የትግሬዎች ሃያልነት የሚሰብኩ ሁለት የፋሺስት ርዕዮት አቀንቃኞች በአሜሪካ ድምፅ የትግርኛ ራዲዮ ክፍለጊዜ ያደረጉት ውይይት በሚመለከት

ጌታቸው ረዳ የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ

ጌታቸው ረዳ

ውድ  ኢትዮጵዊያን አንባቢዎቼ ሰላምታ አስቀድማለሁ። ሁለት ነገሮች ለማለት እፈልጋለሁ። ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት እዚህ ላይ ግልጽ እንዲሆን የምፈልገው ‘ትግሬዎች’ የሚል ቃል ወያኔዎች “ተጋሩ” በማለት የሚጠቀሙበት ቃል ሲሆን። ልጠቀም የመረጥኩበት ምክንያት፤ በሁለት ምክንያቶች መነሻ ሲሆን፤ አንደኛው ምክንያት በይደር አቆይቼ ሁለተኛው ምክንያት ብቻ እጠቅሳለሁ። ‘ተጋሩ’ የሚለው ቃል ትግርኛ ተናጋሪው የትግራይ ተወላጆችን እንጂ ትግራይ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ሰዎች/ተወላጆች/ ማለትም ‘ኩናማዎች፤ዓፋሮች፤ አገዎች፤ሳሆች እና አማራዎችን ስለማይገልጽ፤ ተጋሩ የሚለው ትግርኛ ተናጋሪው ነገድ ብቻ ነው ብየ ስለምከራከር፤ በዚህ ያዙልኝ። ምክንያቶችን ከታች እገልጻለሁ።

 

ከ1887 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በሦስት ደረጃዎች ዕድገት ያለፈው የትግራዋይነት ፋሺዝም እስከ ‘ዳግማይ ወያኔ’ ድረስ በዋናነት የድርጀቱ መዘውር መሪዎችና አፈቀላጤዎች ሆነው በብርቱ አክራሪ ብሄረተኛ ስሜት የተጓዙት፤ በክፍለሃገሩ ውስጥ የሚኖሩ ኩናማዎች፤ዓፋሮች፤ አገዎች፤ሳሆዎች እና አማራዎች ሳይሆኑ፤ “ትግርኛ ተናጋሪው ክፍል” (ተጋሩ) ስለሆነ “ትግሬዎች” የሚል ቃል ስጠቀም ትግርኛ ተናጋሪው ነገድ ብቻ ለማመላከት እንደሆነ እንደ ነጥብ ይያዝልኝ።

 

ወደ መነጋገሪያ ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት ፤ ስለ አዲሱ መጽሐፌ አንብባችሁ ደስታችሁን ለመግለጽ በርካታ፤ እጅግ በርካታ የሆነ የደስታ መግለጫ ጥሪዎች ከመላው ዓለም (ከኢትዮጵያም ጭምር) በስልክና በኢመይል እየደወላችሁና እየጻፋችሁ ደስታችሁን የገለጻችሁልኝ እና ላበረታታችሁኝ ወንድሞችና እህቶች ሁሉ እጅግ እጅግ አመሰግናለሁ። እዚህ ላይ ተዛብኩት አንድ ነገር (እንደ ዘወትሩ)፤ የመጽሐፍ ማንበብ ፍላጎት ያሳደሩት “ተማሩ” የምንላቸው “ደደቦቹ ምሁራን” ሳይሆኑ ሁሌም ስለ አጋራቸው ጉዳይ ለማወቅ የሚንገበገቡት የኔ ብጤ ተራ ዜጎች መሆናቸውን ስታዘብ፤ ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ እንደገለጻቸው “የኢትዮጵያ ምሁራን በሁለት አመት ሩብ (አንድ ሦስተኛ) የመጽሐፍ ገጽ እንኳ የማንበብ ፍላጎት የላቸውም” ሲል ‘ደደብነታቸውን’ የገለጸልንን እውን ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ድሮም ጦር ሜዴ እና ፍልሚያ የሚዋደቀው ተራው የኔ ብጤ ዜጋ ነውና ከ “/ፔቲው/ቡርዡዋው/ም” ሆነ ከተቃዋሚው ትግሬ ማሕበረሰብ የማንበብና የመመራመር ችሎታቸው ብዙም አይጠበቅም። ለዚህ ነው ‘ስለ ማያነቡ ደደቦች ሆነው አገሪቱን ለመከራ ያጋለጥዋት”። ስለ እነሱ ያካተተ በመጽሐፉ ውስጥ ስላለ እዛው መመልከት ነው። አንዳንድ ምሁራንን እዚህ ላይ አያጠቃልልም (ለማወቅ ያሳያችሁት ፍላጎት ምስጋና ይድረሳችሁ)።

