አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ የመሆን ግዴታነትና የእራሱ በሆነው በኢትዮጵያ ፊደል የመገልገል ተገቢነት

በአብርሃም ቀጀላ (ተሻሽሎ የቀረበ)

ከጥንት ጀምሮ አስቀድሞ በሀገረ ኢትዮጵያ ላሉት የህዝብ ቋንቋዎች ሁሉ በምልአት፣ በጥራትና በብቃት ሲያገለግል የነበረው፤ በተለምዶ ግእዝ ፊደል ተብሎ የሚጠራው  የሁሉም ኢትዮጵያውያን ፊደል እ.ኤ.አ በ1983 ዓ.ም በመንግስት መለዋወጥ ተፈጥሮ በነበረው ክፍተት ጥቂት ግለሰቦች በፖለቲካ ስሜታዊነትና ግልፍተኝነት ወደፊት በቀጣዩ ህዝቦች  ላይ የሚያመጣውን ጣጣ፣ መዘዝ፣ ጉዳት እና ቀውስ ሳያጤኑ የቀድሞ ያለፈው ፓለቲካዊ ችግር በፈጠረው ቁጣና ትኩሳት ብቻ በመነዳት አፋን ኦሮሞ ግእዙን እንዲተው አድርገዋል።

በዚህ በነባሩ የግእዝ ፊደላችን አፋን ኦሮሞን በተመለከቱ

1ኛ. ከ16ተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ቅዱስ ቁርአን የተከተበበት ሰነድ በሀረር ይገኛል።

2ኛ. በ1845 ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን በፊት የመፅሀፍ ቅዱስ ወንጌላት በከፊል የተፃፋበት

3ኛ. ከ140 አመታት በፊት በኦሮሞው ሊቅ በቅዱስ አናሲሞስ ነሲብ (አባገመችስ) ሙሉው መፅሃፍ ቅዱስ በአፋን ኦሮሞ የተተረጎመበት

4ኛ. በ1967 አ.ም. ከ20 በላይ በሆኑ በተለያዩ ብሄርና ብሄረሰቦች ቋንቋ የመሬት አዋጅን ፈትፍቶና ቁልጭ አድርጎ የተገለፀበት

5ኛ. የኢትዮጵያ የመስረተ ትምህርት ከ30 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች ቋንቋዎች በብቃትና በጥራት ይሰጥበት የነበረ

6ኛ. የበሪሳ ታላቅ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጣ ለዘመናት በበርካት ቁጥሮች ሲሰራጭበት የነበረ

7ኛ. የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት በበርካታ ባብዛኛው ከ 45 ብሄር ብሄረሰቦች በላይ ቋንቋዎች የተገለጡበት

8ኛ. በበርካታ የእስልምና ዝክሮች፣ መንዙማዎች የተፃፋበት የተዘከሩበት

9ኛ. በርካታ የክርስትያን መዝሙራት በኦሮምኛና በሌሎች ቌንቌዎች የተገለጡበት

10ኛ. በአፋን ኦሮሞና በሌሎችም ከረጅም ዘመናት በፊት የመዝገበ ቃላት የተደራጀበት ናቸው።

ከእነዚህ ነገሮችም በላይ ብዙ በመሳሰሉት ሁሉ አድጎ ዳብሮ  ተፈትኖ  ተፈትሾ  ተመስክሮለት የደረጀ መሆኑን ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱት እውቁ ኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ ሳይንቲስትና ኣርበኛ ዶ/ር አበራ ሞላ (Dr. Aberra Molla) ከዛሬ 30 ዓመታት በፊት ማለትም ኢ ህ ዴ ግ አገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊት በተለምዶ የግዕዝ ፊደል (Ethiopic) ተብሎ የሚጠራውን የኢትዮጵያውያን ሁሉ ፊደል በኮምፒተር እንዲጻፍ በመፍጠርና በዩኒኮድ በማስገባት በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲመዘገብ አድርገዋል።

 

ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት ኢትዮጵያዊ ሊቅ፣ ዶ/ር አበራ ሞላ ኦሮሚፋውንም ኣላስቀሩም

የኣፋን ኦሮሞ የግዕዝ ፊደልና ሌሎችም ቋንቋዎች በብቃትና በምልአት እንዲያገለግሉ በማድረግና የዩናይትድ እስቴትስ የፈጠራ ባለመብትነትና ባለቤትነት አግኝተዋል። “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጃምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” የሚለውን አረፍተ ነገር ላቲን በ36 ቀለሞችና በቁቤ በ45 ቀለሞች ከመክተብ ይልቅ በግዕዝ ፊደል በ24 ቀለሞች መክተብ  እንደሚሻል  በሳይንሳዊና  የተለያዩ መስፈርት ኣሳይተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የስራና የመግባቢያ  ቋንቋ  የሆነው  አማርኛ በአሜሪካና እስራኤል ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚገኙበት ከተሞች  ሁሉ  የሳቸው  ፈጠራ  ዋና ቁልፍ መስፈርት ማሟያ ሆኖ የጽሁፍና የስራ ቋንቋ ሆኗል። ከዚያም በላይ በተለይ በቨርጂኒያ ኣሌክሳንድሪያ ደግሞ የትምህርት ቤት መሞከሪያ ቋንቋ እንዲሆን አስችለዋል። በበርካታ ሚሊዮን ኢትዮጵያያዊያን በኮምፒተርና በኣይፎን በእጅ ስልኮቻቸው ከመጠቀማቸውም በላይ እድሜና ጤና ለዶ/ር አበራ ሞላ ይሁን ይህ ጽሁፍም የተጻፈው በሳቸው ግኝት በሆነው ፊደልና መክተቢያ ነው። ዶክተሩም የግዕዝን ፊደል ለኦሮሚፋ  በመጠቀም  ቋንቋው  ከአማርኛ  ጋር  ተጓዳኝ  የኢትዮጵያ የስራ አገራዊ ቋንቋ እንዲሆን ምክረ ኃሳብ በቃለምልልሶቻቸውም ኣቅርበዋል።

በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ጊዜ የአንድ ድርጅት ቡድን ንዑስ አመለካከት የያዙ የኦሮሞ ምሁራን ተሰብስበው ከግዕዙ ይልቅ ላቲን ይበጀናል በማለት ግዕዙን ትተው ኦሮሚፋን በቁቤ መክተብ ሲጀምሩ በፊደል መከፋፈል ተጀመረ።

