የህወሃት ኢምባሲ ባልደረቦች በደቡብ አፍሪካዊቷ መሐል መዲና ጆሃንስበርግ የዉርደት ሸማቸዉን ተከናነቡ! — ልዑል አለሜ

24/02/2010

በስደት የሚኖሩ የእናት ሐገር ፍቅር የበላቸዉና የወገን ስቃይ የሚያንገበግባቸዉ ኢትዮጵያዊያን የህወሃት ባለስልጣንናትን ወይም ካድሬዎች ባገኙበት አጋጣሚ ሁሉ በማዉገዝ የግፍ ነራቸዉን  በመግለጥና ለአለም በማሳየት በሐገር ዉስጥ ለሚንገላቱት ዜጎቻቸዉ አለታነታቸዉን በማሳየት የጀግንነት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።

ትናንት ከቀኑ 7 ሰሃት አካባቢ ህወሃት የወከላቸዉ ካድርዎች ከፕሪቶሪያ በመነሳት የኢትዮጵያዊያኑ መኖሪያና መነገጃ ወደሆነችዉ  ጆሓንስበርግ ከተማ መሐል ጂፒ መነገድ ላይ ተገኙ ያሽከረክሩዋት የነበረችዉን እጅግ ዉድ ፍርቹን ካሚዮን ፓርክ ካደረጉ ወዲህ ፓን አፍሪካ ወደሚባል ህንጻ በመግባት ኢናይ ከሚባል የምግብ አዳራሽ ዉስጥ ምግብ አዘዉ ይምነሰነሱ ጀመር።

ፓርክ ካደረጉበት ስፍራ አንስቶ ሲከታተሉ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ተጠራርተዉ ይጠባበቋቸዉ ጀመር ካድሬዎቹ ተመግበዉ እንዳበቁ ሂሳባቸዉን ከፍለዉ ሲወጡ ያልጠበቁት ዱብ እዳ ተከሰቱ ኢትዮጵያዊያኑ ተሰባስበዉ ነበር.. ወደ እነርሱም ተጠግተዉ….. ረጋ ባለ መንፈስ

” እናንተ እዚህ ምን ታደርጋላችሁ ከላኳችሁ ወንበዴዎች ሸሽተን ጥገኝነት ተሰጥቶን በምንኖርበት ስፍራ ስለምን መጣችሁ…. እኛ እንደናንተ አይደለንም እዚህ ያሻንን ማድረግ እንደምንችል ታዉቃላችሁ አታሳስቱን ሁለተኛ ወደዚህ እንዳትመጡ ”

ይሏቸዋል ካድሬዎቹ እግራቸዉ እየተምታታ ወዳቆሙት መኪና በመጣደፍ ይገባሉ ከፓርኪንጉ ወጥተዉ መንገድ ሲጀምሩ ግን ሌሎች ኢትዮጵይዊያን በመመልከታቸዉ መሯሯጥ ተጀመረ በፍጥነት ሲያመልጥ የነበርዉ ፎርቹን ጥቂት ብቻ ነበር የተጓዘዉ በድንገት  ጩህት… በለዉ በለዉ ነፍሰ ገዳይ ነዉ… ጩህት… የህዝብ ጩህት ልክ በምድረ በዳ እንደጮኽዉ እንደ አቤል ደም ቃኤላዊያን ላይ ጩኽት… በለዉ….. የመኪናዉ መስታወት እርግፍ ኳ….ዃኳኳ . . . .

እስከ መቼ ነዉ እነርሱ እንደሮጡ እንደሸሹ እንደተሸማቀቁ በደረሱበት ሁሉ ተዋርደዉ አንገታቸዉን ደፍተዉ እስከ መቼ ይሆን የሚኖሩት? ለምን? ከወገኖቻቸዉ ጋር አይታረቁም ለምን ?  የአዉሬዉ ደም የነካዉ ሁሉ ተለይቶ እንደሚታወቅ በደሙም ልክ ዋጋዉን እንደሚቀበል ለምን አያስተዉሉም ?

ለነገሩ እንዳያስተዉሉ ቀድመዉ እጃቸዉን በደም ነክረዋል አይምሯቸዉንም በደም በተጨማለቀ ብእራቸዉ ደም በጥተዉበት አቅልመዉታል፡ ልባቸዉንም በጥቁር ከሰል በመሰለ ባቄመና በረጋ ደም አጥልተዉታል፡ ነፍሳቸዉ ቀድማ ሄዳለች በዚያ በሄደችበት እሳት ይበላታል፤ ነፍስ ይማር እንዳይባሉም ቀድመዉ ሞተዋል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.