ዓረና ትግራይ ህገመንግስት  በሚፈቅድለት ፣ ነገ ጥዋትበ25/02 /2010  ሰላማዊሰልፍ ይወጣል! – ከኣስገደ ገብርስላሴ   

ኣረና ትግራይ ሰላማዊ ሰልፊ  ሊወጡ ለመቀሌ ከተማ  ከንቲባ ጽፈት ቤት እና የከማ ጸጥታ እና ኣስተዳደር  የሃገራችን  ህገመንግስት  በሚፈቅድላቸው  መሰረት   የማሳወቅ እንጅ ኣድርጉ ኣታድርጉ  የሚል ፍቃድ  ሊጠብቁ  ስለማይገደዱ  ነገ ጥዋት በመረጡት ሜዳ ባስቀመጡት ሰኣት ሰልፍ እንደሚወጡ ኣስታውቀዋል ።  የመቀሌ ወጣትም  ከንቲባው  እና የጸጥታ ሃይሎች  የሚያደርጉት  ኣፈና  እንደማያግዳቸው እየገለጹ ናቸው ።

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ   ከንቲባ ዳንኤል  ኣሰፋ ግን ጸረ በሽዎች  መስዋእት   ተከፍሎበት  የጸደቀው  ህገመንግስት   የበላይ  በመሆን በህወሓት  የመንደር  ሬድዮ ኤም  ጣብያ ኣረና ትግራይ  ነገ የሚያደርገው ሰልፍ እንዳይደረግ  ኣውጇል ።  ይህ የኣፈና  ተግባር  የኢትዮጱያ ህዝብ   በኣጠቃላይ ፣ በተለይ ደግሞ  በህወሓት  የኣፈና  ካቴና ቁጥጥር ያለኸው  እና  የታሰርክ የትግራይ ህዝብ  በኣደባባይ  ወጥተህ ኮንናቸው ።

ለዛሬው ኣንድ የሰላም ጥሪ  ለትግራይ የፓሊስ ሃይልና ልዩ ሃይል ፣ በትግራይ ያላችሁ  የመከላከያ ሰራዊት ፣ የኣገር ድህንነት ኣባላት  ፣ዓረና ትግራይ  ፓርቲ  የሚያካይደው ያለው  ሰላማዊ  ሰልፍ መእከሉ  የሰላም የኣንድነት ፣የህዝቦች ፍቀር ለሀገራችን  ህዝቦች ፣  የቢሄር  ፣የዘር ግጭት ፣ የዜጎች ሞት  ይቁም   ባይ ነው ። በተለይ በኣሁኑ ወቅት ዜጎች በየተሰማሩበት ቦታ በጸጥታ ሃይሎች እና  በህዝበች  እርስ  በእርሳቸው  መገዳደል  ይቋጭ  ባይ ነው  ። ኪራይ ሰብሳቢዎች   ሙሶኞች ፣የፓርት ባለስልጣናት በፈጠሩት  ሴራ  ዜጎች እየተቀጠፉ  ስላሉ ይህን  እልቂት መቋጫ  ያገኝ  ዘንድ   ነው ኣላማው ።

በመሆኑ ከላይ  የተጠቀሳቹህ  ጸጥታ   ሃይሎች  በሙሉ   በህወሃት መሪዎችና  ቅጥረኛና  ተጠቃሚ ካድሬዎች በመካኒካል  የኣንባ  ገነኖች ገዳይ  ትእዛዝ   እየተነዳችሁ  በዚ የሚታሰበው ሰላማዊ   የተቃውሞ ሰልፍ  መጥፎ እርምጃ  ከመውሰድ  የሰው ሂወት ከማጥፋት  እንድትጠነቀቁ  ፣የህዝብ  ሃብት  እንድትጠቡቁ  ጥሬን ኣቀርባለሁ ። ልክ እንደየእሮሞ  የፓሊስ እና የልዩ ሃይል  ሰላማውነት ተምራችሁ   እንድት ሰሩ የመቀሌ ህዝብ በኣክብሮት   ይጠይቃችዋል ።
ከኣስገደ ገብርስላሴ
መቀሌ
24  / 02  / 2010

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.