ስለ ግዕዝና ኦሮሚፋ አማርኛ ዊክፔዲያ ስለ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ሥራዎች የተወሰደው ከዚህ በታች እንዳለ ቀርቧል። ይህ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለማያውቁት ለማመልከት ስለ ግዕዝና ኦሮሚፋ የቀረቡ ፲፬ ምሳሌዎች ናቸው። ዋቢዎችና ማያያዣዎች እዚህ አሉ።

ከዶ/ር ኣበራ ሞላ ውኪፒዲያ

(https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%89%A0%E1%88%AB_%E1%88%9E%E1%8 8%8B)

ግዕዝና ኦሮሚፋ ጽሑፍን በግዕዝ ፊደል መጻፍ ያታርፋል።

፩. ኣንድን ገጽ በዓማርኛ ወይም እንግሊዝኛ ጽሑፎች ለመሙላት ዓማርኛውን የበለጠ ጊዜ ይወስድበታል። ምክንያቱም ዓማርኛ ቃላቱን ሲጽፍ ከእንግሊዝኛው በኣንድ ሦስተኛ ግድም በኣነሰ ስፍራ ስለሚያሰፍረው ነው። በእንግሊዝኛ ሦስት ገጾች ለሚያስፈልጉት በዓማርኛው ሁለት ገጾች ገደማ ይበቁታል። ይኸም የሆነበት ግዕዝ ድምጻዊ ፊደል ሲሆን ላቲን ፊደላዊ በመሆኑ ነው። ፪. እንግሊዝኛው የሚጻፈው በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ሲሆን ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ በሁለት መርገጫዎች ስለተከተበ እንግሊዝኛው ብልጫ ነበረው። በቅርቡ ግን በዶ/ር ኣበራ ሞላ ፈጠራ እያንዳንዱን የግዕዝ ቀለም፣ ኣኃዝ፣ ምልክትና ማዜሚያ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ ስለተቻለ ኣከታተቡ ከእንግሊዝኛው ጋር እኩል ሆኗል። (እንግሊዝኛ 47 መርገጫዎች የኣሉትን ኮምፕዩተር ከዝቅ (Shift) መርገጫዎች ጋር በመጠቀም 94 ቀለሞችን ያስከትባል። ግዕዝኤዲት (GeezEdit) የዝቅ መርገጫዎችን ሳይጠቀም ወደ 500 የግዕዝ ቀለሞችን ያስከትባል።) ፫. ከላይ በቀረቡት ምክንያቶች ስፍራዎች ስለሚያስቀንስ ኣንድን ጽሑፍ ወረቀት ላይና በኮምፕዩተሮች ለማቅረብ ዓማርኛው ያታርፋል ማለት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጀምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” በዓማርኛ በ36 መርገጫዎች ተጽፎ 24 ስፍራዎች ይወስዳል። “The quick brown  fox  jumps  over  the  lazy  dog.”  በእንግሊዝኛ  በ37  መርገጫዎች  ተጽፎ  36  ስፍራዎች ይወስዳል። ይህ የእጅ ስልኮችንም (Smartphones) ኣጠቃቀም ይመለከታል። (ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ያካስራል።) ዶክተሩ ሕዝቡን ለማስተማር ከሚጠቀሙበት ኣንዱ ቅምሻ ስለሆነ ቅምሻ ፶፩ በፌስቡክ ለቀረበ ጥያቄ የግዕዝ ፊደል እንደሚያታርፍ መልስ ነበር። ኣንድን ገጽ በዓማርኛ ወይም እንግሊዝኛ ጽሑፎች ለመሙላት

 

ዓማርኛውን የበለጠ ጊዜ ይወስድበታል። ምክንያቱም ዓማርኛ ቃላቱን ሲጽፍ ከእንግሊዝኛው በኣንድ ሦስተኛ ግድም በኣነሰ ስፍራ ስለሚያሰፍረው ነው። በእንግሊዝኛ ሦስት ገጾች ለሚያስፈልጉት በዓማርኛው ሁለት ገጾች ገደማ ይበቁታል። ይኸም የሆነበት ግዕዝ ድምጻዊ ፊደል ሲሆን ላቲን ፊደላዊ በመሆኑ ነው። ዸ፣ ዹ፣ ዺ፣ ዻ፣ ዼ፣ ዽ፣ ዾ እና ዿ የግዕዝ ኦሮሚፋ  ዸ  (dhe) እና እንዚራኖቹ ናቸው።

ታዲያ የአፍሪካ ብቸኛ ጥንታዊ ፊደል የሆነውን የግእዝን ፊደል ጉዳይ አስተውሎ ረጋ ብሎ ለማየት የሰከነ ጊዜ አሁን ነው፣ አልረፈደም።

1ኛ. አፋን ኦሮሞ የራሱን ግእዝ ኦርጅናል ፊደል እየተጠቀመ ከአማርኛ በተጎዳኘ አቻ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ የስራና የህብረት የጋራ መግባብያ  አገራዊ  ቋንቋ  ቢሆንና  በየትምህርት  ቤት  እንደ አንድ የትምህርት አይነት ቢሰጥ ለህዝቦች ትስስርና ሳይኮሎጅያዊ አንድነት ተወዳዳሪ መተኪያ የሌለው አማራጭ መሆኑንና 1ኛ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ይበልጥ እንዲለመድና እንዲስፋፋ እንዲያብብ ያደርጋል።

2ኛ. ወጣቶች የትም ቦታ ሄደው ስራ እንዲያገኙና እንዲሰሩ ያስችላል።

3ኛ. 60% የሚሄነው ኦሮምኛ የማይችለው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀላሉ ፊደሉን ተረድቶ በቶሎ አፋን ኦሮሞን መማር ያስችላል። ለማስታወስ በኦሮምያ ከ 43 ብሄር ብሄረሰቦች አባል የሆኑ  ከ  11-13 ሚሊዪን በላይ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ያልሆነ ህዝብ እንደሚገኝ ያጤኗል።

4ኛ. አፋን ኦሮሞ ተናጋሪውም የሌላውን ቋንቋ በቀላሉ ፊደሉን ተረድቶ በቶሎ መማር ይችላል።

5ኛ. በአጠቃላይ በህዝቡ ውስጥ የእኩልነት የበጎነት ስሜትንና የማህበራዊና የብሄራዊ መግባባትንና እርቅ መንፈስን ይፈጥራል በማለት ጠቃሚ የመፍትሄ ሀሳብ በማቅረብ በአንድነት ይመክራሉ ይዘክራሉ።

አሁን በነባሩ የግእዝ ፊደላችን የሚታተሙ የተሰናዱ ጋዜጣ እና እንዲሁም በመከፈት ሂደት ላይ ያሉ የአፋን ኦሮሞ የቋንቋ ትምህርት ቤት በውጭም በሀገሪቱ ውስጥም ተጠናክረው እንዲሳኩ የሁሉም ድጋፍ ያሻል ይላሉ።

