ኦነግን ከዘር ማጥፋት ወንጀሉ ነፃ ለማውጣት ‘የኦ ኤም ኤን’ ተንኮል እንዳይበቃ የኛዎቹም ተጨመሩበት – ጌታቸው ረዳ

ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ

ኢትዮጵያዊያን በተለይ ኣማራዎቹ እስከመቸ ድረስ በእንዝህላልነት እንደዚህ ያለ የተካነ አሳሳች፤እርቃኑ የወጣ አጭበርባሪ የኦነግ ፕሮፓጋንዳዎች ተሎ ነቅቶበት ሊጥለው እንደሚችል እኔ ልገምት አልችልም። ተቃራኒ አፍራሽ ፕሮፐጋንዳ ካልተሰነዘረ በቀር ተሎ ሊነቃ የሚችል ኣይመስለኝም። ምክንያቱም ላብራራ። የበደኖ እስከ ቡኖ በደሌሊታይ የሚገባው በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም” Must Watch! OMN Documentary Film | From Bedeno to Buno Bedele

የሚል ኦነጎችና “የኦነግ ችግኝ” የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫዎች ያሰራጩት ቅጥፈት የተሞላበት እውነትን የሚክድ፤መንፈሳዊና፤ሰብአዊነት ግበረገብ የጎደለው፤ “የዜና ኢንተግሪቲ” (ሃለፊነት) ያልተከተለ፤ እንዲህ ያለ ‘ታላቅ- ሴራ’ (ኣሻጥር) “የኢትዮጵያ የመገናኛ መደብሮች” የሚባሉ በብዙዎቹ /ዋና ዋና በሚበሉት ድረገፆች ተለጥፎ የአማራውን ጭንቅላት ሰልቦ ለማሳሳት የሴራው ተባባሪ ሆነው መቀጠላቸው ዛሬም አማራም ሆነ ሌሎች ዜጎች /’በዳውድ ኢብሳና በሌንጮና በጃራ… በመሳሰሉ የተመራው ኦነግና እስላማዊ ኦነግ የተባሉት ድርጅት መሪዎች በነበሩበት ወቅት “አማራን ያስፈጁ ነብሰገዳዮች” ወንጀልና ሴራ ይነቃሉ ብየ አልገምትም።

በጠንቃቄ በየድረገፆች ስመለከት አንዳንዶቹ ይህ አጭበርባሪ ቪዲዮ የለጠፉት ድረገፆች ሳጠናቸው “አማራዎች” አንዳሉዋቸው አስገራሚ ከሚያደርገው አንዱ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ሊገርማችሁ የሚገባው። ሁለት አስገራሚ ነገሮችን ልጥቀስ። (1ኛ)- የፊልሙ ርዕስ << የበደኖ እስከ ቡኖ በደሌ፤ ግን ለምን? >>  የሚል ርዕስ ብቻ ነው በፊሉሙ ላይ የሚነበበው ርዕስ። ኢትዮጵያዊያን ተቃወሚ ድረገፆች ነን የሚሉ ግን ከፕሮፓሀጋንዳ ፈልሳፊዎቹ በለጥ ብለው ሁኔታውን በማጋነን አማራውንና ሌላውነ ዜጋ ለማሞኘት ሲሉ <<የበደኖ እስከ ቡኖ በደሌሊታይ የሚገባው በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም”>> ሲሉ መለጠፋቸው አንዳይበቃ ርዕሱን አሳምረው ለሕዝብ አቅርበውለታል።  ለምን?

 

(2ኛው) አስገራሚው ደግሞ ፤- በቪዲየው የተጠቀሱት የዓይን ምስክሮች ተብየው ‘አንዱ’ የወያኔ አገልጋይ የነበረ (ልዩ ወታደር) “አማርኛ ሲናገር ‘ኦሮምኛ’ የሚመስል ልሳን/አክሰንት” ያለው ምስክር ተብየው ከቁም ነገር ሳትቆጥሩት ወደ ጎን ትታችሁ፤-  ሌሎቹ ምስክሮች ተብየዎች ስትመለከቱ፤ ለምሳሌ እስራኤል ውስጥ ኦባንግ ሜቶ ቁጭ ብሎ በሚታይበት ካንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ተደርጎ ስለ ኦነግ በበደኔ ወንጀል ያለመሳተፉ የተናጋሪዎቹ ጥብቅና ስትመለከቱ የሚገርም ነው። እነዚህ “ሁለቱ” አማራዎች ናቸው ብየ እገምታለሁ (ካልተሳሳትኩኝ)፤ (አንዱ የስብሰባው መሪ እና አንዷ ደግሞ ከተሰበሰቡት አድማጭ ተንስታ የኦነግ ኦሮሞ ሳይሆን በደኖ ውስጥ የወያኔ ትግሬ ነው አማራን በማጥፋት ወንጀል የተካፉለው ያሉትን ስታደምጡ “ከሚግርም” በላይም “የሚገርምም” ነው። ሁለቱንም (ወያኔ/ኦፕዲኦ እና ኦነግ) መክሰስ እንዴት ዳገት እንደሆነባቸወ ለኔ አስገራሚ ነው።