የትግራይ ምጣኔ ሃብት ግንባታ የተጀመረው ለወሎ እና ለትግራይ ረሃብተኞች የተለገሰው ዕርዳታ ገንዘብ በመላዋ ኢትዮጵያ የተዘረፈ የባንክ እና የመንግሥት ንብረት መሆኑን በዚች ስዕል ልጀምር። ይህች ላንድሮቨር መኪና እና ቀጥሎ የምትታየው “ቡልደዘር/ግሪደር” ወያኔ በመንግሥትና በሕዝብ ገንዘብና ንብርት ዝርፊያ ሲሰማራ ‘ሀ’ ብሎ ዘረፋው የጀመረው በነዚህ ሁለት ንብረቶች ነው። ላንድሮቨሯ የመጀመሪያ ስትሆን አክሱም ውስጥ ባንክ ሲዘርፉ የተገለገሉበት መኪና ስትሆን ቀጥላ የምትታየው ቡልደዘር ደግሞ ፤ ሽሬ አውራጃ ውስጥ ታሃዱ በመባል የሚታወቀው መንግሥታዊ …የእርሻ ልማት ድርጅት እዛው ድርጅት በሚሰሩ በውስጥ አባሎቻቸው ጥናትና ትብብር የተዘረፈች የመጀመሪያ ቡልደዘር ነች። አጼ ዮሐንስ ከግብጾች የማረኩትን መድፍ “አክሱም ቤተክርስትያን መግቢያው በር ላይ ለታሪክ ማሳያ ተቀምጦ እንደሚታይ ሁሉ ዛሬ ድግሞ ወያኔዎች በሚገርም ሁኔታ ከአገሪቱ የተዘረፉ መንግሥታዊ ንብረቶች ልክ እንደ ጣሊያን ንብረት ተቆጥረው መቀሌ ውስጥ በሚዝየም ተቀምጠዋል። የዝርፍያ ታሪክና የአገሪቱ ንብረት  በሚዚየም ማስቀመጣቸው አስገራሚ ከሚያደርገው አሳፋሪውና ባዕዳዊ የሆነ የወያኔዎች ‘ልዩ’ ባሕሪይ ተመለክተሉልኝ። ከዚያ የሆነውን ስለምታውቁት-ላናንተ  ልተው።

 

አሁን ወደ ርዕሱ እናምራ፡

ሦስት ነጥቦችን እተቻለሁ። ጸሃፊው የነካካቸው ስለ አማራ፤ ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እና ስለ ልደቱ አያሌው (በመጠኑ) እንመለከታለን።  ዛሬ-ዛሬ፤ አብዛኛዎቻችሁ አንባቢዎቼ የትግሬዎች ዓብዮት (ሪቮሊሽን/ወያኔ) የፋሺስት እንቅስቃሴ ዓብዮት እንደሆነ በመጠኑም ቢሆን ቀስ በቀስ እየገባችሁ መምጣቱ እንደሆነ እገምታለሁ። ስለሆነም የትግሬ አክራሪ ርዕዮት ፋሺስት ነው፤ የውስጥ ቅኝ አገዛዝ ስርዓት (ኢንተርናል ኮሎኒ/የውስጥ ሄጀመኒ/) ነው ስንል እንደ ድሮ የሚያቧርቅብን ሰው እምብዛም ነው። ለዚህ ርዕዮት ታላቅ ጥናት ያካሄደውና የፋሺዝም ምንነት እያስተማረን ያለው ታላቁ ምሁር የአአምሮ ሐኪም የምን ጊዜም  ወዳጄ ዶ/አሰፋ ነጋሽ (ሆላንድ) ሳላመሰግነው አላልፍም። ስለሆነም ስለ ፋሺዝም ምንነት ከማየታችን በፊት ወደ ርዕሱ እንግባ።

 

ተዳፍኖ እየፏከተ ወቅት ሲጠብቅ የነበረው ከጥንት ጀምሮ በረዢም አዝጋሚ ሂደት የተጓዘው የትግራይ ቀኝ አክራሪ ብሔረተኛ ስሜት እየተጠናከረ የተከናነበበት “ሂጃብ” (ሽፋኑን) በመጣል ፋሺስት ወደ መሆን ተሸጋግሮ አሁን ወዳለው የተጋሩ ፋሺስታዊ መንግሥት ለመመሥረት በቅቷል። በነጋሲነትና በአንጋሽነት ፤በአይበገሬና በምርጥ ሕዝብነት ስሜት የተቃኘው ይህ  የትግሬ ቀኝ አክራሪ  ብሔረታዊ የፋሺስቶች ንቅናቄ አሁን ወደ አደገበት ደረጃ ለመድረስ ሦስት መሰረታዊ የሆኑ የአካባቢ አክራሪ ንቅናቄዎችን ማለፍ ነበረበት።

 

 

በመጽሐፌ ውስጥ እንደገለጽኩት ከዮሃንስ ሞት በኋላ (1ኛው ንቅናቄ) በእነ አሉላ አባነጋ (ባስታጠቅናቸው ሸዋዎች አንገዛም የበላይነት ስሜት) እንዲሁም በዮሐንስ ዘሮች ማጉረምረም (ለምሳሌ ራስ መንገሻና የአፄ ዮሐንስ እህት…) የተመራው እንዲሁም በወቅቱ በነበሩ አክራሪ የትግራይ ብሔረተኞች ልሂቃን (ደብተራ ፍስሐጊዮርጊስ አብየዝጊ….በኋላም በመጠኑም ቢሆን በዓድዋዊው ገብረህይወት ባይከዳኝ) እና አክራሪ የገጠር ወጣቶች ንቅናቄ (ዮሃንስ ቢሞት እኛ ልጆቹ አልሞትንም በሚል ቅኝት የተቃኙ) በቀኝ አክራሪዎች የተረገዘው አንቁላል፦

