በባቡር ፕሮጀክቱ ቁፋሮ አጥር ተደርምሶ የተጐዳችው ተማሪ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

ለቀላል ባቡር ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆጣጠሪያ ክፍል መስመር ለመቅበር በተደረገ ቁፋሮ የአንድ ትምህርት ቤት አጥር ተደርምሶ ከባድ ጉዳት ደርሶባት የነበረችው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ሕይወት አለፈ፡፡

8b611740ee21d364b6514e64ff948281_Lየኃይል መቆጣጠሪያ ክፍሉ የሚገኘው ሳሪስ አካባቢ ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ ሕንፃ አጠገብ ሲሆን፣ ከጀርባው ደግሞ ፍሬሕይወት ሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ይገኛል፡፡ የኤሌክትሪክ መስመሩን ለመቅበር ባለፈው ሐሙስ በኤክስካቫተር ይደረግ በነበረ ቁፋሮ የተደረመሰው የትምህርት ቤቱ አጥር ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው ሁለት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል፣ ጽዮን ንጉሤ የተባለችው ተጠሪ ባለፈው ቅዳሜ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ ቀብሯም የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች፣ የፍሬሕይወት ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት በብሔረ ጽጌ ማርያም ተፈጽሟል፡፡ በደረሰው አደጋና በታዳጊዋ ሕይወት ማለፍ ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡ ለቀብር ማስፈጸሚያ 30 ሺሕ ብር መስጠቱንና መቶ በመቶ የሕይወት ኢንሹራንስ ለቤተሰቦቿ እንደሚከፍልም አስታውቋል፡፡ ጽዮን ንጉሤ ሕይወቷ ያለፈው በተወለደችበት 17ኛ ዓመቷ ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም. መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች በከፍተኛ ሐዘን ራሳቸውን ሲስቱ ተስተውለዋል፡፡

(ፎቶግራፍና ዘገባ ናሆም ተስፋዬ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.