እባካችሁን ተውንንንንንንን – ሥርጉተ – ሥላሴ

 

ከሥርጉተ – ሥላሴ 28.11.2017 /ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ/

ጎንደርን መሰል መከራን ልቻልህ ብለው ለተሸከሙ የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል …

„ሥጋቸውን መከራ ያስቻሉ፣ በፈጣሪያቸውም አምነው መከራ የተቀበሉ፣ በክፉ ሰዎችም የተነሣ የጎሰቆሉ ፈጣሪያቸውንም የወደዱ ሰዎች ብርና ወርቅን አይወዱም“ (መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 42 ቀጥር 9)

መነሻ

http://www.satenaw.com/amharic/archives/42004

ልጆቻችን ታሪክ የሌለው ሞት እንዲሞቱ አንፈልግም” – „ከመቐለ ተወክለው ጎንደር በነበረው መድረክ የተሳተፉ እናት

ምን አለ ከምወደው ዝምታ ጋር ተርቲሜን ባስነካ። ስለምን ይሆን እምትቆሰቁሱን? … „ይገርማል ይደንቃል የእናትሽ ደም መቅረት“ ይላል ጎንደሬ ሲተርት …. ምን አለ ብትተውን? ተውን እባካችሁ? ምን አለ ዘመን እንደረሳን እርስት ብታደርጉን? ምን አለ ከዕንባችን ጋር ሱባኤችን ብናደርግ?

ሥርጉተ ሥላሴ

አቶ ጸሐፊ እኔም አዳምጨዋለሁ። ህቅታ እዬተናነቀኝ። ሊያስታውከኝ እያቅለሸለሸኝ። „እናቱ የሞተችበትና ወንዝ የወረደችብት እኩል ያለቀሳል“ እንዲሉ …  ነው። ትናንት ደግሞ አቶ አሰገድ ገ/ ሥላሴ ይህውሃቱ አማራን – ኢትዮጵያን – ተዋህዶ ገዳይ ማንፌስቶ ዝክረ ማህበርተኛ „የትግራይ ህዝብ ምንም ፋይዳ አላገኝም“ ብለው የኮለሙትን ደግሞ አነበብኩ። ጉድ ሳይሰማ ነው … ምን ትሁንላችሁ ነው?  ኢትዮጵያ፤ አደግድጎ ኢትዮጵያዊው ሁሉ እኮ ሰጊድ ለከ እያለላችሁ ነው። ምነው ኢትዮጵያ እንደ ብራና ጥቅልል ብላ እነ ባሮም፤ አነ አዋሽም፤ እነ አባይም፤ እነ ነጋሌም፤ እነ ጣናም፤ እነ ላንጋኖም እነ አዲስ አበባም አነ ጋንቤላም አነ አዋሳም፤ አነ ወለጋም በቃ ጥቅልል ብለው እንደ ቦንዳ ጨርቅ ትግራይ ሄደው ይከትሙን? ያው በዛ ካርታ ውስጥ ይሸብለሉን? አንጡራቸው እኮ ከትሟል ያ አይበቃንም? ሌላው ቀርቶ ይህም ማዕረግ፤ ይህም የበላይነት፤ ይህም ሥልጣኔ ሆኖ „“ኑ ወደ ትግራይ በወጣት ቆነጃጅት ተዝናኑ፤ በዚህም ዘርፍ ጥሩ የቱሪዝም ሙቀት አለና ፈታ በሉ እኮም አለ“  … ማፈሪያ። የልጅ ንግድ፤ የባህል ንግድ፤ የወግ ንግድ፤ የትውፊት ንግድ። የነውር ውርርድ … የገመና ፉክክር እንዴት ሴት ወጣት ልጅን እንዲህ ለገብያ ለዛውም ለጸያፍ ሸቀጥ … አበስኩ ገበርኩ። እሰተዚህ ድረስ ነው ሁሉም አይቅርብን … ሂደቱ … እና እነ አቶ አሰገድ የቀራችሁ ነገር የለም። ገመና ሳይቀር ሽሚያ ላይ ነው ተጋሩ ጠረኑ … ፉክክር የተያዘው የተረዘዘው ሁሉ።

