳቸውንም ተቆጣጥረው መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ጠበቆቻቸው ለፍርድ ቤቱ ያስረዱ ሲሆን አንገታቸው ላይ ደጋፊ መሳርያ ተገጥሞላቸዋል።

አቶ አለማየሁ የተፈረደባቸው ዝርዝር መረጃዎች ሳይቀርብ ነው በመባሉ ጉዳዩ በጣት አሻራ ሊጣራ እንደሚችል ፍርድ ቤቱ ጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ስለሆነ የዋስትና መብታቸው ተፈቅዶላቸው ጉዳያቸው እንዲጣራ አቤቱታምቸውን በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል።

ሆኖም አቃቤ ህግ የክስ መዝገቡ እንደሌለው በመግለፁ ክስ መዝገቡን አይቶ በአቤቱታው ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ጥቅምት 15/2010 ቀጠሮ ተይዟል። አቶ አለማየሁ ጋዜጣ ላይ የማደኛ ማስታወቂያ ወጥቶባቸው እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ተይዘው እስር ቤት የገቡት በቅርቡ ነው ተብሏል።

(የአቶ አለማየሁ ቤተሰቦች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በፅሁፍ የቀረበውን አቤቱታ አግኝቼ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ማጠቃለል አልቻልኩም)

http://www.satenaw.com/dutch-court-open-ethiopia-red-terror-war-crimes-trial/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.