 

(‘2ኛው ንቅናቄ’) ከላይ የተጠቀሰው የራሶችና የትግራይ እመቤቶች በሸዋዎች ሥልጣን ተነጠቅን “ቁዛሜ” ((በግጥሞችና አሳዛኝ/አስለቃሽ/ የተነሳው “ተደፈረኩ” ስሜት የሚያንጸባርቁ በኡንጉርጉሮ የታጀቡ ኡሮሮዎች) የተጀመረው ንቅናቄ ቀስ በቀስ አድጎ-አድጎ ወደ እነ ብላታ ሃይለማርያም ረዳ ዘመን ተሻግሮ ‘’የትግራይ ትግርኚን’ ቅኝት እንደ ‘ሁለተኛ’ አማራጭ ዕደል ይዞ፤ ከመአከላዊው የኢትዮጵያዊ መንግሥት በጠመንጃ ውጊያ የተፋለመው የቀዳማይ ወያነ እንቅስቃሴ ነው።

 

(‘3ኛው ንቅናቄ) በተጠቀሱ ሁለት አዝጋሚ ብሔረታዊ ትግራዋይነት አክራሪ ንቅናቄዎች የተጀመረው “ሥልጣንን ወደ ትግራይ የማስመለስ” እንቅስቃሴ ወደ ዳግማይ ወያኔ ተሸጋግሮ የተራዘመ የ17 አመት የጠመንጃ ፍልሚያ በማድረግ ለዘመናት የተቆዘመው የትግሬዎች ኡሮሮ በ1983 ዓ.ም ብሔረተኞቹ ያነጣጠሩት ግብ “የዮሃንስ ዙፋን ወደ ትግራይ የማስመለስ ግብ  ተሳክቷል። ሥልጣንን ወደ ትግራይ ያስመለሰው የፈረንጅ ትምህርት የቀሰመው ይህ ‘ዘመናዊው የመሳፍነቶች ቡድን’ ወደ ‘ጋሃድ የፋሺስት’ ስርዓት ሲሸጋገር በጣም በርካታ የሆኑ “ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመነጠል” የሚንቀሳቀሱ የትግራይ ቀኝ አክራሪ ፋሺስት ወጣት ምሁራንን በከፍተኛ ቁጥር በማደራጀት ‘ትግራይ ልጆቿን ሰውታ ለሌች ነገዶች መጠቀሚያ ሀኖለች’፡ የሚሉ የፋሺስት ግልገሎች ወደ መድረክ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ይህ ፋሺስታዊ ኡሮሮ ዛሬ ከራሳቸው ከወጣት የትግራይ ወጣት ቀኝ አክራሪ ብሔረተኞች ምሁራን  እናደምጣለን/እንወያይበታለን።

 

ከነዚህ ውስጥ በግምባር ቀደም የታወቀው ጸረ አማራ የሆነ ግለሰብ በየማሕበራዊ የመገናኛ ድረገጾች (ፌስ ቡክ፤ራዲዮን….)  የትግራይ (ፋሺዝም (ሱፕረማሲ/ዑቡይነት) ቅስቀሳ ከሚያሰራጭ፤ የዓባይ ትግራይ አቀንቃኝና ትግሬዎች ለሌሎች ጥቅም ስንል ተሰውተን አሁን ባሉት የወያኔ አመራር “ድክመት እና ቸልተኛነት” ትግራይ ተገቢውን ስፍራ (የትግሬ ምሁራን “ተገቢውን ሥፍራ” ሲተነትኑት ሥልጣን በትግሬዎች እጅ በላይነት መምራት ማለት ነው፡) ያለ መያዟ ብቻ ሳይሆን በልማት ከማንኛቸውም የአገሪቱ ነገዶች (ክልሎች) በመጨረሻ እርከን ስለምትገች፤ ትግሬን የበላይነቷን ለማስመለስ ሌላ እንቅስቃሴ ለመጀመር ያልተፈተሹ ደካማ ጎነቻችን እንደገና መፈተሽ አለበት በማለት የሚከራከረው እንደርታዊው “ዶክተር የማነ ዘጽኣት” ነው። ይህ ወጣት ትክክለኛ ስሙ ስለሚደብቅ ከላይ በገለጽኩት ስም (በዘጸአት) ይታወቃል።

 

ይህ ወጣት የሚሰብከው እና ከአንደበቱ የሚወጣው አስፈሪ የፋሺስት ቅስቀሳና ቁዘማ  እንዲሁም “ትግሬዎች የሁሉም ጌቶችና ታምር ሰሪዎች ናቸው” ከሚሉት እጅግ ካስገረሙኝ ዑቡያን የእንደርታ ትግሬዎች አንዱ ነው። ይህ ወጣት በሙያው መቀሌ ውስጥ “ዓይደር የሕክምና ተቋም”  የሕክምና ሌክቸረር/መምህር እና ሐኪም ነው። ወያኔ ወደ መቀሌ ከገባ ወዲህ አጅግ በርካታ አክራሪዎች የተፈለፈሉት ከእንደርታ መሆኑን ስመለከት እጅግ አስገራሚና አስፈሪ ሆኖ አግኝቼዋሉ። እነ ዘጸአት የመሳሰሉ እንደርታዎች/ተምቤኖች/ ራያዎች… የመጀመሪያ ሰለባ የሆነው አመለካካታቸው ብቻ ሳይሆን ‘ልሳናቸውም ጭምር’ ወደ አስማሪኖነትና (ኤርትራዊነትና) ‘አሽዓ’-ነት (አክሱም ሽረ ዓድዋ) ልሳንነት ለመለወጥ የሚያሳዩት አሳፋሪ {የበታችንት ስሜት} ከራስ ጋር ፍትግያ የሚያስገርም ቢሆንም፤ አሳዛኝ ነው።

