የእንግሊዞቹ ነገር – መስቀሉ አየለ

አንድ ውስጥ አዋቂ እንዳለው በራሱ የውስጥ ቅራኔ ፈንድቶ ሊሞት አንድ ሃሙስ የቀረውን የወያኔ መንግስት እድሜውን ለማራዘም እንግሊዞቹ ከፍተኛ እክስፐርቲዝ ያሉበት አንድ ከፍተኛ ልኡክ በመጭው አርብ ወደ አዲስ አበባ ሊልኩ ነው። ልኡኩ ከራሱ የውጥ ጉዳይ ሚንስቴር የተሰጠው መመሪያ እያስገመገመ የመጣውን አመጽ አቅጣጫ በማስቀየር ግዜያዊ ፋታ ለማግኘት ይረዳ ዘንድ እግር ተወርች የተያዘውን የሃይለማርያም፣ ካቢኔት አፍርሶ እንደነሱ አባባል ከአማራ ውጭ የሆነ ጠቅላይ ሚንስቴር ጭምር ተክቶ ማዋቀርን ይጨምራል።

እንደመረጃው ዝርዝር በነርሱ እምነት መሰረቱን በኤርትራ ያደረገውና በአማራው ሃይላንድ አካባቢ እየተፈጠረ ያለው በነፍጥ የታገዘ እንቅስቃሴ አንድ ግዜ በሙሉ ሃይሉ ፈንድቶ አገሪቱን ለማዳረስ የግዜ ጉዳይ በመሆኑ አማራው ዳግም ወደ ስልጣን እንዳይመጣ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን ባዮች ናቸው። ይኽ እንግዲህ ትናንት በሳውዝ አፍሪካ በናሚቢያ፣ በዚምባቡየ የነጻነት ትግል ብሎም በአጠቃላይ በፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ላይ አገራችን ላደረገችው አስተዋጽዖ ጥርስ ውስጥ ገብተናልና ምንም እንኩዋን አፍ አውጥተው ባይናገሩትም እንግሊዞቹ ዛሬም ድረስ የበቀል ሂሳባቸውን አወራርደው አልጨረሱልንም ማለት ነው። አዎ፤ አንድ ማንበብና መጻፍ የማይችል እንግሊዝ የያዘውን ቁራጭ ማስታወሻ እንድታነብለት ሊጠይቕህ ሲመጣ አፍ አውጥቶ “ማንበብና መጻፍ ስለማልችል ተባበረኝ” አይልህም፤ “እባክህን መነጸሬን እረስቸ መጥቸ ነውና ይህችን ነገር ምን እንደምትል ንገረኝ” እንደሚል አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ አይቸ ነበረ።

ሌላው አንዱ ሹክሹክታ ከጀርባ ያሰሉት ነገር ዝርዝሩ ባይታወቅም የቴሬዛ ሜይ አስተዳደር ለመጀመሪያ ግዜ “አንዳርጋቸው ጽጌን ከመጭው የፈረንጆች ገና በዓል በፊት አስፈትተን ወደ ዩኬ ለመመለስ..” በሚል ከወያኔ ጋር ድርድር መጀመሩ ሁኔታዎች ያሳያሉ፤ ምን ያህል እንደሚገፉበት ግን ወቅት የሚገልጠው ጉዳይ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.