የፌዴሬሽኑ አመራሮች ስብሰባ በታሸገ የውሀ ላስቲክ ውርወራ ተበተነ!

– የአቶ አበበ በስታዲየው የፊት መከላከያ በአዳራሹም ሊያስፈልግ ነው!

«ፊፋ ለፕሬዝዳንታዊውና ስራ አስፈጻሚ ምርጫ
ዕውቅና አልሰጥም ማለቱን ተከትሎ ስራ አስፈጻሚው ዛሬ ያደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ድብድብ
ተከስቶበታል።
የፀቡ መነሻ ደግሞ የፊፋ ዋና ጸሐፊና አቶ ጁነዲን ተደጋጋሚ ጊዜ መወያየታቸው ነው። አንደኛው ስራ አስፈጻሚ አበበ ገላጋይ ፊፋ ያገደው አንተ ነግረሃቸው ነው የሚል አቋም ከማራመዳቸውም በላይ አቶ ጁነዲን ላይ የታሸገ ውሃ መወርወራቸው ታውቋል።
አስገራሚ በነበረው ስብሰባና ረብሻ ሰራተኞቹ ተደናግጠው ቢሮውን ለቅቀው የወጡ ሲሆን በሮቹ በጥበቃዎቹ ተዘግተው እንደነበር ታውቋል።አቶ ጁነዲን ብዙ ጊዜ በአቶ አበበ ጥላ ውስጥ ናቸው ተብለው የሚታሙ ሲሆን አፈንግጠው መውጣታቸውና ወሳኙ አለቃ እንደሆኑ ጉባኤው እንደሚካሄድ ምርጫው ግን እንደሚራዘም መወሰናቸው መራዘሙን ለማይፈልጉት አቶ አበበ ብስጭት ማስከተሉ ታውቋል።

የኡጋንዳ ፓርላማን በኮረጀው ስብሰባ ኢንጂነር ቾልና አቶ አሊሚራም መጣላታቸው ታውቋል። አቶ ዮሴፍ፣አቶ ዘሪሁን፣አቶ ተክለወይኒና ዶ/ር ነስረዲን ግልግል ኮሚቴ ሆነው አምሽተዋል።ካፍ እንጂ ፊፋ አያገባውም ያሉ አመራሮች መኖራቸውም ግርምትን ፈጥሯል»

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.