 

ይህ በፋሺስት ርዕዮት የሰከረ የኢትዮጵያን ሕዝብ ወንድማዊና እህትማዊ አንድነት የሚበትን ጸረ አማራ እንደርታዊ ወጣት በየፌስቡኩ የሚነዛው ጥላቻ የማታወቁት ያላችሁ አይመስለኝም። ዘጽአት (ወዲ ዓበይቲ) በሚል ስም በማሕበራዊ ድረገጾች የሚታወቀው ይህ ፋሺስታዊ አቀንቃኝ ወጣት በአዲሱ መጽሐፌ ላይ በሰፊው ከተተነተኑት አንዱ ግለሰብ ስለሆነ እዛው ተመለክቱት። ይህ ግለሰብ እና  የእርሱን ዓላማ የሚጋራ ሌላ መረሳ ፀሐዬ የተባለው (ሙያው አልተገለጸም፤ ምናልባትም ዩኒቨርሲቲ መመህር ? ) ትግራይ ያበቀለቻቸው ወጣት ፋሺስቶች ከዘጸአት ጋር አብሮ “ቪኦኤ ትግርኛ” ከተባለው ተሞዳሟጅ ራዲዮ- ባቀረበላቸው መስተንግዶ ከመቀሌ በስልክ ያደረጉት ውይይት እንመልከት።

 

ራዲዮው ላይ ተጋብዘው “ፋሺስታዊ ቁዘማቸውን እንዲቆዝሙበት” የተሰጣቸው የማስቆዘሚያ ርዕስ በትግርኛ እንዲህ ይላል። ወደ አማርኛ እተረጉመዋለሁ።

 

ኢትዮጵያ ኣብ ዘየቛርጽ ፖለቲካዊን ታሪኻዊን ማዕበል ምዕባለን ለውጢን እያ ትርከብ። ኣብ ነዊሕን ዝተሓላለኸን መስርሕ ህዝቢ ትግራይ ዝወነኖ ጂኦፖለቲካዊን ታሪኻዊን መኣዝን መዘራረቢ ገይርናዮ ኣለና።”

 

“ኢትዮጵያ በማያቋርጥ ፖለቲካዊና ታሪካዊ የለውጥ ማዕበል ውስጥ ትገኛለች። በዚህ በተወሳሰበው ረዢምና አስቸጋሪ በሆነው ሂደት የትግራይ ሕዝብ በባለቤትነት የያዛቸው ጂኦ-ፖለቲካ እና ታሪካዊ መአዝኖች መነጋገሪያዎች እንዲሆኑ የመነጋገሪያ ርዕስ አድርገን ይዘን ቀርበናል።” በማለት አዘጋጁ ከላይ የተጠቀሱት ሁለት አክራሪ ብሔረተኞች እንግዶች አድሮጎአቸው በርዕሱ እተደጋገፉ እንዲወያዩ ጋብዞአቸዋል። በስልክ የተደረገው ውይት በዘጸአት ንግግር ይጀምራል። 

       

        ዘጽአት በትግርኛ እንዲህ ይላል።

       

ገለ ሓይልታት ተጋሩ ድምጾም ኣየስምዑን ዘለው ኢሎም ይነቕፉ ዘለው፣ ቃልሶም ብዘይካ ተሳትፎ ህዝቢ ትግራይ ከምዘይዕወት ስለዝፈለጡይብል ዘጸኣት። ተጋሩ በብዝሕና ውሑዳት /ማይኖሪቲ ሙዃንና አሚንና፤ ኣብ ውሽጢ ካልኦት ሚሊዮናት ሕዘብታት እንዳነበርና ናትና ‘ሮል- መንቴኢን” ክንገብር ክንቅጽል አንዳተዳ ደሊና “ብኢኮኖሚ ጎቢዝካ ሓይልካ” ሌለው “በትምህርቲ፤ኣብ ኣካዳሚ ወሰንቲ ዝኾኑ ሰባት ምፍጣር  ወሳናኢ እዩ።

 

ትርጉም ወደ አማርኛ፡

 