 

እነዚህ በጥንቃቄ የተመረጡ ክሊፖች (የሰዎች ንግግር ማስረጃ) የሚናገሩትን ስታደምጡ ለምሳሌ (የታማኝ በየነን ምስክርነትንም  ጨምሮ) የሚገርም ቅንብር ነው። የታማኝን ሙግት ስናጤነው፤- የካሜራው እውነታ እኔም ሌሎቻችሁም እንዳያችሁት የበደኖ ዕልቂት የሚያሳየው ቪዲዮ (ከታች በግድያው ከተረፉ ሴት ምስክርንትም ወደ ታች እንደማቀርበው) አማራዎች ከነነብሳቸውም ሆኑ ተገድለው ወደ ቁንድፍቱ ሲጣሉ ሳይሆን የሚያሳየው፤‘የበሰበሰ ሬሳን ከገደል በመጫኛ ወደ ላይ ሲወጣ’ ብቻ ነው የሚታየው!

 

ታማኝና የኦ ኤም ኤን’ ጋዜጠኛው ግን እየነገሩን ያለው፤ ወያኔ ሆን ብሎ እዛ ቆሞ ሰዎች ሲጣሉ በካሜራ ሲቀርጽ ነበር ይላሉ። ታማኝ እንዲህ ይላል፤ “….ገደል ላይ ሲጣሉ እኮ እነ አቶ መለስ ስልጣን ላይ ሆነው በዲዮ እየቀረጹ ያሳዩን ነው!” ትላንት ያሳዩን ግን እንሱ የሚፈልጉትን ብቻ ነው ያሳዩን” ይላል።  እርግጥ ቀርጸው ሊሆኑ ይችላሉ፤ ግን እኔ ያየሁት ሬሳ ሲወጣ እንጂ ሲገፈተሩ የሚያሳይ የተቀረጸ ፊልም አላየሁም (እስካሁን ድረስ- አለ ከተባለ ታማኝም ሌሎቹም በድጋሚ ያሳዩን! – ግን ውሸት ነው!!!)። እንደሚሉን ቢሆን ኖሮ “ኦነጎች ወይንም ወያኔዎች በካሜራው ውስጥ ሬሳ ሲገፈትሩ እናይ ነበር።ግን አላየንም። ሲወጣ እንጂ ሲገፈተር አላየንም። ታማኝ ሲናገር  ሬሳዎች ሲገፈተሩ “ወያኔዎች” ካሜራ ይዘው ሲቀርጹ ልክ እዛው ቦታ እንደነበር ነው ዓይነት ሆኖ ነው የሚሞግተው። 5 ትግሬዎችም ወደ ገደሉ መጨመራቸው ከታች  እንደምንመለከተው ምስክሮች በግልጽ ያስመሰገቡት ምስክርነት ነግረውናል። *ትግሬዎች ነን አትግደሉን ቢሉዋቸው ወያኔዎች ቢያንስ ያስሯቸው ነበር እንጂ አይገድሏቸውም ነበር- ግን ኦነግ ስለሆነ ገድሎ ወርውሮአቸው  ሗላ ትግሬዎች መሆናቸው ሲያውቅ መዘዝ እንዳያስከትልበት ሲል ከገደሉ ወዲያውኑ እንዲወጡ አድረጎአቸዋል።

 

