አንጀሊና ጆሊ እና ሌሎችም  (አሌክስ አብርሃም)

አንጀሊና ጆሊ
አንጀሊና ጆሊ

ከሰሞኑ አንዲት አሜሪካ የምትኖር ጠንቋይ የሴቶችን ከንፈር በማየት ብቻ ስለባለከንፈሮቹ ህይዎት ዘክዝኬ እናገራለሁ ማለቷን ተከትሎ አዳሜ እና አዳሚት ከንፈሩን አሞጥሙጦ እየጎረፈ መሆኑን ሰማን ! እና እንደተባለው ከሆነ ሴትዮዋ ካየቻቸው ከሁለት መቶ በላይ ከንፈሮች ስለባለከንፈሮቹ ተናግራ የተሳሳተችው አንዷን ብቻ ነው አሉ! የትምህርት ደረጃቸውን …ስማቸውን … ኧረ ብዙ ነገር ብቻ ብዙ ነገር መጠንቆል እንደቻለች ነው የተመሰከረላት!! ጌታ ይገስጻት አሜን ! ብለን አሁን ስለዴሞክራሲ እናወራልን:)

ወገኖቸ ከንፈር ስል ግን ምን ትዝ አለኝ ? ከሰሞኑ ፌስ ቡክ ላይ ዞር ዞር ስል አንዳንድ እህቶች ከንፈራቸውን ጎላ አድርጎ የሚያሳይ ፎቶ ለጥፈው ተመለከትኩ . . አንዳንዴ ፌስቡክ ላይ የምንለጥፈውን ፎቶ ከመለጠፋችን በፊት ሁለት ጊዜ ብንመለከተው ምናለ…የአገር ገፅታን መገንባት ቢያቅተን የዚች ሚስክን የፌስቡክ ሰፈራችንን ገፅታ ሆስፒታል አናስመስላታ ! እንዴ!

ካየኋቸው ሶስት ‹‹ከንፈር ቀደም›› ፎቶዎች ውስጥ ሁለቱ በከፍተኛ ደረጃ አንጀቴን ሲበሉት አንዱ ግን እንባየ በአይኔ እንዲሞላ ሁሉ አደረገኝ ! ከምር ! ነገሩ ‹‹ሴክሲ›› የመሆን ሙከራ ቢሆንም ግን እኔ የከንፈሮቹ መጎሳቆልና በዛ ሁሉ ቻፕስቲክና ሊፒስቲክ እንኳን ሊወዙ አለመቻላቻው ምን ያህል ‹‹ ኦቨር ዩዝ›› እየተደረጉ ነው ብየ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ! ወይስ የኑሮ ጉዳት የደረሰባቸው ከንፈሮች… ?

አንዱ ከንፈርማ ጭራሽ ለፎረንሲክ ምርመራ ከአስክሬን ላይ የተነሳ ሁሉ ነው የሚመስለው …ክስል ከማለታቸው ቋንጣ መሆናቸው ምን አጉል መካሪ ይሆን ያስለጠፋቸው ….መልሸ ደግሞ ኤጭ ባይለጠፍ ቢቀርስ ሰው እንዴት በዚህ ሚስኪን ከንፈር አስተዛዝኖ ላይክ ይቀበላል ብየ ተበሳጨሁ ! ወገብ ይዞ መነሳት በስንት ጠዓሙ ! አሁንኮ ወገኖች በአይፎን መስተዋት ፊት ስልፊ የሚነሱ እህቶች ከእነሱ ይልቀ ስልኩ የሚያማልልበት ደርጃ ላየ ደርሰናል( ይች አገር ግን ወዴት እየሄደች ነው:)

ታዲያ ለአንድ ፖለቲከኛ ወዳጀ ፎቶዎቹን አሳየሁት ፊቱን ቅጭም አድርጎ ከስልኩ ላይ ቀደም ሲል ያስቀመጠውን የሚያምር የከንፈር ፎቶ ከፍቶ ‹‹ተመልከት ዲሞክራሲ ያለበት አገር እና የሌለበት አገር የከንፈር ልዩነት …. እዚች አገር ላይ ወንድ የለም እንጅ ወንድ ቢኖርማ እንዲህ የእህቶቻችንን ከንፈር ያደረቀውን ወያኔን ተፋልመን ማውረድ ነበር ›› ብሎ ዛተ ! እኔም ክፉኛ ዴሞክራሲ ናፈቀኝና ለሌላ ነገር ሳይሆን ለልምድ ልውውጥ ‹‹ይሄ የማነው ከንፈር ›› በማለት ጠየኩ ….ይሄን ከንፈር ከዚህ በፊት የት ነው የማውቀው እያልኩ ….

‹‹የአንጀሊና ጆሊ !!›› አለኝ ኮስተር እንዳለ!! ቀጠል አድርጎም ተመልከት ይሄን የአንጀሊና ጆሊ ከንፈር በአንድ ሳመንት ብቻ ከሃያ ሚሊየን በላይ ህዝብ ላይክ አድርጎታል ! አለኝ ! እውነትም ዓለም “በዴሞክራሲ ፍቅር አብዷል” ብየ እኔም አገሬን በመወከል ያንን ዴሞክራሲያዊ ከንፈር ላይክ አደርኩት ጓደኛየ ቀጠለ ” የኛዎቹን ተመልከት የስልሳ ብር ሊፒስቲክ አክስረው ሰላሳ ሰው ብቻ ነው ላይክ … በዛ ላይ ኮሜንቱ ….

ኮሜንት ከፍተን ማንበብ ጀመርን ከአንጀሊና ከንፈር ስር አንዱ ምን ብሏል ‹‹በሳመር እንደሚፈነዳ ውብ አበባ የሚያስጎመጅ ቢታይ የማይጠገብ ከንፈር ››

ከኛው ሚስኪን ከንፈር ስር (ልጅቱ አይኗን አስለምልማ የፌስ ቡክን ወንድ ሁሉ በማማለል ከንፈሯ ለአንድ ሳምንት መነጋገሪያ ይሆን ዘንድ 79 ሰው ታግ አድርጋ የለጠፈችው ” ከንፈር ቀደም ” ፎቶ ስር

‹‹ አንች ከክፍለ ሃገር አዲስ አበባ ድረስ ፒስታ ፒስታውን በከንፈርሽ እየተራመድሽ ነው እንዴ የመጣሽው ›› የሚል ኮሜንት !! የተረገመ ! ታዲያ ዴሞክራሲ በየት በኩል ይለፍ. … (ይች አገር ግን ወዴት እየሄደች

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.