ያልፋልን ስትቆጥሪ … – ሥርጉተ ሥላሴ

ሥርጉተ ሥላሴ 12.11.2017 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

„ድሀ፡ በለመነ፡ ጊዜ፡ አፉን፡ እስከ፡ ጆሮው፡ ድረስ፡ ይከፍታል፣ ጩኸቱም ፈጥኖ ወደ እግዚአብሄር ይደርሳል።

 መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፭“

 

ታሪኩ ቀርቶብሽ የዛሬን ብትኖሪ

ዘመንሽ ተሰብሮ ስታይ ቀን ስባሪ፤

በዘመናይ ግራር ያልፋልን ስትቆጥሪ

ምዕላት ጥሎሽ ሄደ መከራ ስ – ት – ድ – ሪ።

በዘመን ውስጥ መኖር ላንቺ መች ሆነና?

በዘመን ወስጥ ማለም ላንቺ ምን ሆነና?

ቁርሾ እያመረተ ያ ሥምሽ ገናና።

ቀንሽ ተቀዳዶ ስፌትን ሲማጸን፤

ዕለትሽም ነዶ – ፈጣሪን ሲለምን፤

ደግነት የት ይሂድ? ወዴትስ ይመንን? ? ?

ጎምዛዛው መከራሽ ግዞት አሳ

ቆምጣጣው አሳርሽ ጭቆናን አስልቶ፤

ጉርብትና ቀረ ቅንነት ተወግቶ።

ያበላው እጅሽ ነው ሃሞቱን አፍርቶ፤

ያስጠጋሽው ቅንቅን ባናቺ ላይ ተላምቶ

ገላሽን ጨረሰው አድቅቆ አላምጦ፣

አንቺነትሽን ወሮ – ነፍስሽን ተረጦ።

በነበልባል እሳት ባትለበለቢ፣

በነዲድ በወበቅ ባትንገበገቢ፣

ምንአለ? ምንአለ በደመራ ረመጥ ባትነገረገቢ?

ምንአለ? ——— ምንአለ ታሪኩ ቀርቶብሽ የዛሬን ብትኖሪ …? —-

ለነገ ብታድሪ ….።

ዘመንሽ ተሰብሮ ስታይ ቀን ስባሪ፤

መርምሪ መርምሪ መርምሪ መርምሪ መርምሪ መርምሪ …

እስኪʼገኝ ገቫሪ።

እሾሁ ከጓሮ ከመዳፍ ብርአንባር፣

ለራብ የሆንሽለት እሱነው ግብርአበር፤

የበቀል ወሸባ የድንኳን ውልሰበር።

ሁሌ አስብሻለሁ እናትዓለም ጎንደር፣

እኔ ልሙትልሽ ልሁንልሽ አፈር፣

ያሳደገኝ ጡትሽ ይመስክር በገበር።

አነባልሻለሁ ቢማኝ ፈጣሪ፣

አለቅስልሽላሁ ቢማኝ ፈጣሪ፣

የውስጤን ፍላሎት ከሆነ ተጋሪ።

ቀንሽ ተቀዳዶ፤ ስፌትን ሲማጸን፣

ድንበር አልፎ ሄደ ጨለማሽ ሆነ ዕውን።

ዓለም መሰከረ ድቅድቁን ኑሮሽን

የቹቻ – የገመድ – የሰኔል – ልማትሽን።

 

  • ሥጦታ —- በሞት አፋፍ ላይ ለምትገኘው ጎንደር ይሁንልኝ። /12.11.2017 -ሲዊዘርላንድ።/
  • ቶው —– ከዘሃበሻ ድህረገጽ ላይ የተወሰደ።

እግዜሩ ይስጥልኝ። መሸብያ ጊዜ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.