ምን እማይሰማ ነገር አለ … ካህኑ ሳይቀር ሥልጣነ ክርስቶስን አሽቀንጥሮ ካድሬነትን ተመስገን ብሎ እዬሰበከ ነው እኮ፤ ተነበርከኩ በኤሉሄ፤ የአሁኑ መንበርከክ አልበቃም መጎንበስንም በሰጊድ ለከ እከሉበት፤ ጆራችሁን ይዛችሁ ቁጭ ብድግ በሉለት ለተጋሩ ለፋሽስቱ እያለ ወጣት የአማራ የተዋህዶ አማንያን መንፈስ ስልብ ለማድረግ ታጥቆ ተነስቷል፤ ካድሬነት ምንም እንደሚል እያጣጣመ ነው እኮ … ዲያቆኑ … በሉት ካህኑ። የሰሞኑ የአማራ ብሄርተነት ምንትሶ ቅብጥርሶ በሚባለው የጉድ መድረክ … ጋብቻም ከፖለቲካ ጥገኝነት ሊመልጥ አልቻለም፤ ያው ነው ልምምጥ ዘመንተኛን።

እትት ይበርዳል …

… ምን አለ አማራ አብሮ ቢዋጋ ቢሞት ተጋሩ አይሙት እንጂ፤ አማራ አብሮ ምን አለ ጉና ላይ ፤ ባድመ ላይ ቢቀበር ለጌቶቹ ለነፈርኦን እስከ ደላቸው፤ በፍቅረ ንዋይ ቁንጣን አስከ አሳያዛቸው ድረስ፤ ምን አለ አማራ ቢዋደቅ በትግራይ ባርነት ተንብርክኮ ኤሉሄ ይበል እንጂ፤ ምን አለ አማራ ቢሰዋ ደሙ የውሻ ነው የንጉሦቹ አይሁን እንጂ .. ይሄ ልግጫ መቼ ነው የሚቆመው …?

አማራ ዛሬም ፍግም ይበል እንደ ለመደበት፤ ህም! ከጓሮው ወገኑን እያስቀበረ፤ ምን አለ አማራ ሁሉንም ይገብር ለሌላ ሲሳይነት ለሌላው ፍሰሃነት – ለሌላው ሰናይነት እስከ እስክስታነት እስከ ዘለለ ድረስ። እም! ለእሱ ኢትዮጵያዊነት ክብሬ – ኩራቴ ማለቱ ብቻ ይበቃዋል። በቃ! ሌላው ጵጵስና – አርበኝነት – የተጋድሎ ታሪክ እሱ ሰማዕት ይሁን በሰማይ ደጅ ያገኘዋል … የቀልዱ ብዛት አታከተ … በረደ እትትትት … ትትትት የ ዕውነት ትነት … ብነት …

እንጃ እኔ እንጃ ይህ ትንታግ እሳት የላሰ የአማራ ወጣት ግን ከእንግዲህ በጅ የሚል አይሆንም። የሚታሰርበት የሃይማኖት ገመድ እንኳን የለም። ሃይማኖት ቤተ እግዚአብሄር ሆነ መስጊዱ ማዕከሉ „ሰው“ ነው። ሰው ከሌለ ሁሉም የለም። እሱ ከሌለ አምልኮተ ዶግማው ወና ነው። የእኔ ጀግናዎች በተለይም የጎጃም አንበሶች የአሻምን ክብር ከለበሱት ቆዩ እኮ። ለአማራነታቸው ተግተው፤ በመንፈሳቸው ጎልብተው እዬሞቱ፤ እየተገበሩ ይገኛሉ የዘመን አውራዎች የበላይ ጌጦች … ባለጥንድ መክሊቶች። አራባራቱ የእኛ እያሉ ነው፤ ወልቃይት የእኛ እያሉ ነው፤ ራዕያ የእኛ እያሉ ነው። አንድም ነገር ቢያክሉ ደስ ይለኛል መተከል የእኛ ቢሉ …  … „ጣና ኬኛም“ ፋሲል የእኛ ፋሲል ኬኛ ብለዋል … ዘመን ጥሩ ነው። ሁሉንም ቢያንስ በመንፈስ መልክ አስያዘው። „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው። በቀለ ገርባ መሪዬ ነው“ ዘመን፤ ትውልድ አሻጋሪ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ገድለኛ የትንግርት ዋርካ ነው። ክስተት። አናባቢ ተነባቢም ተደሞ።ሚስጢር ለግዑፋን እንሆ ሆነ። ተመስገን!

