ከባህር-ዳር ወጣቶች ለመላው የአማራ ወጣቶች የቀረበ የትግል ጥሪ

አማራ ያሰበው ዳር ሳያደርስ አይቆምም። እኛ ደግሞ የነዛ ጀግኖች አያቶቻችን ልጆች ነን። እኛ የባህር-ዳር ወጣቶች ተግባራዊ እርምጃ ወያኔ ላይ መውሰድ ከጀመርን ቆየት ብለናል። በተናጠል የምናደርገው ትግል በፈለግነው መጠን እየሄደ ቢገኝም ግን ይህ የከተማ ውስጥ ትግል ወደ ተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች እንዲሰፋ ለማድረግ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ እምቢተኝነቱ እየተቀጣጠለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለ። ስለዚህም ከዚህ በኋላ ከሌሎች የአገሪቱ ወጣት ወንድሞቻች እና እህቶቻችን ጋር በተመሳሳይ ወቅት አመጹን ማንሳት እንዳለብን ተርድተናል። በዚህ ሰዓት የኦሮሚያ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን አመጽ ላይ ናቸው። እኛስ የማንነሳበት ምን ምክንያት ሊኖረን ይችላል?

❖ ወያኔ/ትግሬ የአማራን ህዝብ ብሔራዊ ጠላታችን ነው ብሎ ፈርጆ ስንት ወገኖቻችን አልጨፈጨፈብንም?
❖ ስንት እናትና እህቶቻችን ዘራቸውን እንዳይተኩ ያለ እድሜያቸው አላመከኑብንም?
❖ ስንቱን የአማራ አምራች ሀይል ወጣት በሱስ እንዲደነዝዝ አድርገው ከትምህርት እና ከሥራ ውጭ አላደረጉብንም?
❖ ከራሱ አልፎ መላው ኢትዮጵያን መመገብ የሚችለውን የአማራን ገበሬን በማዳበሪያና በተለያዮ ብድሮች አቅሙን አዳከመው ራሱን እንኳ መመገብ እንዳይችል አላደረጉብንም?
❖ የአማራን ለም መረኢት ወደ ትግራይ ክልል በማካለል የእኛን ወገን ከመሬቱና ከርስቱ በማፈናቀል ለልመናና ለስደት አላደረጉብንም?

ግፉን ብንዘረዝር አንጨርሰውም፣ የሚያዋጣን የሚከፈለውን መስዋትነት ተከፍሎ ዳር ሳናደርስ ለማናቆመው ትግል መነሳት ግድ ይለናል።

ጎንደር ይሰማል? ጎጅም ይሰማል? ወሎ ይሰማል? ሸዋ ይሰማል? የወሎው ራያና ዘቦ ይሰማል? የጎንደሩ ወልቃይት ጠገዴ ይሰማል? የጎጃሙ መተከል ይሰማል? ለየብቻ እንቅስቃሴ ማድረግ ከዚህ በኋላ ሊበቃ ይገባል።

እኛ የአያቶቻችን ልጆች አማሮች ነን። አማራ ደግሞ አንድ ላይ ሲነሳ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ወያኔ/ትግሬ ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ከፋፍሎ አኖረን። ከአሁን በኋላ ግን መላው የአምራ ህዝብ አንድ ላይ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ጋር በመቀናጀት ወያኔን ልንትገለውና ልናስቆመው ሰዓቱ ደርሷል።

መላው የአማራ ህዝብ ሆይ ለማይቀረው የሞት ሽረት ትግል ታጥቀህ ተነስ!!
የባህር-ዳር ወጣቶች

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.