በበኩላቸው እውቅ የስነ-ፅሁፍ ምሁርና የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ (Professer Fikre Tolossa Jigssa) ባደረጉት ምርምርና ማረጋገጫዎች መሰረት የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ በሚለው እኤአ በ 2016 መፅሀፋቸው አፋን ኦሮሞ የራሱን ነባር ፊደል በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራና አገራዊ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ እንዲሆን እንዲህ ይመክራሉ።—

“እኛ ኢትዮጵያውያን ጥንታውያን ሰዎች እንደመሆናችን ከሌሎች አገሮች በጣም ቀድመን ፊደል ብንፈጥር ብዙ አያስገርምም። ስለዚህ ላቲን ራሱ አንዳንድ ፊደሎችን ከኢትዮጵያ ፊደል የተዋሰ ወይም የሰረቀ በመሆኑ ለኦሮሞ ሕዝብ በላቲን ፊደል  መጻፍ  የሚያኮራ  ተግባር  አይደለም። በርግጥ እነሱ ራሳቸው ከኛ እየቀላወጡ እኛ ለምን በአዉሮጳውያን የላቲን ፊደል እንጽፋለን? ይህን ኦሮምኛን በላቲን የመጻፍ ነገር በመጀመሪ ወደ ኢትዮጵያ ያመጡት ራሳቸው አውሮፓውን ሚሽነሪዎች ነበሩ። የኢትዮጵያን ፊደላት ለማጥናት ስለከበዳቸው ወይም  ስለሰነፉ  በራሳቸው በላቲን ፊደል ኦሮምኛን እየከተቡ መጤ ሃይማኖታቸውን መስበክ ጀመሩ።  የዛሬ  45  ዐመት አካባቢ ራሱ ፖለቲከኛ ከመሆኑ ቀደም ሲል በወለጋ  ለነበሩ  አውሮጳውያን  ተመልምሎ ይሰብክላቸው የነበረው ኃይሌ ፊዳ በፖለቲካ ምክንያትና የሃገሩን ክብር በመጥላት  እና በማንቁዋሸሽ ኦሮሞዎች በላቲን እንዲከትቡ ከሚያራምዱት ውስጥ ግንባር-ቀደም ሆነ።

ከኃይሌ ፊዳ በተቃራኒ፣ አርቆ አሳቢና  ሃገሩን  ይወድ  የነበረው  ኦናሲሞስ  ነሲብ  የኦሮሞ ሚሲዮናዊና መምህር በአውሮጳ ተምሮ በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን መጽሐፍ ቅዱስን በግእዝ

 

ፊደል ወደ ኦሮምኛ የተረጎመ እንዲሁም አስቴር ጋኖ ከተባለች አንዲት የኦሮሞ ሴት ጋር ሆኖ የኦሮምኛ መዝገበ-ቃላትን የጻፈና መዝሙራትንና ምሳሌያዊ አባባሎችን የሰበሰበ ሊቅ ነበር። ፓስተር ኦናሲሞስ ነሲብ የተረጎመውን መጽሐፍ ቅዱስ  “መጽሐፈ  ቁልቁሉ”  ብሎታል።  ያ ጠሊቅ ምሑር የግዕዝ ፊደላትን ተጠቅሞ በ19ነኛው ክፍለ-ዘመን ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ በኦሮምኛ ከጻፈ እኛ በ21ኛው ክፍለ-ዘመን እንደሱ የማናደርግበት ምክንያት ምንድነው? የተከበረው ፓስተር እና ጊፍቲ አስቴር ጋኖ የኢትዮጵያ ፊደላት ለኦሮምኛ  ቋንቋ  መጻፊያነት ከላቲኑ ይበልጥ የተመቹና ተስማሚ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የኦሮሞ ምሁራን ከኢትዮጵያውያን ፊደል ይልቅ የላቲን ፊደልን  የመረጡባቸው  ሁለት ምክንያቶች የግእዙ ፊደል ‹‹dh›› ለሚለው የኦሮምኛ ድምጽ መወከያ ምልክት የሌለው መሆኑና ሰባቱ የግእዝ አናባቢዎች አሥር አናባቢዎች ላሉት ለኦሮምኛ ቋንቋ ‹‹የሚመጥኑ ባለመሆናቸው ነው ይባላል። የሚያስገርመው ነገር ቀደም ሲል እንዳልኩት የሱባ ፊደል ግን ‹‹dh›› የሚለውን የኦሮምኛ ድምጽ የሚወክልበት ፊደል ያለው መሆኑና ሥርዓተ-አናባቢዎቹም ቁጥራቸው አሥር መሆኑ ነው። ከላይ በተቀመጠው የሱባ ፊደል ላይ በ‹‹ዲ›› ተራ የቀረበውን ይመልከቱ እስቲ፤

‹‹dh›› ከአሥሩ አናባቢዎች አንፃር የሚነበብባቸው ፊደሎች አሉት። የጥንት ኦሮሞዎችና ጥንታውያን አባቶቻችን እንዲህ አሟልተው መጠቀማቸው የሚያስገርም ነው።

ስለ ኦናሲሞስ ነሲብ እና አስቴር ጋኖ እንደገና  ለመናገር እነዚህ  ሁለቱ ብቻ አይደሉም  በግዕዝ  ፊደል መጽሐፍት የጻፉ። ከአስቴር ጋኖ እና ከኦናሲሞስ በፊትም ኦሮምኛ በግዕዝ ፊደል ለመጻፉ የተመዘገበ መረጃ አለ። ቋንቋው ኦሮምኛ ሆኖ በግዕዝ ፊደል የተጻፈውን አንድ ጥቅል ቀጥሎ ይመልከቱ። የጥቅሉን እድሜ በትክክል ልነግርዎ አልችልም፤ እንደሚያዩት ግን እድሜ- ጠገብ ይመስላል። ቢያንስ አንድ ሺ ዓመት እገምተዋለሁ። በአንድ ጥንታዊ  የኢትዮጵያ  ገዳም  ውስጥ ነው የተገኘው።

