የመንግስትን ስልጣን ለመረከብ ዝግጁነት አለ ወይ?   (ከሙሉቀን ገበየው)

ህወሃት (ወያኔ)  ከግንቦት 1983 ጀምሮ፡ የኢትዮጲያን ህዝብ  በመሳርያ ሃይል ቀፍድዶ  በአምባገነን አስተዳድር ስር ጥሎታል።  በተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴው እየተጠቀመ አስከፊ አገዛዙን ቀጥሎል። በተለይ በታዋቂው የቅጥፈት ሴራው የ “ከፋፍለህ ግዛው” ዘዴው እየተጠቀመ ሲከፋፍለን፣ በተለይ ትላልቅ ጎሳዎችን እርስ በርሳችን በጠላትንት ስሜት እይሰበከ፣ እያጣላና እያጋጨ ለሶስት አስርት አመታት ቆይቷል። ጎሳን፣ ቋንቋን እንዲሁም ሃይማኖትን የሰቆቃ መግዣ መሳርያ አድርጎቸዋል።

ብዙሓኑ  ኢትዮጲያውያን በአሁኑ ግዜ ይህንን የወያኔን የማጭበርበርያ አስከፊ የአገዛዙ ማራዘሚያ ዘዴው እንጂ የ ዲሞክራቲክ መፍቴ አለመሆናቸውን  ጠንቅቆ አውቆል። በእጁ ጠፍጠፎ የሰራቸውና ያደራጃቸው ኢሕአዲግ በሚል ግንባር የሰበሰባቸው የሃሰት የጎሳ ድርጅቶች፤ አሁን እንደ ቀድሞው  በእውርነት ና በታማኝ  ተላላኪነት ላለማገልገለ ደፈር ማለት ጀመርዋል። ወያኔም እንድ ልቡ የሚቆጣጠርበት ሀይልና ጉልበቱ እየደከመበት መጥቶአል።

ብዙሃኑን በወህኒ ቤት እስር ማጎሩ፣ በወፌላላ ማሰቃየቱ፣ በአስከፊ ጭፍጭፋ መግደሉ፣ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ማድረጉ፣ ማፈናቀሉና ንብረት መዝረፉ፣ መንግስታዊ የሽበር ድርጊቱ፤ ሆድ የባሰውን ህዝብ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያቆመው አልቻለም። የተቃውሞ ሰልፉ ከክልል ወደ ከልል እንደሳት እየተቀጣጠለ ቀጥሏል እንጂ አልተዳፈነም። አምባገነኑ አገዛዝ የፈልገውን ቢቅባጥርና ምክንያት ቢስጥም ‘የኪራይ ሰብሳብነት፣ የአድሎ ስራ ነው፣ የኤርትራ እጅ አለበት’ እያለ ቢጮህም ጆሮ አላገኘም። እንደ ቀድሞው ማንንም ሊያሞኝ አልቻልም። የታፈነ ህዝብ አመጿል።

ወያኔ በሚጠቀምበት ጠንካራው የማማያና የማስፈራሪያ ዘዴውን ጨምሮና የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ድከመት ታክሎበት፤ የተቃዋሚው ሃይል ሲከፋፍል፣ ሲዳከም፣ ቅስሙ ሲሳበር ተስተወሏል። በአንድ ድምጽ ለመጮህና ወያኔን የሚተካ ሃይል ለማደርግ  የተለያዩ በዘውግና በብሄሪዊንት የተደራጁትን የፖለቲካ ሃይሎች ለማሰባሰብ ብዙ ሙከራና ድካም ቢደረገም  በቀላሉ የሚሰባብሩና የተባበሩ ድምጽ ሳይሆኑ ቀርቷል።

ህውያት(ወያኔ) በዚህም ሆነ በዚያ መንገድ ስልጣኑን ቢያጣ፤ ጸረ-ወያኔ ኢትዮጵያውያን የመንግስትን ስልጣን ተረክቦ ሀገርን ለማስተዳድር ተዘጋጀትዋል ወይ?

ጥርስ ያለው፣ ጠንካራ፣ የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ  ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዲሞክራቲክ አስተዳድር የሚያሻገር የተዘጋጀ ሃይል አለ ወይ?

ሰላምና ማረጋግትንስ ማን ያስከብራል?

ባላመዘጋጀታችን የተነሳ የሚከስት ፖለቲካው የሃይል ክፈተትስ አይኖርምን?

ሁሉን በህግ ጥላ ስር፣ ያለ አድሎ ፣ ዲሞክራቲክ አስተዳድር ለመትከል የተዘጋጀ ኢትዮጲያውያን ስብስብ አለን?

እንደ ቀድሞዋ ዩጎዝላቪያና ሶቭየት ህብረት ላለመፍራረስ የሚጥብቅን ዝግጁ ሃይል አለን?

በጎሳና ሃይማኖት ሰበብ ወያኔ ባስቀመጠው መርዙ ምክንያት ሊነሳ የሚችለውን ግጭት የሚከላከልና የሚያስቆም ዝግጁነት አለ ወይ?

የኢትዪጲያን ድንበር ሉአላዊነት ከውጭ ጠላቶችዋ የሚጥብቅ የተዘጋጀ ሃይል አለን?

በአገራችን ከዳር አስከ ዳር የተነሳው የህዝብ ቁጣ የወያኔን  ስሩን መንግሎ  ለመንቀል  ባለበት ግዜ  እንዚህ አንገብጋቢ  ጥያቄውች በብዙሃኑ የለወጥ ፈላጊ መልካም ዜጎች  እርፈት የሚነሱ ሆነው ተገኝተዋል።

በስልጣን ላይ ያሉት የአገዛዙ ቁንጮዎች በህሊናቸው ሰበአዊነትና ኢትዮጲያዊነት የሚሰማቸው ቢሆኑ ለሚወዱት ቤተሰባቸውን ልጆቻቸው ሲሉ፤  አለም አቀፋዊ ጉባኤ ጠርተው፣ ሁሉንም ተቀዋሚ ድርጅትች፣ የሰራተኞች ማህበርን፤ የሲቭክ ድርጅቶችን፤ ታዋቂ የአገር ሙሁራናን ሽማግሌዎችን ያሳተፈ ጉባኤ አድርገው ሰላሚዊ የስልጣን ሽግግርን ማድርግ ይገባቸዋል።

ወያኔዎች ግን በተፈጥሮቸውና እስካሁን ባከናወኑት   ፖለቲካዊ ድርጊታቸውና ያለመቻቻል ልምዶች   ይህን ያደርጋሉ ብሉ መመኝት የዋህነት ቢሆንም በ ፖለቲካ ሳይንስ አይቻልም ማለት ግን አይቻልም ።

ኢትዮጲያውያን ግን እልቂት ለሌለበት ለውጥ ተዘጋጀትናል ወይ? በብዙሃኑ ዘንድ በወጉ ያለመዝጋጀትቻን ፍርሃት ያለ ሲሁን ይህም ጹህፍ ኢትዮጲያውያን ና የተለያዩ የተቃውሞ የ ፖለቲካ ድርጅቶች  ግዜ ሳያጠፉ  በቶሎ መዘጋጅት እንዳለባቸው ጥሪ ያደርጋል። አብዛኛው ህዝብ  የወያኔ አስከፊ አገዛዝ አንድ ቀንም እንኳን እንዳይቀጥል ይመኛልና።

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.