(ከወደታች የምንመለከታቸው ሴት ምስክር በሰፊው የምንመለከተው ቢሆንም) የታማኝ መከራከያ ግን ታማኝ ስላቀረባቸው ሚስታቸው ወደ ገደል የተጣሉት አባወራ በእምባ የታጀበ በመለስ ላይ የመረረ እሮሮ ሲያስሰሙ አስደምጦናል። ያ ግን አጠቃላይ ክስና ምሬት ነው። መለስ ይህንን ያውቃል፤ ያኔ አይቶ ቢዘረጋቸውስ ምን ነበረበት!? ሲሉ “ወንጀለኞቹን ያኔውኑ ይዞ መረሸንና አደጋውን ማስቆም ነበረበት” ነው የሳቸው እሮሮ። ስለሆነም ‘መለስ ነው እያደረገን ያለው፤ ለዚህ ውርደት ሞት የዳረገን’ ሲሉ ስርዐቱን መክሰሳቸው እና ተጠያቂ ማድረጋቸው እንጂ “ኦነግን” ነፃ ማድረጋቸው አይደለም። ልክ ኦነግ በወንጀሉ አልተካፈለም ብለው እንደተናገሩ አድርጎ የተቆረጠ የቪዲዮ ክሊፕ ማቅረብ “ኢንተግሪቲ” የሌለው ወገንተኛ ነት ነው። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ማቅረብና ሰው ከጋዜጠኛው ያደረጉት ያልተነካካ፤ያልተቆራረጠ ግንዛቤ እንድያገኝ ነበር- እውነት የተከተለ ሙሉ የመከራከያ ዘገባ ቢሆን ኖሮ። ለነገሩ ሙሉውን የሰውየው ቃለ መየጠይቅ በጽሑፍ ድሮ ይጠቅማል ብየ አስቀምጬው ነበር የት እንዳደረግኩት ግን አላወቅኩም።

 

እነኚህ ኦነግ ሳይሆን ወያኔ ነው በወንጀሉ የተሳተፈው የሚሉ ምስክርነታቸውን ያስደመጡን ለነዚህ ሰዎች የምለው ነገር ካለ ‘ምርምር አላደረጉም፤ ወይም የሚቀርቡት ዘገባዎች አልተመለከቷቸውም ፤ወይንም ድፍን የወያኔ ጥላቻ ስላላቸው በወያኔ ብቻ አትኩረዋል። ወይንም የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሰንቀዋል። ያም ሆነ ዘረኞችን፤ወንጀለኞችን ማንም ይሁን ማን – አማራ፤ኦሮሞ፤ትግሬ፤ሶማሊ…..ሳንል በሰው ግድያ የተካፈለ ሰው “እኩል” ካልከሰስነው፤ ካላጋለጥነው፤ ለይተን አንዱን ብቻ ስለጠላን ሌላው ይቆይ ተብሎ በይደር የምንሰራቸው የሞኝት ና ያልበሰለ ስራ ወገንተኛነት ነው። “ኢነትግሪቲ” (“ስለ እውንት መቆም”)ን ረግጠናልና እኛም “በዘረኞች” ጭቃ ውስጥ ተለውሰናል ማለት ነው። ስለሆነም እንዲህ ያለ ኦነጋዊ ፕሮፓጋንዳ አማራዎች ነቅተው ካልመከቱት “በስም መቻቻልና አብሮነት” እየተመካኘ አማራው ራሱን ወደ ማወቅ የደረሰበት መድረክ በሚጓዝበት በአሁኑ በወቅታዊ ጉዞው ላይ እያለ በቀላሉ ሊነጠቅ/ሊዳከም/ሊዘጋ/ሊደናቀፍ/ሊሞኝ ይችላል። መጀመሪያ የወንጀሉን ፈጻሚዎች ለይቶ ማወቅ የመጀመሪያው “(ሀ)” ራስን ማዳንና ጠላትን ማወቅ፤ (ለ)ከዚያ ወንጀለኞችን ወደ ሕግ ማቅረብ ነው። የተቀረው እንደየሁኔታው አስፈላጊነት በቅደም ተከትል ትጓዛላችሁ። ከገዳዮቻችሁ ጋር የምትጓዙ ከሆነ፤ ወይንም ፕሮፓጋንዳቸውን የምታሰራጩ ከሆነ፤- “ቢላዋው” አሁንም ወደ እናንተው አቅንቶ እንዳለ መገንዘብ አለባችሁ። በወንጀልና በግድያ የተቀረፁ (ክሪሚናል ማይንድ) ሰዎች ወደ መላእክትነት ሊለወጡ ነው ብሎ በጊዜአዊ የመደለያ ‘ሆሆታና ያልለየለት ጓዳዊነትና አንድነት”  ተደልሎ መላእክት ሆነዋል ብሎ መጠበቅ ከብትነት ነው። አንድ ጊዜ ልትሞኙ በቅታችኋል  ሁለተኛ ጊዜ ብትሞኙ ግን ሕዝብን ወደ ሌላ ዙር አደጋ ከጣለችሁት እንናተም ተጠያቂዎች ናችሁ።