ጥንታውያን ኦሮሞ ምሁራን በግዕዝ ፊደል መጻፍ ከቻሉ ልጆቻቸውም ፍላጎቱ ቢኖረን ኖሮ እንዲሁ መጻፍ እንችል ነበር። ቁቤን ያስጀመሩ ምሁራን ያንን ርምጃ  የወሰዱት  የኢትዮጵያ (ሳባዊ) ፊደላት የአማራና የትግሬ ብቻ ስለመሰላቸው በአማራ፣ በአማርኛ እና በግእዝም ላይ በነበራቸው ጥላቻና ቁጣ ተገፋፍተው ነው። ነገር ግን ግለሰቦቹ በዚህ ነጥብ ላይ ፍጹም ተሳስተዋል። ከሁሉ አስቀድሞ የኢትዮጵያ/ሳባዊ ፊደላት ባለቤቶች ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ኦሮሞን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ግልጽ መሆን አለበት። የማንኛውም የአንድ ነገድ የግል ንብረት አይደሉም።

በተጨማሪም እነዚህ ፊደሎች የሚጠቀሙባቸውን ሰዎች ራሳቸውን እንዲገልጹና እርስ በርሳቸው እና ከሌሎችም ጋር እንዲግባቡ ከመርዳት ውጪ ፊደሎቹ በራሳቸው በማንም ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አላደረሱም። በላቲን ፊደል ከመጻፍ ይልቅ በግእዝ ፊደል መጻፍ ለኦሮሞዎች ጠቀሜታው በርካታ ነው።

አንደኛው የግእዝ ፊደላት ከላቲኑ በተሻለ የኦሮሞን የንግግር ድምጾች 99% ይወክላሉ። ስለዚህ ጥቃቅን ማሻሻያዎችን ለምሳሌ በላቲን ፊደል ላይ ለሌሉት የኦሮሞ ድምጾች አናታቸው ላይ ምልክት አድርጎ ኦሮምኛን በግእዝ ለመጻፍ ያመቻል።

ሁለተኛው ደግሞ ኦሮምኛን በኢትዮጵያዊ ፊደላት መጻፍ ጊዜና ገንዘብ ይቆጥባል። በላቲን ሲጻፉ በርካታ ፊደላትን የሚጠይቁ የኦሮምኛ ቃላት በሳባዊ/ግእዝ ሲሆን ግን በጥቂት ፊደላት ይወከላሉ። ለምሳሌ በላቲን ‹‹Adaamaa›› የሚለውና ሰባት ፊደላት የፈጀው ቃል በ‹‹ሳባዊ/ግእዝ›› ሲጻፍ

‹‹አዳማ›› ተብሎ በሦስት ፊደላት ብቻ ሊፃፍ ይችላል። በ‹‹ግዕዝ›› የሚጻፈው አንድ መጽሓፍ በላቲን ሲጻፍ ሁለት እና ከዚያም በላይ ሆኖ አሳታሚውንም አንባቢውንም ላላስፈላጊ ተጨማሪ ወጪ ይዳርጋል ማለት ነው።

 

ሦስተኛው በታሪካዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶች የ‹‹ሳባዊ/ግእዝ›› ፊደላት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በደንብ የሚታወቁና በስፋት የተሰራጩ በመሆናቸው በነሱ መጠቀም መገለልን ለማስቀረትና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ለመገናኘት ሲባል መሆን ያለበት እውነታ ነው።

አራተኛው የ‹‹ሳባዊ/ግእዝ›› ፊደላት ኦሮሞን ጨምሮ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አንጡራ ንብረት ስለሆኑና ከ4000 ዓመታት በፊት የኦሮሞ፣ የአማራና የሌሎችም ኢትዮጵያውያን አባት በሆነው በኢትዮጵ የሚሠራባቸው ስለነበሩ ለኦሮሞ ህዝብ በነዚህ የራሱ በሆኑ የፊደል ቅርሶቹ መጠቀም የራሳቸው ስለሌላቸው ከላቲን ለመዋስ ከተገደዱት በቅኝ ተገዢነት እና በባርነት  ቀንበር  ስር ከነበሩት አፍሪቃውያን አንፃር ሲታይ የሚያኮራ ነው። ኢትዮጵያ ከሰሀራ  በታች  የአሉ  አገሮች የራስዋ የሆነ ልዩና ጥንታዊ ፊደል ያላት ብቸኛ አገር ስለሆነች እና ግእዝ ከ12ቱ የዓለም ዋና ዋና ፊደሎች አንዱ ነው ተብሎ ስለሚገመት የግእዝ ፊደል ኦሮሞውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አፍሪቃውያንን እና ባጠቃላይም ጥቁር ሕዝቦችን የሚያኮራ ትልቅ ቅርስ ነው።

አምስተኛውና የመጨረሻው፤ ከላቲን ይልቅ በግእዝ ፊደል  መጠቀማቸው  ኦሮሞዎችን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን እንደ  እንግዳና  እንደ  ባእድ  ከመታየት  ያድናቸዋል።  ኦሮሞዎች እና ሌሎችም አማርኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን አማርኛን ለጋራ መግባቢያ ቋንቋነት ቢገለገሉበት በርካታ ጠቀሜታዎች ያገኙበታል። የሥራ ቋንቋዋ አማርኛ በሆነባት አገር በኦሮምኛ ወይም በሌላ አካባቢያዊ ያፍ መፍቻ ቋንቋ ብቻ መናገርና መጻፍ ሰፋ ያለ  የሥራ  እድል አያስገኝም። ለምሳሌ የሥራ ቋንቋ የሆነውን አማርኛን ሳይማሩ በቁቤና በኦሮምኛ ብቻ የሰለጠኑ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ  ከክልላቸው ውጪ ሥራ የማገኘት እድል  አጥተው ሲቸገሩ ይታያል። ላይ ላዩን ሲያዩት ጠቃሚ የሚመስል፤ ውስጡን ሲመረምሩት ግን ጎጂ የሆነውን ይህንን አሳሳቢ ሁኔታ ወላጆች ቢገነዘቡትም የማይቆጣጠሩት ሆኖባቸዋል። አሁን አሁን ብልጦቹ አማራ ያልሆኑ ወላጆች እንደሚያደርጉት ኦሮሞዎችም ልጆቻቸው በማናቸውም የኢትዮጵያ ክልል መሥራትና መኖር ይችሉ ዘንድ አማርኛ እንዲማሩላቸው ይፈልጋሉ። ብልጦቹ ልጆቻቸው በድፍን ኢትዮጵያ ተንሰራፍተው መስፈር እና መሥራት እንዲችሉ ተሽቀዳድመው አማርኛ ያስተምሯቸዋል። የትግራይዎቹ መሪዎች አጼ ዮሃንስ እና መለስ ዜናዊም ኢትዮጵያን በቀላሉ ለመግዛት

