ኢትዮጵያዊነት እና  ለማ መገርሣ፦ወደ ኀላ የለም፤ ወደኀላ ! ዳንኤል ሺበሺ

 

( የአርባ ምንጭ ልጅ የሆነው ዳንኤል ሺበሺ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል የነበረ ሲሆን ሁልት ጊዜ በዉሽት ክስ ተከሶ በወህኒ የማቀቀ አገር ዉኡስጥ የሚታገል ሰላማውዊ ታጋይ ነው። የመጀመሪያው ጊዜ ለሁለት አመት ከአትቶ የሺዋሥ አሰፋ፣ አቶ ሃብታሙ አያሌውና ሌሎችች ሰባትት እስረኞች ጋር በሽብርተኝነት ክስ ተከሶ ፣ አቃብኢ ሕግ መረጃ ማግኘት ስላልቻለ በነጻ ተሰናብቷል። ብዙም ሳይቆይ ከጋዜጠኛ ኤሊአያ ገብሩ ግር አመጽ አስነስታቹሃልል በሚል ለሁለተኛ ጊዘ ታስሮ በቅርብ ፍርርድ ቤት ነጻ ነህ ብሎታል።  አንጋፋ የቀድሞ አንድነት አመራርና አባላት የአንድንነት የለዉጥ ሃይሉ ምመስባሰብ አስፈላጊ ነው ከሚል አዲስ ፓርቲ ከማቋቋም በአቶ የሺዋስ አሰፋ የሚመራዉን ከመኢአድ ጋር በቅርበትት የሚሰርራው የሰማያዊ ርቲ ለእምቀላቅቀል መወሰናቸው ይታወቃል። ዳንኤል ሽበሺ ከነዚህ የቀድሞ አንድነቶች መካከል አንዱ ነው።)
የኦሮሚያው ኦቦ #ለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” አሉ? በርግጥ ልክ ነው፤ ግን ሱስምኮ ሰው ሰራሽ መፈወሻ ዘዴ አለው፡፡ ቢያንስ ለአንድ ወር ያህል ሱስ ከሚያስይዙ ነገሮች የራቀ ሱሰኛን፤ ያ ሱስ ይለቀዋል ይባላል፡፡ ከዚህም ባሻገር በሣይንሳዊ ዘዴ ማከምም የሚቻል መሰለኝ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ለሩብ ምዕተ-ዓመታት ከተቀበረበት በአንዴ ብድግ ሲል ማየት የኢትዮጵዊነት ሥነ-ልቦናዊ ቁርኝት፣ ጉልበት፣ ስሜትና መንፈስ፤ እስከ ምን እንደሆን ብዙም ላልገባን ብዙ ትምህርት ይሰጠዋል፡፡ በተለይ ብዙ ደጋፍና አባል ባይኖራቸውም የኦነግና የኀወሓት አስተሳሰብ አቀንቃኞች ባሉበት አካባቢ ይህ በይፋ መነገሩ ለኛም ብዙ መለዕክት አለው፡፡ አንድን ነገር ማሰብ፤ ያሰቡትን በድፍረት መናገር፤ እና የተናገሩትን ሆነው መገኘት የየራሱ መለኪያ እንዳለው አልዘነጋሁም ፡፡

አሃ! የተሳሳትኩ መሰለኝ፤ ሰውየው የተናገረው’ኮ እንደዛ አይደለም፡፡ አንዱ ጓደኛዬ ሲያርመኝ ኦቦ #ለማ መገርሣ ሲናገር “ኢትዮጵያዊነት ከሱስም በላይ ነው” ያለው እንጂ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ብሎ ብቻ አላለፈም በማለት፡፡ አዎን! አሁን በጣም ተስማማኝ፡፡ አንባቢዎቼ አትቀይሙኝ የግራ ጆሮዬን ለኀወሓት ደንነቶች ሰውቸው ስለነበረ አንደኛው ጆሮዬ በከፊል መስማት ተስኖታልና ዜናው ሸራርፌ ነው ያዳመጥኩትና “ከሰው ስህተት፤ ከብረት ዝገት ይባል የለ!?” ኦቦ ለማ አፉ በለኝ፡፡

