ኪንታሮት ምንድን ነው? የኪንታሮት መነሻ ምክንያቶች

ኪንታሮት በፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ነው። ይህ ችግር ከፍተኛ ህመም እና ስቃይ አለው ነገር ግን የከፋ ህመም ደረጃ ላይ አያደርስም፡፡
በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ሲያብጡ ውስጣዊ ኪንታሮት ይፈጠራል ወይም በፊንጢጣ ቀዳዳዎች አካባቢ ሲያብጡ ደግሞ ውጫዊ ኪንታሮት ይፈጠራል፡፡ ሁለቱም አይነት ኪንታሮቶች በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ሰው ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
በዳሌና ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ የደም ቧንቧዎች ውጥረት ሲበዛባቸው ኪንታሮት ይፈጠራል፡፡ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ ጡንቻዎች በደም ይሞላሉ ይህም የአንጀትና ሆድ ዕቃ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ያመቻል፡፡ ሽንት ቤት ውስጥ ለረጂም ጊዜ ተቀምጠን በምንቆይበት ጊዜ የውጥረት መጨመር በፊንጢጣ ጡንቻዎች ውስጥ ያሉትን የደም ቧንቧዎች እንዲያብጡና እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል ይህም ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

✔የኪንታሮት መነሻ ምክንያቶች

ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰተው በዳሌና ፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ላይ ጫና ሲጨምርባቸው ይፈጠራል፡፡ ግፊት በሚጨምርበት ጊዜ ደም ወደ ስሮቻችን ይገፋና እንዲያብጡ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህ ያበጡ ስሮቻችን በአካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎቻችንን ይለጥጧቸውና ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡
የሚከተሉት ልምዶች የደም ግፊትን በፊንጢጣ አካባቢ በመጨመር ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፦
• ሽንት ቤት ስንቀመጥ በጣም ማማጥና መቻኮል
• ቀጣይነት ያለው ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት በተለይ በሆድና ዳሌ አካባቢ የደም ስሮቻችንን ግፊት በመጨመር ለኪንታሮት ያጋልጠናል፡፡
• እርግዝና እና ወሊድ
በእርግዝና ወቅት የሆርሞኖች ለውጥ ስለሚኖር ወደ ዳሌና አካባቢው የደም ዝውውር እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡ በወሊድ ጊዜ ህፃኑን ገፍቶ ለማውጣት/ሲያምጡ በፊንጢጣ አካባቢ ውጥረት(Pressure) እንዲጨምር ስለሚያደርገው ለኪንታሮት ሊያጋልጣቸው ይችላል፡፡
• የተለያዩ በሽታዎች
ለረጂም ጊዜ የቆየ የልብ እና ጉበት በሽታ ደምን በከርስና ዳሌ አካባቢ
ስለሚገፉት የደም ቧንቧዎች እንዲያብጡ ያደርጋቸዋል፡፡
መልካም ጤንነት!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.