የአቶ ማሙሸት አማረ ባስቸኳይ ከእስር ቤት ይለቀቅ ዘመቻ!

አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሊቀመንበር የነበሩ
አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሊቀመንበር የነበሩ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዓለም አቀፍ የድጋፍ ትብብር ግብረ ኃይል።

Dallas, Texas U.S.A.
November 18, 2017

ባስቸኳይ የመኢአድ ሕጋዊው ሊቀመንበር ማሙሸት አማረ ከእስር ቤት ይለቀቅ!

መኢአድ ለመላው ኢትዮጵያውያን ድምጽ ሆኖ የተቋቋመ ድርጅት ነው።
በመኢአድ በሕጋዊው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ማሙሸት አማረ በሊቀመንበርነት መመረጡ ይታወቃል። በተለያየ ጊዚያት በአንባገነኑ የወያኔ መንግስት በተደጋጋሚ በሃሰት ሲወነጀል እና ሲታሰር እንደነበር ለሁላችንም ግልጽ ነው። እንደገና በኢትዮጵያ አቆጣጠር በመጋቢት ወር ሁለትሺ ዘጠኝ (2009) ጀምሮ በከፋ ሰቆቃ እየደረሰብት በእስር ላይ ይገኛል።

ክቡር ውድ ታጋይ ወንድማችን ማሙሸት አመረ እና 122 በላይ የሆኑትን የመኢአድ አባላትን ጨምሮ በወያኔ እስር ቤት እየተሰቃዩ ስለሆነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁልን በአገር ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትዮጵያዊያት ከዚህ በታች ባለው የፊርማ ማሰባሰቢያ ሰነድ ላይ ፊርማችሁን በመሙላት ትተባበሩ ዘንድ በክብር ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።

https://www.thepetitionsite.com/466/469/764/release-mamushet-amare/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.