የኢትዮጵያዊነት ብዥታን ማከም የሚቻለው ግን ከነፍሱ፣ ከሥጋው፣ ከሕይወቱ እና ከመላ ሀሳቡ የኢትዮጵያዊነት ሐቅ በመቀበል ነው፡፡ ቀደምት አባቶቻችን ለሀገር የከፈሉትን ዋጋ በማስታወስ ነው፡፡ ይሄንን በጥልቅ ስንረዳ፣ ኢትዮጵያዊነት ከዜግነት በላይ መሆኑን፤ ኢት/ዊነት የውርስ ጉዳይም አለመሆኑን፤ ኢትዮጵያዊነት በግድ የሚፃፍብን ሳይሆን #በፍቅር-በእምነትና-በዕውቀት የተቀበልነው ማኀተም መሆኑን፤ ኢት/ዊነትን ያገኝነው እንደ ዲቪ ሎተሪ በማመልከቻና በውልደት የተገኘ አለመሆኑን፤ በቀደምት ወላጆቻችንና በአሁኑ ትውልድ ደምና አጥንት የተገነባ መሆኑን በመረዳት ሲሆን፤ የሀገር ግንባታ ብቻም ሳይሆን #እኛምእርስ በርሳችን በደም የተገናኘን መሆኑን፤ እንደ እናት ልጅ በደም፣ በአጥንት፤ በሽልና (Fetus) በእንብርት የተቆራኘን መሆናችንን ስንረዳ ኢትዮጵያዊነት ማለት #መኖር ማለት ነው ብለን እንቋጨዋለን፡፡ በቃ! #መኖር ማለት ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ብዙ ነገራችን ነው፤ የአምላክ ፀጋ ብለን እንደመድመዋለን ፡፡

ወዳጆቼ ፦

ከኢትዮጵይያዊነት መራቅ የሚቻለው በክህደት ብቻ ነው ፡፡ የሚኒልክ፣ የቴዎድሮስ፣ የዮሃንስ ወይም የየትኛውም ነገሥታት ጉዳይ አይደለም፡፡ የኦሮሞው፣ ወላይታውና የአፋሩ ወዘተ ወላጆቻችን ለኢት/ዊነታቸው ተዋድቀዋል፡፡ ኢት/ዊነት ግን ረቂቅ ነው ያስባለው ምስጢር ይህ ነው፤ በደም ዋጋ የተገኘ ማንነት በመኖሩ ነው፡፡ እንደ ሌላው ዓለም ሀገራት በማመልከቻ የሚገኝ ዜግነት አይነት አይደለም፡፡

ኢት/ያም እንደ ሀገር በደም አጥንትየ ተገኘች የቃለ-ኪዳን ምድር ነው፡፡ ሐቁን መቀበል እንጂ፤ ምክንያት መደርደረ የትም አያደርስም፡፡ የበደለን የጎዳን ኢት/ጵያዊ መሆናችን አይደለም፡፡ የአገዛዝ ሥርዓታችን ነው፡፡ በዚህ ደግሞ የእያንዳንዳችን ድርሻ አለብን፡፡ እንደ ሰው ከወላጆቻችንም ከእኛም የተሰራ ስኀተት መኖሩን አምነን በመቀበል ወደ መፍትሄው መሄድ እንጂ ኢት/ዊነትን መራገም መሻልን አያሳይም ፡፡

ኦቦ ለማ በዚሁ መንፈስ ይቀጥሉበት፤ ወደ ኀላ የለም! ቃል ከተግባር ጋር እንጠብቃለን፡፡ የጋሽ ለማ አይነት አስተሳሰብ ያላችሁ በመጀመሪያ ሰው ነበራችሁ፤ ቀጥሎም ኢትዮጵያዊ ናችሁ፤ በመጨረሻም ወደ አይቀረው ዘለዓለማዊ ቤታችን እንሄዳለንና ደስ ይበላችሁ፡፡ ከፍታው የኛ ነው፤ ወደ ኀላ የለም! ወደኀላ፡፡ የትግላችን ፍሬ እንደሆነ ይሰማኛል፤ ትግላችን ምን ያህል የነጠረ እንደሆን አንዱ ማረጋገጫችን ይህ አስተሳሰብ መንሰራራቱ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያዊነታችን ጋር በውስጣችን ደምቆ ይኖራል፡፡ ሰላም !

1 COMMENT

 1. You are starting from a very wrong position. TPLF does not means the people of Tigrai.It is the same stupid mistake as those who claim the Derg represented the military or Hailselases’s government represents the Amhara people.
  TPLF represents the 60th poletical ideology .

  People are exited about the new PM because
  1. He is not part of the old group who was brought up in the communist philosophy of “Who ever has different idea from mine is my enemy and need to be destroyed”
  2. After 44 years for the first time we found a poletician who is not filled with hate or preach hate
  3.for the last 44 years we had the same group of people leading our countries poletics. It is obvious every one was yearning for a change
  4.The actions of the so called Lemme group in the OROMO region proved they are for positive change.
  Your assumption he dies not have the support TPLF is wrong they are Ethiopian as such there are people who want change and who oppose change in the TPLF too.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.