በሕወሃት ውስጥ የስብሃተ ነጋ ኃይል – ናኦሚን በጋሻው

ሕወሃት በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ያልሆኑ እንደ አቶ መስፍን እና አቶ ስብሀት ነጋ ያሉ ተገኝተው እንደነበረ በስፋት ተዘገቧል። በተለይም አቶ ስብሐት ነጋ ከመለስ ዜናዊ በፊት ለረጅም ጊዜ የሕወሃት አመራር ሆነው እንደማገልገላቸውና በድርጅቱ ውስጥም ያሉ አመራሮችን በጥቅምና በዝምድና  የያዙ እንደመሆናቸው ቀላል የማይባል ተጽኖ አላቸው። በግትርነታቸው የሚታወቁት አቶ ስብሀት ነጋ ለብዙ ጊዜ በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል በተለይም በሰሚን ሸዋ አስተማሪ ሆነው ያገለገሉ፣ የሕዝቡን ችግርና ድህነት በሚገባ የሚያወቁ ሲሆን በተለይም አማራ በሚሉት ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸው፣ በትረ ስልጣኑን ከስሜን ወደ መሐል የወስዱት የሸዋ ነገስታት ናቸው በሚል የሸዋን ሃይል ለማጥፋት የግል አላማቸው (personal mission ) ይዘው የሚንቀሳቀሱና፣ ስር የሰደደ ዘረኝነትና የሸዋ ጥላቻ ያለባቸው ሰው መሆናቸው ይነገራል።

ከዚህ በታች ያለው ፎቶ ምን ያህል ሕወሃት በእኝህ ሰው እንደተያዘ በግልጽ የሚያመላክት ነው። ህወሃት የትግራይ ሕዝብ ጥቅም፣ የአድዋና ህዝብ ጥቅም የሚያስጠብቅ ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ስም የጥቂቶችን የበላያነት ያሰፈነ የማፊያ ቡድን መሆኑ መገንዘብ ይቻላል።

ጦማሪ ዮናስ ሃጎስ አይጋ ፎረምንና ጦማሪ  Natnael Asmelashን በመንጭነት በመጠቀም “ፎቶው ላይ ያሉትን ሰዎች ተዋወቁዋቸው” በሚል የሚከተለዉን ጦምሯል።

1.ከፊት ለፊት ያሉት አቶ ስብሃት ነጋ ናቸው።
2.ከስብሃት ነጋ በስተ ግራ ያሉት አቶ ተክለወይኒ ናቸው፣ አቶ ተክለወይኒ የአቶ ስብሃት ነጋ የአጎት ልጅ ናቸው። አቶ ተክለወይኒ የማረት ገንዘብ ቆርጥመው የበሉ ናቸው፣ ከዚህ በተጨማሪ ለትግራይ ልማት ማህበር ከውጭ የተላከ አንድ መርከብ ሙሉ ብረት ሸጠው መርከብዋ ባህር ውስጥ ሰመጠች በማለት ብዙ ሚልዮን ብር የበሉ ናቸው።
3.ከስብሃት ነጋ በስተቀኝ በኩል ያሉት አቶ ጸጋይ በርሄ የስብሃት ነጋ የእህት ባል እና የጠቅላይ ሚኒስትር የደህንነት አማካሪ ናቸው።
4.ከአቶ ስብሃት ነጋ ጀርባ ያሉት ሁለቱም ሴቶች ተመልከቷቸው። አንደኛዋ የአቶ ስብሃት ነጋ እህት ወ/ሮ ቁድሳን ነጋ ስትሆን ሁለተኛዋ ከአቶ ስብሃት ነጋ እህት ጎን ያለችው ሞንጆሪኖ ትባላለች፣ የአቶ ስብሃት ነጋ የአጎት ልጅ ነች።
***
የጦማሪ ዮናስ ሐጎስን አባባል በመዋስ “ አልታወቀንም እንጂ አሁንም በኢትዮጵያ ከፊውዳል ስርዓት ገና ነፃ አልወጣንም.”። አገራችንን አፍንዉአን ተቆጣጥረው ችግር ውስጥ እየከሰሷት ያሉት እኝሁ አቶ ስብሀት ነጋና በርሳቸው ስር ያለው ቤተሰባዊ ቡድን ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.