የህዝቅኤል ጋቢሳ መንገድ (ሰሎሞን ይመኑ)

 

ህዝቅኤል ጋቢሳ

‎ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳና ጸጋየ አራርሳ እንዲሁም ሌሎች እነሱን የመሰሉ የአክራሪ የኦሮሞ ብሔር አቀንቃኞች መነሻቸውም መድረሻቸውም ጠላታቸውም ሊያጠቁት የሚፈልጉት ብሔር እና ሊያጠፉት የሚፈልጉት ብሔርም አማራው እንደሆነ ደጋግመው የሚሰብኩት መልእክት ያውም ወያኔ የሚጠቀመውን ትምክህት የሚል ቃል በመደጋገም ነው፡፡ ይህም በአንድ በኩል የሰዎቹን የትምህርት ደረጃና የሚናገሩትን አመለካከት ሳይ እነዚህ ሰዎች እውን የኦሮሞን ህዝብ የሚጠቅም ትግል እያደረጉ ነው ወይስ የወያኔ ቅጥረኞች ናቸው የሚለውን ጥያቄ እንዳነሳ ያስገድደኛል፡፡

  በተደጋጋሚ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች እና የሌላ ብሔር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግድያና መፈናቀልም የነዚህ ፅንፈኞች የአስተምህሮ ውጤት ለመሆኑ ማሳያ የሚሆነውም ይህ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰ ያለው በእነዚህ የቅርብ አመታት ውስጥ እንጅ የዛሬ 30 እና 40 አመት የሰፈሩ ሰዎች ምንም ችግር ሳይደርስባቸው ይኖሩ እንደነበር እየተናገሩ ነው፡፡

ለእኔ ፕሮፌሰር ማለት በፕሮፌሰርነቱ ሃገርን የሚጠቅም ስራ ሲሰራ እንጅ ህዝብን ከህዝብ የሚነጣጥል እና የሚያጋጭ ስራ መስራት አይመስለኝም ከዚህም በተጨማሪ ያለምንም ጥናታዊ ማሳያ አንድ ፕሮፌሰር የሚያክል ሰው በደም ፍላት በመሰለኝ እና በደሳለኝ የአንድን ብሔር ክብር በጠቅላላው መንካት ለኔ ከአርቆ አሳቢው ያገሬ ገበሬ በታች ነው፡፡ 

  ህዝቃኤል ጋቢሳ ከዚህ በፊትም የአማራ እና የኦሮሞ ትግል እየተናበበ ሲሄድ እና የሕውሓት ትንፍሽ ወደመቆሙ ሲጠጋ የኦሮሞ ህዝብ ቻርተር በሚል በተነሳው ሃሳብ ሲጠየቅ በቪኦኤ እኔ የማውቀው የለም ካለ በኃላ በሳምንቱ የቻርተሩ አርቃቂና ዋና አወይይ ሁኖ ቀረበ ይህዝቡን የመተጋገዝ የትግል ጉዞ ለማስቆምም ለወያኔ አጋርነቱን ያሳየ እንቅስቃሴ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ከህዝቡ ትግል ጀርባ ያሉ ሚስጥራዊ ደባዎችንም አይተንበታል፡፡ ዛሬ ደግሞ «የአማራ ልሂቃን ወደ ድሮው ስርአት ሊመልሱን ይፈልጋሉ» ሲል ይወርፋል ይህንም አብረውት ውይይት ላይ ለነበሩ ነጮችም ለማስረዳት ደፋ ቀና ሲል ይታያል፡፡

*1ኛጥያቄ…በህዝቅኤል አገላለጽ የአማራ ልሂቃን ወደየትኛው የድሮ ስርአት አይነት ሊመልሱን እንደሆነና የተሰሩ ስራዎችን እባክህ በነካ እጅህ ዘርዝረህ አስረዳን?

*2ኛ ጥያቄ…አንተ ያቀረብከው የውይይት ሃሳብ ስለአማራ ልሂቃን ለነጮች ያቀረብከው የግል አቋምህ ነው ወይስ የወያኔ ትእዛዝ ነው? እነዚህ ነጮችስ ከአማራ ልሂቃን ጋር እንዲያስታርቁህ ነው ወይስ ከሃገራቸው እንዲያስወጡልህ ነው ልመናው?

 በመጨረሻም ህዝቅኤ የምትችል ከሆነ ይህን አቋም የሚያራምዱ የአማራ ልሂቃን አድራሻቸውን ብትጠቁመን መልካም ነው፡፡

ሌላው የህዝቅኤል ሰው ጸጋየ አራርሳ

***********************

ይህም ልክ እንደህዝቅኤል በአማራ ህዝብ ላይ የተነሳ የአማራን ህዝብ ልክ እንደ ወያኔ «ትምክህተኝ» እያለ ይገልጻል፡፡ 

ከወራቶች በፊትም ስለ አዲስ አበባ በተነሳ ክርክር አማራው መጤ ነው ይላል፡፡ እንግዲህ ይህ ሰውየ በስደት ካናዳ ይሁን አሜሪካ ሁኖ ጥገኝነት ጠይቆ እና የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቶ ቤተሰብ መስርቶ ሃብት ንብረት አፍርቶ እየሰራ እየኖረ ለኢትዮጵያ ህልውና ደሙን እና አጥንቱን ለገበረው አማራ መጤ ነው ማንም አማራ በኦሮሚያ ክልል መኖር የለበትም ይላል፡፡ እሽ ይህን ካልክ አማራ ክልል ላይ የሚኖሩ ከ3 ሚሊዮን በላይ ኦሮሞዎችስ የት ይግቡ? እነሱም ከአማራ ክልል ይውጡ? እኔ እሰከማውቀው ድረስ እንደናንተ አፉን ሞልቶ በአማራ ክልል ላይ በሚኖሩ ኦሮሞዎች ችግር እንዲደርስባቸው በሚዲያም ይሁን በተለያዩ መንገዶች የቀሰቀሰ የአማራ ልሂቅ የለም፡፡

  

ለአማራ ልሂቃን

**********

የእነ ህዝቅኤል መንገድ የወያኔ መንገድ እና የወያኔ ቡድን እንደሆነ በግልፅ እያሳየ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኑሮ ፍሽስት ወያኔን ለመጣል ስቃይና ችግር ውስጥ ያለውን የአማራ ህዝብ ለትግላቸው እንቅስቃሴ እንደፓለቲካ መቆመሪያ ልክ እንደወያኔ ባላሰሩ ነበር፡፡

  በመጨረሻም የእነ ህዝቅኤል መንገድ ተጋብቶና ተዋልዶ የሚኖርን ህዝብ ለመነጠል እና የግጭት ማእከል ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት የአማራ ልሂቃን ካላችሁ በቃ ልትሏቸው ይገባል፡፡

በመጨረሻም የአማራ ልሂቃን ካላችሁ እስኪ ህዝቅኤል እንደሚለው ወደ ድሮው ስርአት መልሱን እና እንዴት እንደነበር እንየው እባካችሁ፡፡ በጣም ኮሚክ የሆን ሰውየ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.