 << “አንዳንድ ሃይሎች ‘ትግሬዎች” ድምጻቸውን እያሰስሙ አይደለም በማለት የትግራይን ሕዝብ ሲወቅሱት ይደመጣሉ። ትግላቸው የትግራይ ሕዝብ ካልተሳተፈበት ለድል አንደማይበቃ ስለሚያውቁ ነው።” ‘ማይኖሪቲ እና ማጆሪቲ” የሚል ነገር እየመጣ ነው። የትግራይ የፖለቲካ ዕምብርት ናት። የትግራይ ሕዝብ ሚና እና ዕጣ ፈንታ ምንድ ነው ለሚለው ‘በሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ እየኖርን የትግራይ ሕዝብ በማይኖሪቲነታቸን ማወቅ እና “የምጣኔ ሃብት ጉልብቶ ተጠናክሮ መቆየት” ሲሆን፤ ሌላው ወሳኝ ደግሞ “በትምህርት፤አካዳሚ ወሳኝ የሆኑ ሰዎችን መፍጠር” ሲቻል ‘ማይኖሪቲነታችንን’ ወደ ሃያልነት “ሮል’ -ሜየነተይን’ ለማድረግ (ለመጠበቅ) የሚያስችሉ ወሳኝ ነገሮች በነዚህ ጠንክረን መስራት ነው። ’ሲል ዘጸአት የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለትግሬዎች ምንም ማድረግ እንደማይችል፤ የትግሬዎች ታምር ሰሪነትና ሃያልነት “የፋሺስቶች መለያ የሆነው እኛ ሃያላን እነሱ ደካሞች” የሚለውን ዶ/ር ‘ዘጻአት’ ከወያኔዎች  አስተምህሮ የቀሰመው ፋሺስታዊ ትምህርት ሲያንጸባርቅ  በምጣኔ ሃብት መጠናከር አዲስ የተማረ ሰው መፍጠር የትግሬዎችን ሃያልነትና “ሮል/አስተዋጽኦ” ‘ሜይነተይን” መጠበቅ ካልተቻለ፤ በሚሊዮኖች የሚኖሩባት ትልቅ አገር እየኖርክ ‘ጥቂት ሕዝብ’ (ማይኖሪቲ) ሆነህ መኖር “ጥቅምህን እና መብትህን ማስተበቅ አስቸጋሪ ነው። ትግሬዎች በኢኮኖሚ “ኢማፓወርድ” ሆነን ‘በሃብት የተገነባን’ መሆን አለብን።>>  ሲል አስተያየቱን ገልጿል።

 

ቀጥሎ የዘጸአት ትዕቢት የሚጋራውና የሚያጠናክረው “መረሳ ፀሃዮ” ደግሞ እንዲህ ይላል። በትግርኛ ላቅርብ ቆይቼ እተረጉመዋለሁ።

 

መረሳ ፀሃየ፦

 ብሓደ ወገን ሃገራዊ ሓላፍነት ተሰሚዕዎ፣ ልቢ ኣዕብዩ ንዓመታት ስምዒቱ ካብ ምግላጽ ተቖጢቡ ነይሩ። ብካልእ ወገን ኣብ ክልተ ስለስተ ዓመታት ብሕልፊ ኣብ መንእሰያት ናይ ምንቕቃሕ ተርእዮታት ተዓዚብና ኣለናይብል። (መረሳ ፀሃየ)

 

 

<< (የትግሬ ሕዝብ) ባንድ መልኩ ሓላፊነት ተሰምቶት፤ ልብ አድርጎ፤ ለበርካታ አመታት ስሜቱን አምቆ ከመግለጽ ተቆጥቦ ነበር። በቅርቡ በነዚህ ሁለት ሦስት አማታት ውስጥ ግን የትግሬ ወጣቶች የመነሳሳት ሁኔታዎች እየታዘብን ነው።”>>

 

ሲል የዘጸአትን ትምክህት በሌላ አገላለጽ በማጠናከር፤ የትግሬ ሕዝብ አምቆት የነበረው ‘ትዕግስትና ለባምነት” ከእንግዲህ ወዲህ የትግራይ ወጣቶች ግን ይህንን ትዕግስት መቀጠል እንደሌለበት በተጻራሪ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው እየነገረን ያለው፤ “መረሳ ፀሃየ”።

 

ትዕግስቱ እየገነፈለ የመጣው ምን ይሆን የሚሉ ጥያቄዎች ልታነሱ ትችላለችሁ። የትግሬ ፋሺስት ወጣቶች ለትዕግስታቸው መገንፈል ዘጸአት ሲያብራራ ምክንያቱን እንዲህ ይነግረናል።

 

ትግርኛውን እነሆ፤ ትርጉም ይከተላል።

 

‘ናይ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቅልውላው ንኹሉ ዘስክፍ’ዩ። እቲ ጸገም ካብ መዓልቲ ናብ መዓልቲ መልክዑ እናቀየረ እናገደ ህይወት ሰብን ንብረትን ይተፍእ ኣሎ፣ ናብ ዘይንወጾ ቅልውላው ንከይንኣቱ ኣብ ዘስግእ ኩነታት ኢና ንርከብ’።  ኣብ’ቲ ፖአቲክዊ ቅልውላው ብሓደ ወገን ቀደም ስለዝተሳዓርና ሕነና ክንፈዲ ባሃልቲ ብሕልፊ እቶም መራሕቲ ዕድመኦም እናደፍአ ስለዝርከብ ተጓዪና ስርዓት ኢትዮጵያ’ውን ተዳኺሙ ስለዘሎ ቀልጢፍና ነጽድፎ ዝብሉ ከምዝኾኑን፣ ከም ግብጺ ካብ ዝኣምሰሉ ናይ ወጻኢ ሓይልታት ዋላ’ውን ካብ ሰይጣን ይኹን ሓገዝ ረኺቦም ነዚ ስርዓት’ዚ ሰው ከብልዎ ይደልዩ’ዮም’ ። (ዘጸኣት)።

