ሼህ መሓመድ አል አሙዲን ፋና ሬድዮ ላይ እና ድሬ ቱብ ላይ ተፈቱ….!  – ልዑል አለሜ

 

በኢትዮጵያ ላይ ማንም ግፍ ሰርቶ እንደሆነ ይጠንቀቅ!! ገንዘብ ወይም ስልጣን ወይም ዘር ማንዘር አያድንወም ሁሉም የእጁን ያገኛል… ከዚያ ዉጭ በሼህ መሓመድ አል አሙዲን መታሰር ተተያቂዉ እራስቸዉ ሼህ መሐመድ አል አሙዲን ብቻ ናቸዉ በተጨማሪ ሼሁን ያሰረቻቸዉ በሙስና ምክንያት ከፍተኛ ችግር ላይ የምትገኘዉ ሳኡዲ አረቢያ ናት ሳዉዲዎች ከመሬት ተነስተዉ በስሜታዊነት ወይም በጸብ እንዲህ አይነት አለም አቀፋዊ ስህተት ይፈጽማሉ ማለት ዘበት ነዉ።
እዉነቱን መጋፈጥ ግድ ይላል ሼህ ማህመድ አላሙዲን የተፈቱት ፋና ሬዲዮና ድሬ ቱብ ገጽ ላይ ብቻ ነዉ ከዚያ ዉጭ ምንም ማራገብ አያስፈልግም ከእንግዲህ እስረኛ ነዉ።
በርግጥ በሼሁ ድርጅቶች ዉስጥ ከ41 ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያኖች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዉ እየሰሩ ይገኛሉ ይህ ደግሞ የድርጅቶቹ ግዴታ ነዉ በሐገራችን ላይ እስከሰሩ ድረስ ያንን የማድረግ ግዴታ አለባቸዉ ከሰዉ ሐይል በዘለለ ሁናቴ መናፍስትን አምጥተዉ ሊያሰሩ የሚችሉ አይደሉምና።
ህወሃታዊያን ህዝባችንን አግባብ ያልሆነ ግብር እየተቀበሉት ከዘረፉት በቀረቻቸዉ ጥቂት ገንዘብ 6 ወር የሚዘልቅ መንገድ ሰራንልህ እያሉ በሚያላግጡበት ሐገር ላይ እንደ አላሙዲን አይነት ባለጸጋን እንደ ፈጣሪ መመልከቱ አይገርምም.. ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንዳለን ባንዘነጋ መልካም ነዉ
በሌላ በኩል ሙሰኝነትን በደግነት ሸፋፍኖ ማቅረቡም ተገቢ አደለም ሼሁ በሳኡዲ የፈጸሙት ወንጀል ተረጋግጦ እዉን ከሆነ በኢትዮጵያ ላይ በተመሳሳዩ በተዛማጅነት የፈጸሙት የሙስና ወንጀል የመጣራት ተግባር እንደሚቀጥል መጠራጠር የለብንም…. ሙሰኝነት እራሱን የቻለ ተግባር ነዉ ደግነት ደግሞ ሌላ ነገር ነዉ ሆኖም በችሮታ ወይም በስጦታ የሚሸፈን እዉነት ግን ግዜና ወቅት ይጠብቃል እንጂ መገለጡ አይቀርም ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.