የጎንደሩ ጉዳይ ህወሀትና አማራ ሊታረቁ እንደማይችሉ፤ ለእኛም ፈተና እንደሚሆን ነው – አያሌው መንበር

“የጎንደሩ ጉዳይ ህወሀትና አማራ ሊታረቁ እንደማይችሉ፤ ለእኛም ፈተና እንደሚሆን ነው ያረጋገጥኩት”…ይህንን ያለኝ አንድ ቀድሞ የማወቀው እና ሰሞኑን በቦታው የተገኘ ሰው ነው።
ሰውየው ቀጠል አድርጎም ” ህወሃቶች ራሳቸው ይህንን አውቀውታል፤ ሳይገርማቸውም የቀረ አይመስለኝም” አለኝ።

እኔም “የዋህ ነህ ለካ፤ እኛ እኮ ይህንን ያህል የምንጮኸው የመጮህ ሱስ ስላለብን አይደለም፤ የዛሬ ስቃያችን ብቻ ሳይሆን የነገው ኑሯችንም እጅግ ፈታኝ መሆኑን ስለተረዳን ነው አልኩት።ብዙዎች በተለይም በእኔ እንዲህ ፅንፍ መያዝ ይገረማሉ፤ አንዳንዶች ሊመክሩኝም ሊገስፁኝም ይሞክራሉ፤ ጥቂቶች ደግሞ ሊያስፈራሩኝ ይጥራሉ።እንከፍ ዲያስፖራ ደግሞ ዛሬም በ70ዎቹ እንደተኛ ነው።እና እላችኋለው ሁሉም የእኔን የመጮህ ምክንያቴን አይጠይቁኝም።ብዙዎች ግን በተለይም ለመረጃ እና ለፖለቲካ ቅርብ የሆኑት ስህተት እንዳልሆንኩ ይልቁንም እነርሱም ቢናገሩና ቢፅፉ እንደሚታፈኑ ስለሚፈሩ እንጅ ትክክል እንደሆንኩ እንዲያውም በእኔ እንደሚኮሩ ይነግሩኛል።የእኔ ዋና Target Audience ብየ የማስባቸውም እነዚህ ሰዎች በመሆናቸው ለሌላው ስድብ ይሁን ማሰፍራሪያ ቦታ አልሰጠውም።በተለይም ስታርባክስ ቁጭ ብሎ አልያም በድግስ ሲገናኝ ፖለቲካ ትውስ ሲለው የሀሜት ሱሱን ለሚወጣ “ነፃ አውጭ” ደንታ የለኝም።

እናም እነዚህ ብዙዎች በተለይም በኦሮሚያ/ኦህዴድ ጉብኝት ላይ በነበረኝ የተለሳለሰና ሁኔታዎችን ያገናዘበ አቋም ሲገረሙ ነበር።በሰሞኑ የትግራይ/ህወሃትና የብአዴን ድግስ ላይ በነበረኝ እጅግ የጠነከረ አቋም ነገሮችን ማለዘብ እንዳለብኝም የመከሩኝ ነበሩ።ባልቀበላቸውም ይህንን በማለታቸው አልተቀየምኳቸውም።እነርሱ ይህንን ያሉት ከሁኔታዎች አስፈሪነት አንፃር እንጅ የአማራ ህዝብ ቁስልና በደል ሳይገባቸው ቀርቶ ነው ብየ አላምንም።እናም ዝም አልኩና መፃፌን ቀጠልኩ።