 

<< “አሁን በክስተት ላይ ያለው የኢትዮጵያ የመናጋት ውጥረት (ክራይሲስ) ሁላችንም የሚያሳስብ ሁኔታ ነው። ችግሩ ከቀን ወደ ቀን መልኩን እየቀየረ እየባሰ የሰው ህይወትና ንብረት በመብላት ላይ ይገኛል። ወደ እማንወጣው ደረጃ እንዳንገባ አስፈሪ ሁኔታ ላይ ነን ያለነው።”  በዚህ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ተዋናዮች የሆኑት  ክፍሎች፦ በትግሬዎች ስለተሸነፍን ብድራችን/ ቁጭታችን/  መመለስ አለብን ባዮች የሚሉ ሲሆኑ፤ ለዚህም አመች ሁኔታ ሆኖልናል የሚሉት፤ በተለይ ደግሞ መሪዎቹ (የወያኔ መሪዎች) ዕድሜአቸው እየገፋ ስለመጣ እና የኢትዮጵያ ሁኔታ ስለታደከመ እንደ ግብፅ እና የመሳሰሉ  የውጭ ሃይሎችም ሆነ ከሰይጣንም ቢሆን ዕርዳታ በማግኘት ፤ተሎ ተሯርጠን ስርዓቱን ወደ ገደል እንግፋው የሚሉ ናቸው።>> (ዘጻአት) ይላል።

 

ከባድ ሚዛን የያዘው ያለፈው የትግሬዎች ታሪክ ዛሬስ እቦታው ላይ ይገኛል?  ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ዶ/ር ዘጸአት ሲመልስ፤-

 

ትግርኛው እነሆ ትርጉም ይከተላል፤

 

“ትግራይ ብኹሉ መመዘኒ “ሚኒማም” ዝባሃል ነገር እውን ኣይረኸበትን። መንእሰይ ፎቖዶ ስደት ዓሳ ይበልዖሎ ፍርቁ ናይ በረኻ ኣራዊት ይበልዖ ኣሎ። ፋሕ ክንብል ኮይኑ ትግራዋይ ናይ ኩሉ ሕማቕ ምልክት እዩ ኮይኑ።ብናብራ ምንቁልቋል ይመርሕ አሎ። መራሕቲ ካብ ሎሚ ጽባሕ ልቢ ዶኾን ይገብሩ እንዳበልና ነይርና ግን አይገበሩን። መንእሰይ ትግራይ ከምቲ ኣብ ካልእ ከባቢ ዘሎ ፖለቲካዊ ንቕሓት ተፈጺሙሉ እዩ ንክንብል አጸጋሚ እዩ።  ካብ ሥልጣን ካብቲ ኢኮኖሚ ካብ ኩሉ ክወጽእ እዩ ተገይሩ። ጹቡቕነቱ ግን እዚ ህዝቢ እዚ ናይ 2ተ/ 3ሺህ ዓመታት ናይ ሥልጣነ ፤ናይ መንግሥትነት ሥልጣነ ባህሊ ዘለዎ ሕዝቢ እየ። መራሕቲ እንተሓነቑዎ፤ ዝሓሹ መራሕቲ ሰባት ናይ ምፍጣር ሽግግር ክፈጥር ይኽእል እዩ። ሕዚ ግን ንእሹተይ ደውታ ይራኣይ አሎ። ኮይኑ ግን ምንቅስቓስ ይራአይ አሎ ምዕባይ ጥራሕ እዩ ዘድልየና።” (ዘጸአት)

 

ትርጉም፡

<<  ትግራይ በማንኛውም መመዘኛ በፖለቲካም በመጣኔ ሓብትም “ሚኒማም” (በትንሹ እንኳ ይህ ነው የሚባል) የሚባል ነገር እንኳ አላገኘችም።የትግራይ ወጣት ወደ ስደት በማማምራት በባህር ሲጓዝ የዓሳ ነባሪ ሲሳይ ሆኖ በየሰሓራ በረሃ የአራዊት ሲሳይ እየሆነ ነው። ትግሬው የችግር ቀማሽ ‘ምሳሌ/ምልክት” መሰያ ሆኗል።በኑሮ ማሽቆልቆል በመጀመሪያው እርከን ላይ ይገኛል። መሪዎች ከዛሬ-ነገ ‘ልብ ገዝተው’ እየሆነው ያለው የትግራይ ሕዝብ ኑሮ የመጨረሻ ደረጃ መሆኑን አስተውለው ነቅተው ማስተካከያ ያደርጉ ይሀናል እያልን ኑሮናል። ሆኖም አላደረጉም። የትግሬ ወጣት በሌሎቹ አካባቢዎች እንደሚሰጠው የፖለቲካ ንቃት አልተደረገለትም። የትግራይ ሕዝብ ከሥልጣን፤ከፖለቲካ ከምጣኔ ሃብት እንዲገለል ተደርጓል (አድልዎ እየተፈጸመበት ነው)። መገንዘብ ያለብን ነገር፤ ይህ ሕዝብ የሁለትና ሦስት ሺሕ አመት የሥልጣኔ፤የመንግሥት፤የባሕልና ያስተዳዳር ልምድ ያለው ሕዝብ ስለሆነ መሪዎች እንቅፋት ቢሆኑትም የተሻለ የመሪነት ብቃት ያላቸው አዳዲስ መሪዎች የመፍጠር ችሎታው የተረጋገጠ ነው። ለጊዜው ግን ትንሽ የመቆም ሁኔታ ታይቷል። ቢሆንም አዲስ እንቅስቃሴ እየታየ ነው ያንን ማሳደግ ብቻ ነው የሚጠበቅብን። (ዘጸአት)>>