ምን ነበር ያሉት ሥም የለሹ ጸሐፊ የሚያኮሩ ብልህ እናት።“ ወይ መዳህኒተአለም አባቴ? ስንቱን መስቃ እንቻል ይሆን ዘንድሮ? ስንቱንስ ጡር እንሸከም ይሆን ትናንትና ዛሬ? አሁን ከሙታን መንደር በከተመች ከተማ ይህን ያህል ሲደለቅ ሐሤት ሆኖ ሲመስጥ ትእቢት – ሲመሰገን፤ ጉድ በል ጎንደርስ አሁን ነው። ያ የፋቲክ ስብሰባ ስሜት የሚሰጥ፤ ለዛ ያለው ሆኖ ነው ወይንስ ለጨዋታ ማሟያ?  ወይስ ማተበ- ቢስነት? ለነገሩ ከመጤፍ ስላልቆጥርነው፤ ብጣቂም የክብር ቅርጥምጣሚ ስላልሰጠነው አጀንዳ እንዲሆን ለመስጮኽ ታስቦ ነው … በትርጉም መቃናት ከተቻለ …

እንዲህ ዓይኑን በጥሬጨው አሽቶ ከተመጣ ግን … መባል ያለበት ይባላል? ለነገሩ የተገለበጠ ነው ከአንዲት እናት ባህርዳር ላይ „ብሄር አልቦሽ“ ናቸው ልጆቼ ሲሉ አዳምጫለሁ። ትንሽም የተጋሩ ደም ያለባቸውም ይመስላል ገጻቸውን ሳስተውለው፤ የሆነ ሆኖ ተደማጭነት ነበረው። የትውልዱን ዕጣ ያነሱ ስለሆነ የተገባ ነበር፤ አምክንዮውም አቅም ነበረው። ብልህ ሊባሉ፤ አኮሩን ሊባሉ የሚገባቸውስ ይቺ ድንቅ ዬይልማና እና ዴንሳ ነዋሪ ናቸው። የነተጋሩ ችግር በፈለገው ዓይነት መሥፈርት ይሁን ከተበለጡ ቁንጣን- በቁንጣን ነው የሚሆኑት። እኛም አለን ዓይነት ነው … ታስታውሳላችሁ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዲቅሳ የመጀመሪያዋ የአንድ ብሄራዊ ፓርቲ መሪ ስትሆን አረና ደግሞ ወ/ሮ አረጋሽን ይዞ ብቅ ብሎ ነበር። ለምደነዋል። ሥም የለሹ ጸሐፊ …  ምን አለበት ይህነን ለባለቤቶች፤ ለመከረኞች፤ ለመስቃ ለባሾች ዳኝነቱን ቢተውት … ተዚያ ማዶ ተሁኖ ቁስል አይታከምም …  ብቻ እውነትም ጎንደር ተቆርቋሪ ልጅ ባታወጣም፤ ሌላ ታምረኛ ልጅ ፈጣሪ ስለሰጣት እምለስበታለሁ። ጉዳዩ እጅግ በሚመስጥ ሁኔታ የፋሲል መንፈስ ያረፈበት ቅድስና ስለሆነ። ሰፊ ጊዜ ሰጥቼ ወደ ውስጡም እዘልቃለሁ – ከሰሞናቱ። ያው ቅናት መለያው የሆነ ደግሞ ይብተክትክ።

በሌላ በኩል ቀድሞ ነገር የትኛውም ጸሐፊ ነው ከተጋሩ ውጭ „መቀሌን“  „መቐለብሎ የሚያወቀው። ስለዚህ ጸሐፊው አድማጭ ያልነበረውን የተጋሩ የገዳይ ብርአንባር – ግጥግጦሽ በጎንደር ማስጮኽ አሰኝቷቸው ስለሆነ ያው ቤተ ተጋሩ እሱ – በእሱ ነው፤ የሚደንቅ፤ የሚገርም የእኛ የሚባል ጠረኑ ልም ነው ከነተጋሩ .. ሠፈር … ሰውነት የለም። ተፈጥሯዊነት ድርቅ የመታው ነው።