ዛሬ ማታ መረጃ ለመሰብሰብ ወደ ጎንደር አካባቢ ሰው ሳፈላልግ አንድ ሰው አገኘውና ከለማ መገርሳ የትግሬ ህወሀት ማለዘቢያ ጉብኝት ጀምሮ እስከ ዛሬው የህወሃት የጋቢ ሽልማት አጫወተኝ።እርሱ የዛሬውን ስብሰባ ከጅምሩ እንዲህ የተጠላ እና በህዝቡ ዘንድ እንደ ሀጢያት ይቆጠራል የሚል እምነት አልነበረውም መሰለኝ። መጨረሻ ላይ ከቦታው ተገኝቶ ሲመለከት ግን እኛ የምንጮህለትን እውነታ በደንብ ተገነዘበው።”እኛ ራሱ ከህዝብ ጋር እንዴት እንደምንታረቅ አናውቅም አይደለም ህወሃት” ብሎኝ አረፈ።ትክክል ነው።በአሁኑ የጎንደር ላይ ሽርሽር ህወሃት ላይ ያለን የተለመደ የጠላትነት ስምና ግብር አይቀየርም።ብአዴን ላይ በከፊል የነበረን “ሊለወጥ ይችላል” የሚለው የሞኝ ምኞት ግን ያከተመበት አንዱ መለኪያ ይህ ስብሰባ ነበር።ብአዴን ብዙ ድስኩሮችን በስብሰባው አሰምቷል።አቶ ገዱ የአማራን ህዝብ ባህሪይ ለትግሬ ህወሃት የጋቱበት መንገድ ብቻ በበጎው ሊነሳ ይችላል።ያም ቢሆን ግን ቂጥ ጥሎ ክንንብ ነው።መጀመሪያውን ከህወሃት ጋር ለመሸማገል ከመሞከር ይልቅ ህወሃት የአማራን ህዝብ መሰረታዊ እና የማይቀለበሱ ጥያቄዎች እንዲፈታ መመካከር ይቀድም ነበር።ይህ አልሆነም።የአባይ ወልዱ አንድ መቃብር ውስጥ እንቀበር ልመናም ትክክል ነበር።አንድ አውጭ ጉድጓድ ውስጥ የወጡ ሁለት አውጭዎች ሞታቸውም ተመሳሳይ እንደሚሆን መቸ ጠፋንና።አባይ ወልዱ የተሸወደው ግን የአማራ እና የትግራይ ህዝብን አንድነት ለማሳየት የሆደበት ነው።በግሌ ሁለቱ ህብዞች ተጣልተዋል ባልልም የትግራይ ህዝብ የአማራ ህዝብ ገዳይ ህወሃትን እየተንከባከበ በመያዙ ቂም አልያዘም ማለት አይደለም።እናም ትግሬና አማራ በአንድ ሚዛን የሚቀመጠው ትግሬ ህወሃት እኮ ወንጀለኛ ነው ብሎ በአደባባይ ሲናገር እንጅ “እምበር ተጋዳላይ” እየጨፈረ አይደለም።እና ለእኛ ለአማራዎች ለጊዜው ከእናንተ አንድነት ይልቅ ማዶና ማዶነት ይሻለናልና ያዝ አድርጉት ነው መልሳችን።

የሆነው ሆኖ ብአዴን ልክ እንደ ወልቃይትና ራያ ሁሉ ግጨውን አስረክቦ አይኔን ግንባር ያድርገው ያለ እርሱ ታውሮ ሌላውንም እንደ እውር የሚቆጥር ድርጅት ነው።ብአዴን በ37ኛ በዓሉ አማራ የሚል ስም መጥራት ያሳፈረው ወራዳ ድርጅት ነው።እዚህ ድርጅት ውስጥ ያላችሁ ወንድሞቸና እህቶቸ ብአዴን የአማራን ክብር ከማዋረድ አልፎ ህዝባችን በድህነት ውስጥ እንዲማቅቅ ማደረጉን በማስረጃ ሳቀርብላችሁ ስለቆየው ዛሬ ወደ ዝርዝር አልገባም። ብአዴን ምን ማደረግ እንዳለበት ማዘዝ ባንችል እንኳን የተሻሉ አማራጮችን ነገረነው ነበር።ብአዴን ግን በድን ነው።እናም ለወዳጀ እናንተማ እንግዲህ “አ* የነካው እንጨት ናችሁ” አልኩት።

ከዚያም እናንተ ደግሞ በቃ ጋዝ እያርከፈከፋችሁ ህዝብ ፊት እንዳንቆም አደረጋችሁን አለኝ።እኔም ከህዝብ ፊት እኮ እንዳትቆሙ የሆናችሁት ባለፈው አመት የተነሱ ጥያቄዎችን “የስራ አጥነት ጥያቄዎች ናቸው” ብላችሁ ራሳችሁን ያታለላችሁ እለት ነው በማለት ወደ ቀልድ አዘል ንትርክ ስንገባ በል ደህና አምሽ ተባብለን ተለያየን።የባለስልጣናትን ተስፋ መቁረጥ፤የህወሃትን መሸማቀቅ (ይህችን እንኳን ለማመን ከብዶኛል)፣ወደፊት ምን ማደረግ እንዳለባቸው ግራ መጋባት ጉዳይም በስፋት አጫውቶኛል።

የሆነው ሆኖ በጎንደሩ ስብሰባ አማራ ድል አድርጓል።ህወሃትና ብአዴን እንኳን ከህዝቡ ጋር ሊቀራረቡ ቀርቶ ያልጠበቁት የህዝብ ጥላቻ በመከሰቱ እርስ በርሳቸውም ድግሳቸውን በሰላም የበሉ አልመሰለኝም።እኔም ክብር ለጎንደር አማራ ማለትን ወደድኩ!!!

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሌላ መንገድ እባክህ ተወን ያላችሁት መልዕክት ደርሶኛል።እኔም መልሴ የምትዋችሁ አማራ መሆን ስትችሉ ነው የሚል ነው።መልካም የፖለቲካ የጫጉላ ሽርሽር ይሁንላችሁ ብያለው።እኛ እና ትግሬ ህወሃት ግን ለአርባ ትውልድ አንታረቅም።ይህንን እውነታ ካላመንክ አንድ የአማራ ወጣትን ጠይቀው ይነግርሃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.