 

 

መራሳ ጸሃየ በበኩሉ እንዲህ ይላል። ትግርኛውን መጀመሪያ ትርጉም ይከተላል።

 

ኣብዘን ክልተ ሰለስተ ዓመታት እኮ ትግራይ መሰልና ኣይረኸብናን እንትንብል እኮ  እዚ ኣይባሃልን ነውሪ እዩ ኣይንጽበብ እንዶ ዝባሃል ሰፊሕ ኩነታት እዩ ነይሩ። ድኽመት ነይሩና እዩ ምኽንያቱም ‘ናይ ነዊሕ ጊዜ ኩናት አካይድካ ተዳኺምካ ናይ ምምጻእ ሕ ናብ ለምዓት ዓብይ ትኹረት ናይ ምሃብ እዩ ተገይሩ ነይሩ። በትኻልእ ወገን እንቶም ካልኦት አባላት ናይ ኢህወዴግን ካልኦት ናይ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሓይልታትን ትግራይ መስዋእት ገይሩ፤ዲሞክራሲያዊ አስተዋጽኦን መንግሥታዊ ሕገ መንግሥትን አምጺኡ እዩ ስለዚ አስተዋጽኦ ስለዝገበረ ተናአሰ -ተናኣሰ (ሕዝቢ ትግራይ) ‘ማተሪአላዊ’ ጥቕሚ ኣይርከብ አስተዋጽኦ ስለዝገበረ “አፍልጦ” ክርክብ እዩ ዝብል ዓብይ አምነት ስለዘዝነበረ ባዕልኻ ምግላጽ ‘ድልየታታኢካ ኣብ ምቕማጥን ምድርዳርን አስተዋጽኦ ኣይነበረናን”። ስለዚ እዚ እዩ ክሳታኻኸል ዝግቦኣኦ፤ ሕዚ’ውን ረፊዱ እዩ ዝብል አምንት የብልናን። ናይ (ኣፕርሲየሽን) ምስጋና አፍልጦ ስለዘይተውሃቦ፤ ናይ ዓብላላይን፤ጎባጣኢን ልዕልነት ዘለዎ ስለዝራአይ ዘሎጸ ድለየታትና ነጸርና፤ ከምተጋሩ መሰልና ክነኽብር ንባዕልትና እውን ክንካላኻል፤ን ናይ ትግራይ ጥቕምታት አውን ክንዳራደር ክንጅምር አለና። ኣብቶም ካልኦት ውድባት/ከባቢታት አንትንርኢ- ኣብቲ ጠንካራ-ጠንካራ ዝባሃል ናይ መንግሥቲን ውድባትን መሓውር ኣትዩ እቲ መንግሥቲ ዝሃቦ እናተጠቕመ  ነቲ ስርዓት መንግስቲ ነግ ነግ ዘብሎ ዘሎ ኩነታት ንርኢ። ኣብ ናይ ትግራይ ኩነታት እንተርኢና ግን፤ ፖሊታከዊ ምስልቻው ፤ኣብ ውሽጥን ደግን ኮይና እንታይ አፋላይ አለዎ ማለትን ናይ ትግራይ ጥቕሚ ኣብክንዲ ምኽባር ኣይንጽበብ እንዶ፤ አንዳበልና ስለዝጸናሕና ፤እዚታት ክንእርም ኣለና ዝብል እምነት ኣለኒ። (መረሳ ፀሃየ)

 

 

ወደ አማርኛ ትርጉም

 

<< በነዚህ ሁለት ሦስት አመታት እኮ ትግሬዎች መብታችን አላገኘንም ስንል ፤እባካችሁ ነውር ነው “አትጥበቡ” እየተባልን  መብት ተነፍጎን ኖረናል። የኛ ድክመት ነው። የረዢም ጉዞ ጦርነት ስላካሄድን ድካም ስላለ ትኩረታችን ወደ ልማት እናድርግ በሚል ትልቁ ትኩረት ወደ እዛው ነበር። እኛ ከዛው (ኩራኬውና ከሱታፌው) ተገልለን ሌሎቹ የኢሕአዴግ እና ከነሱ ውጭ የሆኑ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች መንግሥት በዘረጋላቸው ተጠቅመው ዋና ዋና በሚባሉት የስርዓቱ መዋቅሮች በመንሰራፋት ገብተው ተጠቅመው አሁን ሥርዓቱን እያናጉት እያየን ነው። የትግራይ ሕዝብ መስዋእት ከፍሎ ሕገ መንግሥት መሥርቶ፤ ዲመክራሲ አምጥቶልና እና ህሳቤ ይደረግለት ብለው ቢያንስ ‘ማተሪያለዊ’ (ቁሳዊ) ጥቅም ባይሰጡትም/ባያገኝም/ ‘ሪኮግንሽን’ ምስጋና ይቸረው ይሆናል በሚል እንደተቀሩት (ነገዶች) የመደራደር ፍላጎታችን አላሳየንም ነበር። ምስጋና ቀርቶብን አሁን “አፋኝ፤ቆራጭ፤ፈላጭ፤ እየተባለ በጮቋኝንት እና አንደ የበላይ ሆኖ እየታየ ነው። አህን ግን ጥቅማችን ማንም ስለማያስክብርብን ጥቅማችንን ለማስከበር መደራደር መጀመር አለብን። የትግራይ ሕዝብ ጥቅም ከማስከበር ይልቅ ፤ እባካችሁ አንጥበብ፤አክራሪዎች አንሁን እያልን ስናመነታ ስለነበር፤ እነኚህ አደናቃፊ አባባሎች ማስተካከል (ማስወገድና) እና መደራደር መጀመር አለበን፤ እላለሁ በበኩሌ ያለኝን አስተያየት። (መረሳ ጸሐየ)>>