እንዲመቻቸው በአማርኛ ይናገሩም ይጽፉም ነበር። ትግሬ ባልሆኑት ኢትዮጵያውያን ላይ ትግርኛን ጭነውበት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያን ለመግዛት አስቸጋሪ  በሆነባቸው ነበር። ኦሮሞዎችም አማርኛን  ችላ ሳይሉ መጠቀሚያቸው ለማድረግ ብልሆች መሆን አለባቸው። የአማርኛን ጥቅም የተገነዘቡት ተጋሩዎች ወገኖቻችን በትግርኛና በአማርኛ አቀላጥፈው እንደሚናገሩት ሁሉ የኦሮሞ ልጆችም በኦሮምኛና  በአማርኛ  አፋቸውን  እየፈቱ  ልሳነ-ክልኤ  መሆን  ይችላሉ።”

የሚከተለውን የቁቤ ጽሁፍ ወስደን ከግእዝ እና ከላቲን ፊደል የትኛው ይበልጥ ውጤታማና ብቁ እንደ  ሆነ  እንመለከታለን፡-

“Uummanni Oromoo ilmaan namaa biyya lafaa ኡመኒ ኦሮሞ ኢልማን ነማ ብያ ለፋ

Kanarratti Uumaman kessaa tokkodha biyyi

ከነረቲ ኡመመን ኬሳ ቶኮዳ ብዪ

Chuun nama hin dhiba

ቹን ነመ ሕን ድቡ”

 

ከላይ ከቀረበው ናሙና ውስጥ የተወሰኑ ቃላትን እየጠቀስን የኢትዮጵያው ፊደል ኦሮምኛን ለመጻፍ ከላቲኑ እና ከኢትዮጵያው ፊደል የትኛው ብቁ፣ ቀልጣፋ እና ጊዜ እና ገንዘብ ቆጣቢ እንደሆነ እንይ፤ Uummanni Oromoo ilmaan namaa biyya lafaa

“Uumamaa”  የሚለው  ቃል  በላቲን  ሲጻፍ  7  ሆህያት  ፈጅቷል።  በኢትዮጵያው  ግን  “ኡመማ” ተብሎ  በ3  ፊደላት  ይጻፋል።  “oromoo”  የሚለው  ቃል  በላቲን  6  ሆህያት  አሉት፤  በግዕዝ  ግን “ኦሮሞ”  ተብሎ  በ  3  ሆህያት  ይጻፋል።  “ilmaan”  የሚለው  በላቲን  6  ሆሄያት  አሉት፤  በግዕዝ ግን  አራት  በቂው  ነው።  “namaa፣  biyya፣  lafaa፣”  የሚሉትም  ቃላት  በላቲኑ  እያንዳንዳቸው  5 ሆሄያት ፈጅተዋል። በግዕዙ ቢሆን ግን “ነማ፣ ቢያ፣ ለፋ” ተብለው እያንዳንዳቸወቅ በ 2 ፊደላት ይጻፋሉ።

“ኡመኒ ኦሮሞ ኢልማን ነማ ብያ ለፋ Kanarratt Uumama kessaa tokkodha biyyi የሚሉትን ደግሞ ስናይ “Kanarratti” በላቲን ሲጻፍ 10 ሆሄያት ያስፈልጉታል። በኢትዮጵያው ፊደል በግዕዙ ግን በ 4 ሆሄያት ይጻፋል። “Uumaman” በላቲን 7 ሆሄያት ያስፈልጉታል። በግዕዝ ግን 4 ሆህያት ይበቁታል። “kessaa” የሚለው በላቲን 6 ሆሄዎች ያስፈልጉታል። በራሳችን ፊደል ግን “ኬሳ” ተብሎ  በ2  ፊደላት  ይጻፋል።  “Tokkodha”  እና  “Biyyi”  የሚሉትም  በላቲን  እንደ  ቅደም ተከተላቸው 7 እና 5 ሆህያት ሲኖሯቸው በግዕዝ ግን 3 እና 2 ሆሄዎች ብቻ ነው የሚኖራቸው።

በገጽ ሲታሰብ በላቲን 100 ገጽ የሚፈጅ ጹሁፍ በግዕዝ ግን በ40 ገጽ ሊጻፍ ይችላል። ብዙ ሺ ኮፒ ሲታተም በላቲን ሲሆን አላግባብ የሚባክነውንና በግዕዙ ሲሆን ግን የሚቆጠበውን ስንትና ስንት ቶን ወረቀት አስቡት። ጊዜንና ገንዘብን በተመለከተም እንዲሁ ነው።” አንባቢ ይገምተው።

ስለ ጉዳዩ ለማጠቃለል ለዘለቄታውም መታሰብ አለበት። የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ቁጥር በጣም በርካታ ስለሆነ ካናዳ ውስጥ እንግሊዝኛንና ፈረንሳይኛን የሥራ ቋንቋዎች አድርገው እንደሚሠሩባቸው በኢትዮጵያ ውስጥም ከአማርኛ ጎን ለጎን ኦሮምኛ ሁለተኛው የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ሊታሰብበት እና ጥቅምና ጉዳቱ በተጨባጭ  እየተመዘነ፣ አዋጭነቱ በሳይንሳዊ መንገድ ስለተጠና፤ አማርኛን እንደ  ሁለተኛ  ቋንቋቸው  በተቀበሉ  እንደ ደቡብ ክልል ባሉ ሕዝቦች ላይ ጭነት አለመሆኑም በደንብ እየተረጋገጠ በጥንቃቄ ሊመከርበት ይገባል። ይህ ጉዳይ ባንድ ቀን ጀንበር የሚፈጸም ሣይሆን አዲስ ቋንቋን ለመማር በቂ ጊዜ ስለሚያስፈልግ ዓመታት ሊወስድ ይችላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አሁን እጂግ አስፈላጊና አንገብጋቢ የሆነው የፊደሉ ጉዳይ ነው። ኦሮሞ  ያልሆኑ  የቋንቋው  ተናጋሪዎች  በኦሮምኛ  ለመጻፍ  በላቲን ፊደል እንዲጠቀሙ ሊገደዱ ነው? “ጊዜና ገንዘብ ከሚያባክነው ከላቲኑ ፊደል ይልቅ  ቆጣቢ፣ ቀልጣፋና ምቹ በሆነውና በምናውቀው ባገራችን ፊደል እንጽፋለን” ቢሉ ምን ሊደረጉ  ነው? “በባዕዳን ፊደል የሚጽፉ በቅኝ ገዢዎች ሲገዙ የነበሩና አማራጭ ያልነበራቸው ሕዝቦች ናቸው።     እኛ በጀግኖች አባቶቻችን ደም እና አጥንት ነፃነታችን ተከብሮልን የኖርንና አኩሪ ቅርስ የሆነ የራሳችን  ፊደል  ያለን  ሕዝቦች  እንደነሱ  ልንሆን  አይገባም”  ብለው  ቢቃወሙ  ምን  ሊባሉ  ነው?  ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ባግባቡ መልስ ሊያገኝ እንጂ እንደ ዋዛ ሊታለፍ አይገባም። Page 14 of 14