 

ሊታይ የሚገባው እየተባለ ኦነግን ነፃ ለማውጣት የሚደረግ ሴራ ለኔ “የወንጀል ተባባሪነት ነው”። በሰው ልጆች ፤በአማራዎች ደም ማሾፍ ነው። የበደኖ እስከ ቡኖ በደሌሊታይ የሚገባው በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም” የሚለው  የተጠቀሱት ቦታዎች የበደኖን እልቂት አሁን የተደረገው ከቡና በደሌ ጋር እያመሳሰሉ የሚሰነዘሩ ንጽጽሮች፤ የእልቂት መጠን አንድ ሰውም ቢሆን ክቡር ደም ቢሆንም፤ ማሳነስ የማይገበና የደምና የወጀል ጉዳይ ቢሆንም “በበደኖ እና በመሳሰሉት የተፈጸሙ እጅግ ዘግናኝ የአማራዎችን እልቂት” ወያኔ በኦሮሞዎች ላይ የፈጸመው ወንጀል ጋር ማነፃጸር የአዘጋግብ ፈርጁ ምን ለማለት እንደሆነ አልገባኝም።

 

ለአማራ ሞትና ደም ከተቆረቆረ ‘የፊልሙ ዘጋቢ ቡድን’ በኦኖጎችና በእስላማዊ ኦሮሞ ነፃ አውጪዎች በአማራዎች ላይ የተፈጸሙት ዘግናኝ ወንጀል ለምን ሊዘግበው አልቻለም? መልሱን እንጠብቃለን። እሺ (ኦፒዲኦ የተባለው ሌላው ጸረ አማራ የኦነግ ህቡእ ድርጅት መንካት አልፈለጉምና ወደ ጎን አንተወው ላሁኑ) ወያኔ ብቻ በአማራ ላይ  ያደረገው ወንጀል ነው ብለው ነግረውናል። ወያኔን መወንጀል የሚከብድ ክስና ምስጢር አይደለም። ወያኔ ሌላ ቀርቶ ‘ባዶ እጁ ደብተር ብቻ’ የያዘ ተማሪን ሁሉ የማይምር ጥይት የሚያዘንብ አገር የሚያውቀውን ደም የጠማው የወያኔ ታጣቂ ብቻ ተቆናጥጦ የኦነግን ወንጀል መደባበቅ አያስኬድም።

 

“ኦ ኤን ኤም” ከተባለ አክራሪ ጸረ አማራና፤ ጸረ ምኒሊክ፤ ጸረ ቴዲ አፍሮ፤ጸረ ኢትዮጵያ የዜና መደብር ኦነግን ከወንጀሉ ነፃ ለማውጣት የሚያደርገው ትግል አዲስ አይደለም። ይህ የዜና ማሰራጫ ድርጅት በማን እንደሚካሄድ እናውቃለን። ስለሆነም የሚጠበቅ ፕሮፓጋንዳ ነው።

 

