‘ፑቲንን ለመግደል ያሴረው ሰው’ ሲቆስል ሚስቱ ተገድላለች

ባልና ሚስት በበጎ ፈቃደኝነት ከዩክሬይን ጦር ጎን በመቆም በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል የሩሲያ ደጋፊዎች ሆኑ አማጺያንን ተዋግተዋል

በዩክሬይን ዋና ከተማ ኪዬቭ አቅራቢያ በደረሰ ጥቃት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ለመግደል አሲሯል የተባለው የቺቺንያው ሰው ጉዳት ሲደርስበት ሚስቱ ተገድላለች።

እንደ የዩክሬይን የሃገር ውስጥ ሚንስትር አማካሪ አንቶን ሄራሽቼንኮ ገለጻ የአዳም ኦስማቭ መኪና ላይ ተኩስ ተከፍቶ “ቢቆስልም በህይወት አለ”።

ህሌቫሃ መንደር በደረሰው ጥቃት የኦስማቭ ሚስት አሚና ኦኩዬቫ ተገድላለች ብለዋል።

እ.አ.አ በ2012 ፕሬዝዳንት ፑቲንን ለመግደል በኢስላማዊ ቡድኖች በተደረገው ሙከራ ውስጥ ኦስማቭ ተጠርጣሪ መሆኑን የሩሲያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ፑቲን በየቀኑ ይጎበኙታል በሚባለው የሞስኮው ኩቱዞቭስኪ አደባባይ ላይ ቦንብ ለመቅበር ተዘጋጅተው እንደነበር በወቅቱ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር።

ኦስማዬቭ ተላልፎ እንዲሰጣት ሩሲያ ተደጋጋሚ ጥያቄ ብታቀርብም የአውሮፓ ሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት ተላልፎ በመስጠት ላይ ለቀረበው ይግባኝ መልስ እስኪሰጥ በሚል ኪዬቭ ጥያቄውን ውድቅ አድርጋ ቆይታለች።

ባለፈው ሰኔም በኪዬቭ ከተደረገበት የመግደል ሙከራ ሊያመልጥ ችሏል። ከኦኩቫ በተከፈተ ተኩስ ጥቃት አድራሹ ጉዳት አጋጥሞታል።

ባልና ሚስት በበጎ ፈቃደኝነት ከዩክሬይን ጦር ጎን በመቆም በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል የሩሲያ ደጋፊዎች ሆኑ አማጺያንን በመዋጋት ታዋቂ ናቸው።

ስለሰኞው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ ወገን የለም።

ጥቃቱ አንድ ዩክሬይን የህግ ባለሙያ መኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ የተፈጸመ ነው።

ጥቃቱን ተከትሎ የኢሆር ሞሲይቹክ ጠባቂና ሌላ ግለሰብ ሕይወት አልፏል።

ኦኩቫ በአንድ ወቅት ህግ ባለሙያው አማካሪ በመሆን ሰርቷል።

ኪዬቭ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እያስተናገደች ነው።

BBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.