ከ30 ዓመት ወዲህ የተወለዱና የማስተማሪያ ቋንቋቸውን ኦሮምኛ ብቻ  ባደረጉ  የትምህርት ተቋማት የተማሩ የኦሮሞ ወጣቶች ተጎጂዎች ሆነዋል። እነዚህ ወጣቶች በክልላቸው መንግሥት የተነገራቸውን ተቀብለው በኦሮሚፋ ብቻ በመማር የትምህርት ጊዜያቸውን አባከኑ። በጥሩ ውጤት ከተመረቁ በኋላ ግን በፌዴራሉ የሥራ ቋንቋ ስለማያነቡና ስለማይጽፉ በመላ ኢትዮጵያ በሚገኙት የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም። ያለ በደላቸው ሌሎች ዜጎች የሚያገኙትን  ዕድል የኦሮሞ ልጆች አጡ። የኦሮምያ ክልል መሪዎች ብልሆች ቢሆኑ ኖሮ የሚፈጠረውን ችግር አስቀድመው ገምተው ተጋሩዎቹ እና ሌሎቹም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንዳደረጉት ልጆቻቸው አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋቸው እንዲማሩ አድርገው የሥራ አድላቸውን ባሰፉላቸው ነበር።

 

ባለፈው የፓለቲካ የድንበር ስካር እብደት ዘመን የሀረሪ ወይም ሀደሬ ብሄርረሰብ ግእዝን በመተው ፊደላቸውን በላቲን ለውጠውዋል። ግን የህብረተሰቡን  ፍላጎትና  በዛውም  ጉዳቱን  በማየትና በመገንዘብ እንደገና  ወደ  ግእዝ  ተመልሰው  እየተጠቀሙ  ይገኛሉ።  ስህተትን  ማረም  ትልቅ ማስተዋል ነው። የማይሳሳት ፈፅሞ የማይሰራ ወይም የሞተ ብቻ ነው።

አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደሚታወቀው

1ኛ በ17ተኛው ክፍለ ዘመን በጎንደር ዘመን በተለይም በአፄ ሱስንያስ ጊዜ የቤተመንግስት የአደባባይና የወታደር መነጋገርያ ቋንቋ እንደነበር

2ኛ በዘመነ መሳፍንት በ18ተኛው ክፍለ ዘመን ራስ አሊና በመሳሰሉት ጊዜ በአደባባይ እንደሚነገር

3ኛ በአፄ ምኒሊክ ጊዜም የሰራዊት መነጋገርያ እንደነበር

4ኛ በንጉሰ ነገስት አፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ ከንጉሱ ጋር በአደባባይና በችሎትም ጭምር የኦሮሞ ጀግኖች አርበኞችና የፓርላማ አባላት እነ ደጃች ብዙነሽና እነ የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በኦሮምኛ ይነጋገሩ እንደነበር የህያው ምስክር ምሳሌዎች ናቸው። በዚህም ታሪካዊ ነባርነት መሰረት አፋን ኦሮሞ የእራሱን ነባር የቀድሞ ግዕዝ ፊደል እየተጠቀመ ብዙ ተጠቃሚዎችም ስለአሉት ከአማርኛ ጋር አቻ ተጓዳኝ የስራና የሁሉ መግባብያ ሀገራዊ ቋንቋ የመሆን ብቃትና ግዴታነትን ያስረግጣል።

ዛሬ በሰከነ አእምሮ በረጋ ልቦና ለዘለቄታው በማሰብ ታሪካዊ ቅርስና ሀብት ግእዝ ፊደልን ጉዳይ ለማየትና ለማረም የሰከነና የተደላደለ ጊዜ አሁን ነው። ያኔ ነበር ማለት ከንቱ ነው! አሁንም አልረፈደም እንረዳዳ እንተሳሰብ ሁላችን ኢትጵያያውያን እንድንወያይበት አደራ እላለው አደራ እሰጣለሁ።

ኣፋን ኦሮሞን በላቲን ፊደል መጻፍ የተጀመረው የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያ ለመነጠል ነበር። የመገንጠል ጥያቄ አከተመ ከተባለ አፋን ኦሮሞ ተጓዳኝ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ ይሁን ማለት ተገቢና የሚደገፍ ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን አፋን ኦሮሞን በራሱ ነባር ይግዕዝ ፊደል ኢትዮጵያውያን እንዲጠቀሙበት ሲሆን እንጂ ላቲንን ኣስከትሎ ኣይደለም። ተጓዳኝነቱም ቢሆን ለምርጫ ቀርቦ ሕዝቡ በድምጽ ብልጫ እንዲደግፈው ከሆነ በኋላ ነው። አለበለዚያ አፋን ኦሮሞ ላቲንን እንግቦ ኢትዮጵያን በማዳከም መቀጠል እንጂ ኢትዮጵያዊም ነኝ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ብቁ የሆነ የእራሷ  ፊደል  የአላት  ጥንታዊ  አገርና  ፊደሏንና  ነፃነትዋን ጠብቃ የቆየች ስለሆነች ነው። ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ ከጣላት አንዱ የጥቂት ኦሮሞዎች የመገንጠል ወሬ እንጂ የሌሎች መገንጠል ኣይደለም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ኣደጋ ውስጥ ብትወድቅ ማንም ስለማይደርስልን ተጠያቂው የታወቀ ነው።

ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት ከቀረቡት የሚከተሉት አሉበት።

  1. ፕሮፌሰር ባዬ ይማም ላቲንን በመቃወም በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. የተጻፈ እዚህ አለ።

http://www.ethiopians.com/bayeyima.html  (Ethiopian)  Writing  System

  1. ሰማያዊ ፓርቲ፣ ግዕዝ የአማራ ብሔር ብቻ አይደለም፣ ለኦሮምኛ የግእዝ ፊደል ይሻላል

http://hornaffairs.com/am/2013/05/22/ethiopia-semayawi-party-amhara-oromo/amp/

  1. ከዚህ በታች የሚታየው ደግሞ በኢትዮጵያዊ ፊደል በ16ተኛውና በ17ተኛው ክፍለ ዘመን የተከተበ ጥንታዊ የኦሮምኛ ብራና ነው።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1066297630168549&id=100003649675444

https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%89%A0%E1%88%AB_%E1%88%9E%E1%88