 

እንናተ ተንታኞች በየፌስቡክም ሆነ በየድረገጾች እንድትወያዩባቸው በሚል ነው ትችቴን ብዙም ወደ ውስጥ እራሴ ሳልተነትን ተርጉሜ ያቀረብኩላችሁ። ሁለቱ የትግራይ ሰዎች የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ያደመጣችሁት ፍሬ ነገር፤ ሲጨመቅ አንዲህ የሚል ነው።

 

“ኢትዮጵያዊያኖች ያለ ትግሬዎች ምንም መሥራት አቅም የላቸውም”፤ ትግራይ አድራጊ ፈጣሪ፤ የፖለቲካ የሥልጣኔ እምብርት፤ ነጋሽ እና አንጋሽ፤ ትግሬዎች መስዋእት ሆኖው ለሌሎቹ ዲሞክራሲ አምጥተው፤ሌሎቹ በሕገ መንግሥቱ ገብተው ተጠቅመው ስርዓቱን ሲያናጉት ትግሬዎች ግን ዲሞክራሲም ሆነ በምጣኔ ሃብት አልተጠቀሙም። የትግራይ ሕዝብ የመከራዎች እና የድህነቶች ሁሉ ህይወት እያሳለፈ ከሌሎቹ ዜጎች በመጨረሻ እርከን ይኖራል። ስለሆነም የችግር፤ የመከራ፤ የድህነት መገለጫ ሆኖ ሌሎቹ ከሱ በተሻለ እየኖሩ ነው። ስለዚህም በምጣኔ ሃብት የበላይነት አግኝተን የተሻለ የተማረ ሰው ፈጥረን ራሳችንነ ገንብተን ሃያልነታችንን ማሳየት እና ራሳችንን መከላከል አለብን። “አንዳንድ ሃይሎች ‘ትግሬዎች” ድምጻቸውን እያሰስሙ አይደለም በማለት የትግራይን ሕዝብ ሲወቅሱት ይደመጣሉ። ትግላቸው የትግራይ ሕዝብ ካልተሳተፈበት ለድል እንደማይበቃ ስለሚያውቁ ነው።

 

 በማለት እነዚህ ሁለት ፋሺስት ወጣት የትግራይ ምሁራን ሂትለር ሲናገራቸው የነበረውን ቅስቀሳ ተመሳሳይነቱ ለማየት ይህንን ቪዲዮ ጋብዤአችለሁ። ትዕግስት አድርጋችሁ ስታደምጡት የሁለቱም ትግሬዎች ፋሺስታዊ ‘አልተጠቀምንም” እና “ሃያልነታችን እናስመልስ” “ጀርመን ለሌሎች ጠቀሜታ ስትውል የጀርመን ሕዝብ ግን ከድህነት ወለል በታች እየኖረ ነው፡  ቢሆንም ሌሎች ያለ ጀርምን ኣይኖሩም፤ ራሳቸውን ለውጥ ማምጣት አይችሉም፤ የምናገረው ቀልድ ይመስላቸዋል፤ ግን ውጤቱ እንድያዩት አደርጋለሁ፤ በምጣኔ ሃብትና በወታደራዊ በፖለቲካው “ኤምፓውርድ” ሆነን ሌሎቹን በመምራት ታምር እንሰራለን! …. የሚለው የሂትለር ተመሳሳይነቱን ይህ “ቀይ ክኒን” የሚባለው ከሂትለር የተወሰደ ንግግርና “ የአሜሪካ ሂትለር ደጋፊዎች” ያሰራጩት ቪዲዮ ነው። ደጋፊዎቹ ልክ እንደዚህ ያሉ የትግራይ ፋሺስት ወጣት ምሁራን “ወያነ’ ፋሺሰት ኣይደለም፤ ጨቋኝ አይደለም..ዲሞክራሲ አምጥቷል..” ሲሉ አንደሚከላከሉለት ሁሉ፤ የሂትለር ርዕዮትንና ጭካኔ የሚያወድሱ ፈደጋፊዎች በዩ-ቱብ የለጠፉት የሂትልር በራሱ ልሳን ሲናገር ነው በእንግሊዝኛ ሳብ ታይትል እየተጠቀሰ የምታደምጡት ጥቅሶቹ። “ቀይ ክኒን” ተመልከቱ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com (Ethiopian Semay)

 

The Ultimate Red Pill

https://youtu.be/jWHuFuuYHso

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.