አቶ በረከት ስምኦን የሙስና ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)

በቅርቡ ከፖሊሲ ምርምርና ጥናት ተቋም ምክትል ሃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ስራቸውን የለቀቁት አቶ በረከት ስምኦን የሙስና ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።
በተለይም በ300 ሚሊየን ብር ወጪ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ደብል ትሪ ባለ አራት ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል የርሳቸውን ነው በሚል ምርመራ ተጀምሯል።

በአቶ በረከት ላይ የተጀመረው ምርመራ ሌሎች አሏቸው የተባሉና በግለሰቦች ስም የተያዙ ንብረቶችንም እንደሚጨምር ምንጮቹ ለኢሳት ገልጸዋል።
በሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ውስጥ በተፈጠረው ክፍፍል “የመለስ ሌጋሲ” የተባለውና በአቶ በረከት የሚደገፈው የእነ አቶ አባይ ወልዱ ቡድን እየተዳከመ መገኘቱን ተከትሎ ከንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነት ተባረዋል።
ይህን ተከትሎም የፖሊሲ ምርምር ተቋም ምክትል ዳይሬክተርነታቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት አቶ በረከት ስምኦን ለሕወሃት መዳከምና በሀገሪቱ ለቀጠለው ቀውስ በሌላኛው የህወሃት ቡድን ተጠያቂ ሲደርጉ ቆይተዋል።
አሁን በአቶ በረከት ላይ የሙስና ምርመራ የከፈተውም ይህው ቡድን እንደሆነም መረዳት ተችሏል።

በዚህም አቶ በረከት በቤተሰቦቻቸውና በሌሎች ግለሰቦች ስም የሚያንቀሳቅሷቸው ተቋማት ተለይተው እንደታወቁ ምርመራ ተጀምሯል።
ጄ ኤ ኤፍ ቢ ቢ በተባለ ኩባንያ ስም የተገነባውና ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘው ባለ 11 ፎቁ ደብል ትሪ ሆቴል ቅድሚያ ትኩረት ውስጥ መግባቱ ተመልክቷል።
ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የተገነባውና 106 መኝታ ክፍሎች ያሉት ይህ ሆቴል በባለቤትነት የተመዘገበው አቶ ተካ አስፋው በተባለ ግለሰብና በቤተሰባቸው እንደሆነም ታውቋል።

ሆቴሉ 70 በመቶ በአቶ ተካ አስፋው እንዲሁም 30 በመቶ በባለቤታቸው በወይዘሮ ፍቅረማርያም በላይ መያዙንና በሰነዶች መመዝገቡን ምንጮቹ ይገልጻሉ።
ምርመራው በግለሰቦቹ የሃብት ምንጭና በአቶ በረከት ስምኦን ግንኙነት ዙሪያ የሚያተኩር እንደሆነም ከመረጃው ለማወቅ ተችሏል።
የሆቴሉ ባለቤት ሆነው የተመዘገቡት አቶ ተካ አስፋው ረዳት አቃቢ ህግ ሆነው በህግ ሙያ ውስጥ የቆዩ መሆናቸው ታውቋል።
በሼህ መሀመድ አላሙዲን ኩባንያዎች ውስጥ አሁን በህግ አማካሪነት እየሰሩ መሆናቸው የተነገረው አቶ ተካ አስፋው፣ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር ያላቸው ግንኙነት በሼህ መሀመድ አላሙዲን አማካኝነት እንደሆነም የምርመራውን ፍንጮች መሰረት ያደረጉት የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ከደብል ትሪ ሆቴል በተጨማሪ በባለቤታቸው ስም አለ የተባለውን ማተሚያ ቤት ጨምሮ በሌሎች በዘረፋ ተገነቡ በተባሉ ድርጅቶቻቸው ላይ መርመራው እንደሚቀጥልም መረዳት ተችሏል።

በሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ውስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ አሁን ባለበት በእነ አቶ ስብሃት የበላይነት ከቀጠለና ሰራዊቱንም ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ከቻሉ በሌሎች የብአዴን መሪዎች እንዲሁም በኦህዴድ መሪዎች በእነ አቶ አባዱላ ገመዳ ላይ ተመሳሳይ ሁኔታዎች እንደሚቀጥሉ የቅርብ ምንጮቹ ይገልጻሉ።
በአለም አቀፉ ሂልተን ሆቴል መለያ የሚታወቀውና በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የተገነባው ሆቴል ከ6 ወራት በኋላ በሰኔ ወር ስራ ለማስጀመር መርሃ ግብር የተያዘ ቢሆንም በአቶ በረከት ላይ የተጀመረው ምርመራ በሆቴሉ ስራ መጀመር ላይ ምን እንደሚያስከትል ግን የታወቀ ነገር የለም

1 COMMENT

  1. Dear Betemariam,
    c/o Satenaw.
    The answer to your question is that Haile, the international celebrity, has a voice in disproportion to his body size. He is recognized world-wide. He is now lending the weight of his voice to the shaken Tigray Front. The idea is to create the perception that what is happening in the country is not the result of repression followed by civil unrest but the work of anarchists and terrorists trying to destabilize a stable and fast growing economy! Haile is concerned about his business. This is his way of showing gratitude to a regime that he thinks made him what he is, including appointing him president of Ethiopian Athletics Federation. Interestingly, Haile did exactly the same thing following Tigay Front stealing elections 2005, 2010. In fact, he publicly presented the jersey he broke world record in to Meles Zenawi. In both cases, Haile had little consideration for suffering Ethiopians, some of whom were shot killed for no reason than for protesting Tigray Front repression.

  2. Please write it in Amharic, a language that he understands much better, so that he can get the message with out any ambiguity.

    ሓይለ እውነት የሮጠው ለኢትዮጵያ ሲል ነው? እንደኔ ክትትል ከሆነ እሱ የሮጠው ገንዘብን ለማግኘት ዋና ዓላማ በማድረግ ነው:: ባንዲራ ለሱ የማሸነፍ (byproduct or positive side effect) ነበር:: ለ አገኛቸው ኦሎምፒክ ጎልድ ሚዳልስ ስለሺ ስህን ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው መታወቅ አለበት:: ለእኛ ያ ወያኔ ትግሬ የረጋገጠው የወደቀው ባንዲራ መውለብለብ ሲታሰበን ለሱ ግን ገንዘብ ማግኛ ቢዝነስ ነበር:: ይሄንን አንርሳ! እስቲ እነ ታላላቆቹ ወደር የለሽዎቹ አበበ ቢቂላ: ማሞ ወልዴ እና ምሩፅ ይፍጠር የሮጡበት የኢትዮጵያነት ስሜት ለመሆኑ ሓይለ ያውቀዋል?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.