የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት ረገጣውን እንዲያቆም እንግሊዝ አሳሰበች

 

የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲያቆም እንግሊዝ አሳሰበች፡፡ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ሱዛና ሞርሄድና ለኢትዮጵያ መንግስት በሰጡት ማሳሰቢያ፣ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሔዱ ካሉ ተቃውሞች ጋር በተገናኘ የሰብዓዊ መብት ረገጣ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡ ይህም ጉዳይ እንግሊዝን እንዳሳሰባት አምባሰደሯ ተናግረዋል፡፡ አምባሳደር ሱዛና ሞርሄድና ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሰደርን ጨምሮ የኤምባሲው የስራ ኃላፊዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ተገኝተው እንደነበር ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በውይይቱ ላይ እንደተገለጸው ከሆነ፣ በኢትዮጵያ ከሚካሄዱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ጋር ተያይዞ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን የእንግሊዝ አምባሳደር ተናግረዋል፡፡ ሌለው የውይይቱ አጀንዳ የነበሩት የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መሆናቸውን የጠቀሰው መረጃው፣ በውይይቱ ላይም ስለእሳቸው መነሳቱም ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእስር አያያዝ ምን እንደሚመስል ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የጠቀሰው መረጃው፣ ከኢትዮጵያ በኩል ‹‹እንደ ማንኛውም እስረኛ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡›› የሚል ምላሽ መሰጠቱን መረጃው አክሏል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ‹‹የአቶ አንዳርጋቸው ሰብዓዊ መብት እየተከበረ ይገኛል፡፡›› ሲሉም ገልጸዋል፡፡ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በመንግስት በኩል ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ከዱባይ ወደ ኤርትራ በሚያመሩበት ጊዜ የመን ላይ ተጠልፈው ለእስር መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡

BBN news November 15, 2017

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.