የምንጃር ተቃውሞ – ልዑል ዓለሜ

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መብራት በተከታታይ ለ13 ቀናት ጠፍቶ በመቄየቱ ምክንያት በዛሬዉ እለት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡ በወጣቶችና በአረርቲ ከተማ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በዋናነት ሲቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎች
1. ለመብራት ችግር ዘለቄታዊ መፍትሄ ይሰጠን
2. የዘይትና የስኳር ሰልፍ ይቅር
3. ፍትሃዊ የሆነ የግብር አከፋፈል ስርዓት ይዘርጋ
4. ለኢንዱስትሪ ፓርክ የእርሻ መሬት ለሰጡ አርሶ አደሮች የተከፈለዉ ካሳ በቂ እና ፍትሃዊ አይደለም
5. ለወጣቶች የሚፈጠረዉ የስራ እድል በቂ አይደለም፤ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የተመደበዉ ተዘዋዋሪ ፈንድ ወጣቶችን ተጠቃሚ አድረጎ አላየንም እና ሌሎችም ጥያቄዎች ተነስተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.