አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም እና አባ ገ/ ስላሴ ፀሎት እንዳያደርጉ፣ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዳይቀርቡ፣ ምግብ አብረው እንዳይበሉ ተከለከሉ

አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም እና አባ ገ/ ስላሴ ወ/ሐይማኖት የዋልድባ መነኮሳት ናቸው። የ”ሽብር” ክስ ቀርቦባቸው ቂሊንጦ ይገኛሉ።

የቂሊንጦ ዞን 3 ኃላፊ ኦፊሰር ካህሱ ፀሎት እንዳያደርጉ፣ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዳይቀርቡ፣ ምግብ አብረው እንዳይበሉ እገዳ እንዳደረገባቸው በችሎት ገልፀው ነበር። እስር ቤቱ ከደህንነት መስርያ ቤቱ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት እንደሚከታተላቸውም ተነግሯቸዋል። እስረኛ መስሎ አብሯቸው የሚተኛው ግለሰብ በየእስር ቤቱ እየገባ የሚሰልል የደህንነት መስርያ ቤቱ ሰራተኛ መሆኑ ታውቋል።

አሁን ደግሞ መነኮሳቱን ነጣጥለዋቸዋል ተብሏል። አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያምን ከዞን 3 ወደ ዞን 2 ቀይረዋቸዋል። ዞን 2 ኃላፊ የሆኑት የትህነግ ታጋዮች ደግሞ ከካህሱ የባሱ ናቸው። ኃላፊዎቹ እየፈፀሙት እንዳለው ወከባ በቅርቡ መነኮሳቱ ጨለማ ቤት ገቡ የሚል ዜና እንሰማ ይሆናል።

(በጌታቸው ሺፈራው)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.