%8B#.E1.8C.8D.E1.8B.95.E1.8B.9D.E1.8A.93_.E1.8A.A6.E1.88.AE.E1.88.9A.E1.8D.8B

  1. ግዕዝና ኦሮሚፋ

ግዕዝ በዶክተር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ለዓማርኛ ተመድበው ከተረፉት ሦስት መርገጫዎች ኣንዱ ለኣፋን ኦሮሞ (Afan Oromo) ሲሆን ሌላው ለትግርኛ ተሰጥቶ የቀረው ለኣገው/ቢለን ሥራ ላይ ውለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ጊዜ የአንድ ድርጅት ኦሮሞ ምሁራን ተሰብስበው ከግዕዙ ይልቅ ላቲን ይበጀናል በማለት ግዕዙን (Ethiopic Oromo syllabary) ስለተዉት የሚከተሉትን መጋራት ሳይጠቅም ኣይቀርም። ፩. ጥንትም ቢሆን ፊደላት በእጅ ጽሑፍ ሲጻፉ ላቲን ከግዕዙ በፍጥነት የተከተበበት ጊዜ ኣልነበረም።

፪. የላቲንና ግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ መሣሪያ ሲከተቡ የሁለቱም ኣጠቃቀሞች እኩል ነበር። በእዚህ ዘዴ የኦሮሚፋ ዓማርኛ መተርጐሚያ በ1850 ግድም በኣቶ ሓብተ ሥላሴ፣ (Lexicon) ፣ መጫፈ ቁልቁሉ በ፲፱፻፺፱ እ.ኤ.ኣ. በቅዱስ ኦነሲሞስ ነሲብ፣ እና ከእዚያም ወዲህ ጋዜጣዎች በግዕዝ ፊደል በኦሮሚፋ ታትመዋል። ቀደም ብሎም በግዕዝ ፊደል በኦሮሚፋ ከቀረቡት መረጃዎች ኣንዱ ጀምስ ብሩስ የወሰደው ጽሑፍ ኣለ። በእጅ የጽሕፈት መሣሪያ ዘመን ታይፕራይተር ዓማርኛን ስለኣልጻፈ ላቲን ብልጫ ነበረው። ፫. እ.ኤ.ኣ. በ1987 በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ የሆነው ግዕዝ ለገበያ ቀርቦ በማተሚያ ቤቶች ፊደላቱ መክተብ ስለተጀመረ

 

ምሁራን ደስ ሊላቸውና ቴክኖሎጅውን ማወቅና ማስተዋወቅ በተገባ ነበር።  ይህ  በኣለመሆኑ እ.ኤ.ኣ. 1992 በፕሮፈሰር ጥላሁን ጋሜታ ከቀረቡት የኣማርኛ የጽሕፈት መኪናን የሚመለከቱት ጊዜ  የኣለፈባቸው  ምክንያቶችም መልሶች ነበሩ።         ስለዚህ በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ፊደላት ሲጻፉ የነበሩት በኮምፕዩተር ስለቀረቡ ቴክኖሎጂው ስለተሻሻለና ስለቀለለ ጉዳዩ ይመለከተናል የኣሉት የኦሮሞ ምሁራን ሊደሰቱ የሚገባ እንጂ ወደ ላቲን የሚያስዞር ኣዲስ ምክንያት ኣልነበረም። በጊዜውም በፕሮፌሰር ባዬ ይማም በዓማርኛ መልስ ቀርቦ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽና ፕሮፌሰር ሳሙኤል ክንዴ ወደ እንግሊዝኛ ተርጕመውታል። ፬. ላቲን የእራሱ ችግሮች የኣሉት ፊደል ነው። በዶክተሩ ፈጠራ እየኣንድኣንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች  መክተብ  ተቻለ።  ላቲን ይኸን እየኣንዳንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች የመክተብ ችሎታ ስለሌለው  ግዕዝን በግዕዝ ፊደል መክተብ ብልጫ ኣገኘ። ስለዚህ ኦሮሚፋን በላቲን ፊደል መክተብ (ቁቤ) መሻሻል ኣይደለም።

፭. ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሚፋው የግዕዝ ፊደል ከሌሎቹ  ጋር  በዶክተሩ  ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ለኣለፉት ፴ ዓመታት በኮምፕዩተር ቀርቦ በኋላም በዩኒኮድ ዕውቅና  ቢያገኝም  ሁሉም ባይሆኑ ኦሮሞዎች ግዕዙን እርግፍ ኣድርገው ጥለው ወደ ላቲኑ ስለዞሩ የተፈጠሩት ችግሮች ቀጥለዋል። ፮. በእጅ የጽሕፈት መሣሪያ ዘመን ታይፕራይተር ኦሮሚፋን ስለኣልጻፈ ላቲን ብልጫ ነበረው። የዶክተሩ ፈጠራ ለእውሸቱ የታይፕራይተር የአማርኛ ነገሮችና ለትክክለኛዎቹ

የማተሚያ ቤቶች ፊደላት ኣጠቃቀሞች ፈውሶች (Breakthrough) ነበር። ስለ ታይፕራይተሩ ድክመት ዶክተሩ እ.ኤ.ኣ. በ1991 ስለኣቀረቡ መሣሪያው ወደ ቁቤ ለመዞር ምክንያት መሆን ኣልነበረበትም። ከእዚያም ወዲህ በኮምፕዩተር የኦሮሚፋው የግዕዝ ፊደል በዶክተሩ መከተብ ችሎታና የተጠቃሚዎች መኖር ግንዛቤ ውስጥ ሳይገቡ ብዙ ዓመታት ባክነዋል። ፯. ቁቤ በላቲን ዋየሎች ከሚጠቀምባቸው በተሻለ ኣፋን ኦሮሞ በግዕዙ ሊጠቀም ይችላል። ለኦሮሚፋ ከላቲኑ ቁቤ የግዕዝ ፊደል ይጠቅማል። ፰. መጽሓፍ ቅዱስ በከፊል እ.ኤ.ኣ. በ1841  በኦሮሞ ቋንቋ በግዕዝ   ፊደል ተጽፏል። እንዲሁም እ.ኤ.ኣ. በ1875 የኦሮሞ ሓዲስ ኪዳን በግዕዝ ፊደል ታትሟል።

