የጣልያን ፍርድ ቤት ለግራዚያኒ ሃውልት ያቆሙትን እና መሬት ያቀረቡትን ከንቲባ በእስራት እና በገንዘብ ቀጣ

እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2012 ከሮም ከተማ በስተ ምሥራቅ ሃምሳ ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምትገኘው የአፊሌ ከተማ“አባትነት” እና “ክብር” የሚሉ መጠሪያዎች ተሰጥተውት በ160 ሺህ ዶላር ወጪ ለግራዚያኒ ሃውልት መቆሙን ተከትሎ የጣሊያን ፍርድ ቤት ድርጊቱ ተገቢ አይደለም በሚል ይህን ስራ የሰሩትን ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ መቅጣቱ ነው የተገለጸው፡፡

የመታሰቢያ ሃውልቱን እንዲቆም አድርገዋል የተባሉትን የከተማይቱን ከንቲባ ኤርኮሌ ቪሪ ፍርድ ቤቱ ስምንት ወር እስራት እና የ120 ዩሮ ቅጣት ሲጣልባቸው ይህንን ሃውልት እንዲቆም አድርገዋል የተባሉት ሁለት የምክር ቤት አባላት ጊያምፔሮ ፍሮሶኒ እና ሎሬንዞ ፔፐሮን እያንዳንዳቸው የስድስት-የስድስት ወራት እስር እና የ80 ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ተከሳሾቹ የሰሩት ጥፋት ትልቅ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ በማንኛውም የመንግስት ስራ ውስጥ ገብተው እንዳይሰሩ እገዳ የተጣለባቸው ሲሆን በጣሊያን የፋሽስት ተቃዋሚ ለሆነው የጣሊያን ድርጅት በምጻረ ቃሉ /ኤ ኤም ፒ አይ/ 8ሺ ዩሮ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ካርቤሎ ክሬሼኒ የተባሉ ጣሊያናዊ ውሳኔው እልባት እንዲያገኝ እና አጥፊዎቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በማድረግ በኩል ትልቅ ጥረት በማድረግ የኢትዮጵያ ባለውለታ መሆናቸውን አስመስክረዋል ሲል “ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ” የተባለው የኢትዮጵያውያን ማሕበር ገልጧል፡:

በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ አሥር ሺዎች ኢትዮጵያውያን በመርዝ ጋዝ የተገደሉበትን ጨምሮ በኢትዮጵያና በሊቢያ በፋሺስት ወረራ ዘመን በፈጸመው በርካታ የጦር ወንጀሎች ተጠያቂ ለሆነው ለሮዶልፎ ግራዚያኒ የመታሰቢያ ሃውልት መቆሙን እና የመዝናኛ ሥፍራ ለክብሩ መሰየሙን በመቃወም ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ለቆየው ድርጅት ተከሳሾቹ 1800 ዩሮ እንዲከፍሉ ውሳኔ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል፡፡

ውሳኔውን ተከትሎ “ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ” የተባለው የኢትዮጵያውያን ማሕበር የጣሊያን ፍርድ ቤት እንዲህ አይነት ውሳኔዎችን ማስተላለፉ ለእኛ እንደ ትልቅ ድል እንቆጥረዋለን ብሏል፡፡
ከሌሎች መሠረታቸው ጣልያን ከሆኑ ቡድኖች ጋር ላለፉት አምስት ዓመታት ወገኖች አንዱ ነው። ይባላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.