ኦነጎች መዋሸት በተለያዩ ሰዎችና መደብሮች ስም እየቀያየሩ መምጣት አዲስ አይደለም።  ካሁን በፊትም ዘሐበሻ ድረገጽ ላይ ሁሌም የሚጽፍ የድሮ ኦነግ አባል የነበረ “አፈንዲ ሙጡቂ” የተባለ አንዴ ወዲያ አንዴ ወዲህ የሚል በኔ አገላለጽ “እስታዊ ኦነግ”፤ “ወተር” በሚባለው ቦታ የተገደሉት 230ዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው። ሲል ዋሽቶ ዘግቧል (ምንጭ፦ደግሞ በሞረሽ ወገኔ ድርጅት የተጻፈ ምጽአተ ዐማራ መጽሐፍ ተዘግቧል)። እኔ የሚገርምኝ ኦሮሞ ሆኖ የኦሮሞን ህጻናት ጎሮሮ በካራ የሚያርድም ሆነ ኦሮሞ ሆኖ ኦሮሞ ነብሰጡር የሆነችን የሚቀድ ኦሮሞ ሆኖ፤ ኦሮሞ የሆነችን ሴት ጡቷዋን ቆርጦ ጉረሺ የሚል ኦሮሞ አይቼም ሰምቼም አላውቅም።  ስለሆነም የአሁኑ ኦነጎችም ሆኑ ነበር (ኤክስ) ኦነጎች ድርጅታቸውን አጋልጠው ይሰጣሉ ተብሎ አይገመትም (ልክ እንደ ወያኔ ነበርና (ኤክስ) አባል ወያኔዎች ድርጅታቸው ወያኔን ማጋለጥ እንደማይፈልጉ)። ስለሆነም ከነዚህ የሚጠበቅ ነው። የሚገርመው ግን አሁንም ካለፈው ሙግታችን ተምረው ይሆናል ብለን ስንጠብቅ ዛሬም ‘ኢትዮጵያ ሚዲያ ነን” የሚሉ እንዲህ ያለ የውሸት ፊልም ‘”መታየት” ያለበት እያሉ ለጥፈው ሕዝብን ሲያሳስቱ ማየት ዛሬም አግራሞቴ ቀጥሏል። መታየት ያለበት ካሉም ለምን መታየት እንዳለበት ቢነግሩን ለተመልካች መንገድ ይከፍት ነበር፡ ግን አላደረጉም። መታየት አለበት ሲሉ “ኦነግን ከወንጀሉ ንጾህ ነው” ውሸትንና ውሸታሞችን “አድንቁ፤አሞግሱ ነው” እያሉን ያሉ።

 

‘ኦ ኤን ኤም’ ሆነ የዓይን ምስክሮች ወይንም ጠቃሚ ምስክሮች ተብለው በጥንቃቄ የተቀረጹ በፊልሙ ያደመጥናቸው ሰዎች/ምስክሮች/ ‘ኦነግ’ ስለ በደኖም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የዘር ማጥፋት ወንጀልና ግድያ አላከናወነም፤ የዘር ፍጅት፤ጸረ አማራ፤ጸረ ኢትዮጵያ ቅስቀሳ አላስተማረም፤ በፖሊሲው አልጻፈም ብሎ የሚል ዕውር ነውና ዓይኑን በዘረኛነት/በኦሮሞኛነት/ ሕሊናውን የተሸፈነ ሰው ብቻ ነው። ማድረግ የምንችለው፤ እንደ ሰው እንዲያስብ ጤና እንዲያገኝ” እንጸልይለታለን።  ኦነግ በተጠቀሰው በደኖ እና ሌላም ቦታ ውስጥ የዘር ፍጅት ያከናውን እንደነበር የዶ/ር አሰፋን ቃለ መጠይቅና ጥናት፤ የሙሉቀን ተስፋው (መጽሐፍና ቃለ መጠይቅ)፤የአባ ኒቀዲሞስ አስፋው የተባሉ ወጣት ካህን፤ሌሎችም ምስክሮች….እንዲሁም ‘ሞረሽ’ <<ምጽአተ ዐማራ> የተባለው ባለ 665 ገጽ መጽሐፍ የዘገበው ሰንድ ውስጥ ለናሙና ላቅርብና ምስክሮችም ሆኑ ፤ለኦነግ የቆሙት የኦነግ ‘ችግኞች’ና ሚዲያዎቻቸው ይህ ወንጀል ተመልከቱና እንደ ጤነኛ ሰው አስቡ። ኦነግ በበደኖ የፈጸመው ወንጀል!

 

ምፅአተ ዐማራ መጽሐፍ እንዲህ ይላል በገጽ 327 ላይ

 

<<“…………በዚያ ገደል ለመወርወር ዓይኗ ተሸፍኖ ልትወረወር ስትል በምታውቀው የኦነግ ሠራዊትና ስሟ አንዳይጠቀስ የፈለገች ሴት አንዲህ ትላለች።

