ሰበር ዜና ….ኣባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕረዝዳንት  እና የህወሓት ሊቀወንበር ከስልጣን ተወገዱ – ከኣስገደ ገብረስላሴ 

በተጨማሪ እስከ መጭው የፓርቲው ጉባኤ  ወይዘሮ ኣዜብ መስፍን ታገደች ፣በየነ መኩሩ ከስራ ኣስፈጻሚ ወደ ተራ ማእከላይ ኮሚቴ ወርዶ እንዲቆይ ተደርጓል ። ሌሎችም ኣዲስ ኣለም ባሌማ  በማስጠንቀቅያ ታለፈ ፣ ብርሀነ ኪዳነማርያም (ማራት )  ከስብሰባ ጠፍቶ የት  እንዳለ የማይታወቅ በሌለበት ታግዳል ፣  በርከት ያሉ   ኣማራር ማስጠንቀቅያ  እየተሰጣቸው እንዳለ፣የኣምስት ሳምንትሰብሰባ በድራማ ተዘጋ ። ሂስ ግለሂስ እየቀጠለ እንዳለ ቢታወቅም  ኣሁንም ወጤቱ ኣልባ ነው ።

ይህ ስብሰባ ከጅምሩም ውጤቱ ውሀ ቢወግጡት
እቡጭ    ነው ብለን ነበር ።ኣሁንም ኣባይ ቢወርድ ወይ ኣዜብ መስፍን በጉባኤ ጠቅልላ ልትወገድ ለዝግጅት ቢያግዷት ፣ ሌሎችም 100 % ማእከላይ  ከሚቴ ማስጠንቀቅያ  ቢሰጥ ለኢትዮጱያ ህዝብ በተለይ እጅጉን የጎዱት የትግራይ ህዝብ ምንም ፋይዳ  ኣላገኜም   ።

የህወሓት መሪዎች 26 ኣመታት ሙሉ ሀገራራችን ለማች ኣደገች ተመነደገች  እያሉ ዋሽተው ፣ ህዝባችን  በጸረ ዲሞክራሲ ኣፈና ለረሀብ ለስደት ዳርገው ፣በህዞቦች በቢሄሮች መካከል ዘረኝነት መገዳደል እንዲስፋፋ በማድረግ  ፣ዜጎች በተለይ እቢ ለጭቆና ብለው በሰላማዊ ትግል ለተሰማሩ  ሊሂቃን ኣስረዋል ኣክስመዋል  ፣ካገራቸው ወጥተው የስደት ንሮ እንዲገፉ ተደርገዋል ። ታድያ የርዋንዳ ኢንተር ሀሞዌይ እልቂት እንዲቀጣጠል ያደረጉ የሀገራችን ሀበት  በቢሊዮን  ዶሏርዶሏር የዘረፉ ዘርዘራቸው ቢሌኖሮች እና ሚሊዮኖሮች ኣድርገው ፣   እያሉ ሂስ ኣደረጉ ኣላደረጉ ትርጉም ኣይሰጠንም ።

በመሆኑ   እች ኣገር 26 ኣመታት ያለኣንዳች እስትራተጂ እቅድ መርተናታል ሲሉ የማያፍሩ   ኣሁን ደግሞ   የስልጣን ማውረድ ቢያደርጉም እች ኣገር በምን መንገድ በየተኛው እስትራተጂ ኣገር ትመራለች የሚል መልሲ ስላልሰጡ ኣሁንም የስብሰባው ውጤቱ ባዶኖው ።
ይቀጥላል
ከኣስገደ ገብረስላሴ
መቀለ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.