፱. በልሳነ ግእዝና በኣፋን ኦሮሞ (ግእዚፊ ኣፋን ኦሮሞቲን – Giiiziifi Afaan Oromootiin) የተዘጋጀው መጽሓፈ ቅዳሴ – ክታበ ቅዳሴ – Kitaaba Qiddaasee መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢሊሌ ሆቴል ተመርቋል። የትርጐማና የኣርትኦት ሥራው 10 ዓመታት የወሰደው ባለ ሦስት ዓምዱ ክታበ ቅዳሴ፦ የመጀመርያው ረድፍ በግእዝ ቋንቋ፣ ሁለተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በግእዝ ፊደል፣ ሦስተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በቁቤ ፊደል ተጽፏል ይላል ሪፖርተር ጋዜጣ።

፲. መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል የግዕዝ ቋንቋ (ግዕዝኛ)፣ ዓማርኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮሚፋ፣ ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከምባታ፣ ወላይታና ጌዴኦ  ይገኙበታል።  ፲፩.  በኣነሰ  የኆኄያት  ግድፈቶች (Spelling / እስፔሊንግ) እና ስፍራዎች (Spaces) ማስከተብ ብልጫዎች የነበረው የግዕዝ ፊደል በዶ/ር ኣበራ ፈጠራ የተነሳ የግዕዝ ፊደል ሓሳብን በኣነሰ ጊዜ (Time)፣ መርገጫዎች (Keystrokes) እና ገበታዎች (Keyboards) በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በማስከተብ ብልጫዎቹ ወደ ኣምስት ዓይነቶች ከፍ ብለዋል። ለምሳሌ ያህል “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጃምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” የሚለውን ዓረፍተ ነገር ላቲን በ36 ቀለሞችና በቁቤ በ45 ቀለሞች ከመክተብ ይልቅ በግዕዝ ፊደል በ24 ቀለሞች መክተብ የተሻለ ነው። ፲፪. የቁቤ ሥርዓት እ.ኤ.ኣ. በ1992 ገደማ የተመሠረተው ኣንዱ ቀለም ኣንድን ድምጽ በመወከል ነው  ተብሏል።  የላቲንም  ሆነ  የቁቤ  ቀለሞች  ኣንድን ድምፅ በኣንድ ቀለም ከሚወክለው የግዕዝ ፊደል ጋር የመወዳደር ችሎታ የላቸውም።

፲፫. ማንኛውንም የኦሮሚፋ ፊደል በሦስት መርገጫዎች መክተብ ነውር ነው። ማንኛውንም የኦሮሚፋ ድምጽ በሦስት መርገጫዎች መክተብ ነውር ነው። ፲፬. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ዓማርኛ የማጥበቂያ ምልክት የለውም የሚሏቸውን ስሕተቶች ቀጥለውበታል። ዓማርኛ መጥበቅ የኣለበትን ቃል ከማይጠብቀው የሚለይበት ሁለት ዘዴዎች ኣሉት። ከእነዚህ ኣንዱ ከሚጠብቀው ቀለም ኣናት

 

በላይ ኣንድ ነጥብ መክተብ ሲሆን ምሳሌውም በ፲፮፻፺ ዓ.ም. ታትሟል። ይኸንንም ኣጠቃቀም ሓዲስ ዓለማየሁ በ“ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሓፋቸው ኣስፋፍተውታል። በኣዲስ ቅርጽ ለኮምፕዩተር እንዲስማማ መጥበቅ ከኣለበት ቀለም ኋላ እንዲከተብ ተደርጎ ማጥበቂያ በዶክተሩ ፓተንትም ውስጥ ኣ.ኤ.ኣ. በ2009 ተጠቅሷል።       ፲፭. የቁቤ ዋየሎች “ኤ”፣ “ኢ”፣ “ኣይ”፣ “ኦ”  እና  “ዩ”  (“a”፣  “e”፣  “i”፣  “o”  አና  “u”)  ስለሆኑ  በቁቤ  “ክታበ”ን  ከ“ኪታባ” የመለየት ችግሮች ኣሉት። ይህ በኣዲስ ፊደልነት የቀረበውንም ይመለከታል።  ግዕዝ  ሰባት እንዚራን ሲኖረው ኦሮሚፋ 10 ያስፈልጉታል የተባለው ትክክል ከኣለመሆኑም ሌላ ቍጥሩን መጨመርም ስለኣላዋጣም ኣልቀጠለም። ፲፮. ይህ ግዕዝና ኦሮሚፋ ሳይንሳዊ ጽሑፍ ስለ ፊደላቱ እንጂ ቋንቋዎቹን ኣይመለከትም። የኦሮሚፋ ቋንቋ መዳከም ስለሌለበት ስለ ፊደል ስንወያይ ሰለኣልፈጠርናቸው ቋንቋና ኦሮሞነት መቀላቀል ሳይንሳዊ ኣይደለም።

፲፯.  እነ  “ሸ”፣  “ቸ”፣  “ኘ”፣  “ዸ”፣  “ጠ”፣  “ጨ”፣  “ጰ”፣  እንዚራኖቹንና  ሌሎች  ቀለሞች የኣሉትን ለኦሮሚፋ የሚያስፈልጉትን ቀለሞች ትቶ እነዚህን ወደ የሌሉት የላቲን ፊደል መዞር ሳይንስ ኣይደለም። ፲፰. የኦሮምኛ ድምጾችንና እርባታዎችን የሚወክል የፊደል ገበታ (ከኣማርኛ ታይፕራይተር፣ ዓረብኛና ላቲን) ለጊዜው የተሻለው ላቲን ነው በማለት በስሕተት የቁቤ ኣጻጻፍ ሥራ ላይ ዋለ። ይህ ለዓማርኛው በኣለመደረጉ ዶክተሩ በመፍትሔው የደረሱለት ለኣፋን ኦሮሞ ጭምር ነው። ምክንያቱም ዓማርኛና ኣፋን ኦሮሞ በትክክለኛው የግዕዝ ፊደል ለብዙ ምዕት ዓመታት ተጠቅመዋል። የጄምስ ብሩስና ለሎች መረጃዎችም ኣሉ። ፲፱. በዶክተሩ ፈጠራዎች ከ”አ”  እና  “ኸ”  መርገጫዎች  ፲፬  የግዕዝ  ቀለሞች  እየተከተቡ  ናቸው።  ፳.  ቁቤ  በ“a”፣  “e”፣ “i”፣  “o”  እና  “u”  በተጠቀመው  ዓይነት  በ“ኣ”፣  “ኤ”፣  “ኢ”፣  “ኦ”  እና  “ኡ”  የግዕዝ ቀለሞች መጠቀም ይችል ነበር።

 

 

(ዋሺንግተን ዲሲ)

Email – asiyefyared@yahoo.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.