እንቁፍቱ” ማለት በአማርኛ ሲተረጎም የማይሞላ ማለት ነው። አማራ የሆነውን በሙሉ እጃችን በገመድ እየታሰረ ዓይናችን በሻሽ እየተሸፈነ ወደ ገደሉ ጫፍ እንቀርባለን። ከገደሉ ከመጣላችን በፊት ከእጃችን፤ከጆሮአችን፤ከጣታችን እና አንገታችን ላይ ወርቅና ብር ይነሳል። ጣት ያለ ወርቅ በቀላሉ የማይወልቅ ከሆነ ጣት ይቆረጣል።ለምሳሌ የኔ የጆሮ ወርቅ ሲወልቅ ወደታች ስበውት ሙሉው ተቀዷል። ወደ መጀመሪያው አካባቢ በጥይት እየሞቱ ወደ ገደሉ ይሸኙ ነበር። በኋላ ግን ለዚህ ሁሉ ሰው ለምን ጥይት እንጨርሳለን በማለት፤ በሜንጫ አንገት አንገታቸው እየበጠሱ ወደ ገደሉ ተጣሉ። ከነ ሕይወታቸው የተወረወሩት በጣም ብዙ ናቸው። አራት ያህል ትግሬዎች በስሕተት ተጥለው አስከሬናቸው ወዲያውኑ ገብተው አወጥተዋቸዋል። እኔ በደኖ አካባቢ ጎረቤታችን የነበረ ከገዳዮች አንዱ የሆነ የኦነግ ሠራዊት አባል አይቶኝ እህቴ ናት ብሎ ነው ያተረፈኝ።

 

ከተገደለው ሰው ብዛት የተነሳ፤ አካባቢው በመጥፎ ሽታ ተሞላ። በዚህም ምክንያት ከአንድ ሳምንት በኋላ ኬሚካል እየተረጨ ብዙ ሬሳ ወጣ። ነገር ግን ከገደሉ መጨረሻ ድረስ ሂደው ስለላወጡት፤በእኔ እምነት አሁንም ድረስ ያልወጣ የብዙ ሰዎች አጥንት ቅሬት ይኖራል ባይ ነኝ። አንዲት ወይዘሮ አልማዝ የሚባሉ የአቶ አበበ ምትኬ ባለቤት ወደ ገደል ሲወሰዱ መሄድ ሳይችሉ ቀሩ። ወይዘሮ አልማዝ ሰውነታቸው ወፍራምና በጣም የሚያምሩ መልከመለካም ሴት ነበሩ። በውፍረታቸው ምክንያት ወደ መጣያቸው መድረስ ባለመቻላቸው መንገድ ላይ <አፋን አጅዋ አማራ! (ግም አፍ አማራ)> እያሉ ሆድ እቃቸውን በሳንጃ ዘረገፉት። ሳይሞቱ እያጣጣሩ እያለ ጎትተው ወስደው ወደ እንቁፍቱ ጨመሯቸው። ባለቤታቸው ድሬዳዋ ኖረው ከዓመት በፊት በንዴት ሕይታቸው አልፏል።>>  በማለት አስረድታለች።>> (ምፅአተ ዐማራ ገጽ 327)

 

ወያኔ እንጂ ኦነግ አማራን አልገደለም እያሉ ሲቦተልኩ የነበሩ ምስክሮችም ሆኑ ስለ እውነት ይናገራሉ ተብለው የሚጠበቅባቸው እነ ታማኝ በየነም “የተገደሉ ሰዎች ሲገደሉም ሆነ ወደ ገደል ሲገፈተሩ ወያኔ በቪዲዮ ይቀርጽ ነበር” ብሎ የሚለን የታማኝ ምጉት ስናነጻጽር “ለመገደል ታጭተው ከገደል አፋፍ ላይ በታምር የተረፉ ምስክሮች የሚነግሩን ምስክርነት ለየብቻ ነው።” ኦነግ በበደኖ የዘር ፍጅት ተጠየቂ ነው። ስለሆነም በተቃዋሚነት ስም የምታላግጡ ስለ እውነት ቆመናል የምትሉን “ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ድረገፆች ሁሉ” ኦነግን ከወንጀሉ ነፃ ለማውጣት ኦነግ በሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ላይ እያቆነጃጃችሁ “መታየት ያለበት” የምትሉት የማጃጃያ ፕሮፓጋንዳ  ሰነድ  የሴራ ተካፋዮችና አደማቂ አስራጮች ከመሆን እንድትታቀቡ የዘወትር ማሳሰቢያየ ዛሬም ይድረሳችሁ። ማንም ይሁን ማንም የሰው ደም ያፈሰሰ መጠይቅና መወቀስ አለበት። “ኢንተገሪቲ” (ለእውነት ቃል ኪዳን ዘብ መቆም) የግድ ይለናል!

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.