ዓረና ትግራይ በመቀሌ ከተማ ሰላማዊ ሰልፊ ለማድረግ ተከለከለ !!!  – ኣስገደ  ገብረስላሴ

በትግራይ  የሚገኝ የህወሓት  ፋሽሽታዊ   ቡዱን  ዓረና ትግራይ  በመቀሌ ከተማ ሰላማዊ ሰልፊ ለማድረግ ጠይቆ  በመቀሌ ከተማ ከንቲባ  ጽፈት  ቤት   የህወሓት  ማእከላይ ኮሚቴ  ለሆነው  ዳኒኤል  ኣሰፋ  በጽሁፍ ጠይቆ    ከንቲባ ዳኒኤልም  የሰጣቸው  መልስ  በኣሁኑ ጌዜ  በሃገር ደረጃ መጥፎ ሁኔታ ስላለ  በከተማችን  የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ኣንፈቅድም  ብሎ ለኣረና  ኣማራር  እንደመለሳቸው  ከከንቲባ ጽፈትቤት ምንጮች  ጠቁመዋል  ።
ኣያይዘው  የኣረና  ኣማራሮች   ሰላማዊ  ሰልፍ   ኣይፈቀድም  ካላችሁ  የምትሰጡን  መልስ  በጹሁፍ  ስጡን ሲሉዋቸው ነገ  ልንሰጣችሁ  እንዳሏቸው   ኣክለው  ጠቁመዋል ።
ለዚሁ የሀወሓት ቡዱን  ጸረዲሞክራሲና ጸረሕገመንግስት  ተግባር   መላው የኢትዮጱያ ህዝብ በተለይ  ደግሞ በቅርበት የዚሁ ኣፋኝ ቡዱን  ግፍ ቀማሽ የሆነው  የትግራይ ህዝብ  እምቢ ኣማራጭ ሀሳብ እንሰማለን በማለት  ተጽእኖ  ሊያሳድር እጠይቃለሁ ።
የተከበራቹ  የኢትዮጱያ  ህገመንግስት ኣንቀጽ 30   እንደሚፈቅደው ፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ስቢክ ማህበራት ፣የሃይማኖት ስበሰባዎች  ሰላማዊ ሰልፍ  ለማድረግ ከፈለጉ  ለኣካባቢ ኣስተዳደሮች  ከ48  ሰኣት በፊት የእናደርጋለን  ያስታውቁ እንጅ  ፍቀዱሉን  ብለው ኣያስተውቁም   ኣመለክቱም ። ኣስታዳዳሪዎች ቀጥሉ ኣተቀጥሉ ባይሉም  ፣ ተሰላፊዎች ወይ ተሰብሳቢዎች  መለስ ሳይጠይቁ  ያሰቡትን ይፈጽማሉ  ።መንግስትም  ጸጥታ ማስከበር ህገመንግስታዊ  ግዴታው ይሆናል ይላል ።
ይህ ህግ ግን በህወሓት እና በተላላኪ ጠፍጥፎ የሰራቸው የሌሎች  ፓርት  መሪዎች  ኣድማጭ የለውም ።  ስለዘህ  የኢትዮጱያ ህዝቦች ሁላችሁ  በኣሁኑ ጊዜ  የህወሓት  ኢህኣደግ ኣንባገነን  መሪዎች  የፈበረኩት ዘረኝነት፣ መተላለቅ  በማጀብ የነዚህ ፋሽሽቶች  ተግባር ማጀብ  ትተን የኣንድነት ሰላማዊ ዝናር በመታጠቅ በልጆቻችን ፣በወንድሞቻችን  መስዋእት  የተረጋገጠ ህገመንግስት  በተባበረ ክንድ በሰለማዊ መንገድ  በአመጽ ለውጥ ለማምጣት መዝመት  ይገባናል ።   ሞት  ልቅሶ የሃብት ውድመት የዜጎች  መታሰር መቋጫ ያግኝ ።
ኣስገደ  ገብረስላሴ  ፣
መቀለ
23  /  02  / 2010

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.