„ልጀቻችን ታሪክ የሌለው ሞት እንዲሞቱ አንፈልግም።“ ወዘተ ወዘተ …. አዬ እናቴ ልጆቾዎት ከሞቱ እኮ ቆዩ። ሲፈጠሩ በሙት መንፈስ ነበር። ሙሶሎኒ በተፈጠረባት ምድሩ የድንጋይ ሐውልቱ ፍርሷል። ያን የድንጋይ ሐውልት የተሸከሙት የርስዎ የማህጸን ፍሬዎች ናቸው። እናትዬ ልጆቸዎት ጣሊያን ቀብሮት የሄደውን ቦንብ አፈንድተው ኢትዮጵያን ባለቤት አልቦሽ አድርገው፤ ፈረካክሰው፤ ሽንሽነው፤ በጎሳ አናውፀው መሳቂያ መሳለቂያ አድርገዋታል። የአፍሪካን ቁንጮ የነበረች ልዕለ ሐገር ከሞሪሺዬስም ከጋናም ያነሰች ናት። ሥነ – ልቦናዋን መጥምጠው አጋድመው እዬጋጡ፤ ከድሆች ተርታ ብቻ ሳይሆን ከፈራሽ ሀገሮች ተርታ እኮ ያሰልፏት የእርስዎ ማህጸን ያፈራቸው ርጉሞች ናቸው። ዛሬ … ዛሬማ ነጮች ሳይቀሩ ኢትዮጵያ ስለ አፈራቻቸው እሾኾች እና ጃርቶች ጉድ እያሉ እኮ ነው። …

ሌላው ደግሞ ምንድን ነበር እትጌ ያሉት „ጠላታችን ድህነት ነው“ እም! ወይንስ ህም! ይባል ይሆን። እኛ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እስከነ ማንፌስቶው ነው ጠላታችን። ይህ የመላ ኢትዮጵያውን ድምጽ ነው። ወያኔ ልቀቀን! በቃህን! ብሄራዊ እድምታ ነው። ከእነ ቅል ቋንቁራህ ብን በልልን ነው የትግሉ እንብርት። ለነገሩ እናንተማ ከድህነት አረንቋ ብቻችሁን ወጥታችሁ ከዓለም ደረጃ ጋር በብልጽግና ስትፎካካሩ ከብራዚል/ ከቻይና ጋር ሆነ እኮ መደባችሁ፤ የዓለሙ የንውይ መ/ቤትም ጨላማ የከተመባትን ያቺን የጥንት የጥዋቷን የትውፊት ከተማን፤ አጉራሻችሁን ጎንደርን ድጣችሁ እናንተኑ በምሽት፤ ብርሃንን እንደ አጋይስተ ዐለሙ አርአም ቦግ ብላችሁ በጨለማ የተከደነችውን ጎንደርን ደግሞ እንደሆነችው አድርጎ የሳትላይት ምስል ዕድሜ ለቴክኖሎጂ እንጂ አያችሁት አይደል። ስንት በእወቀት የበለጸጉ አንቱዎች አፈራችሁ በ26 ዐመታት? ቁጥር ሥፍር አለውን? አሁን ያአለው የትግራይ ሙሁር/ሊቃናት መበራከት ጣሪያ ላይ እኮ ነው። ጥበቃው፤ የህግ ከለላው ቀዳሚው ለትግራይ ዜግነት ለወርቁ ባለደም ነው። እኛ ደግሞ የባርነት ቀንብር ይውረድልን እግዚኦ የነፃነት ያልህ እያልን ነው። ኧረ ከእግዚኦታም በላይ ነው፤ ጠላታችን የማህበረ ፈርኦን፤ የማህበረ – ደራጎን፤ የማህበረ – ሳዖል አገዛዝ እንጂ ድህነት አይደለም። ከርሱ የፈርኦን ማህበር ሲተነፍስ ድህነቱም ደረጃ በደረጃ ይቃለላል። በቅድሚያ መኖሪያ ብኛኝ አፈር ይኑረን፤ አማራ ሀገር – ባዕት አልባ ነው። አማራ ተቆርቋሪ ባለቤት፤ የህግ ጥበቃ የለውም፤ አማራ ከማደጎ ልጅነትም በታች የተንዘገዘገ ነው። ተገንዞ – ተወግዞ – በግዞት የሚገኝ መከረኛ።

ከእናንተ ከሲኦሎች ስንላቀቅ እኛ ስለድህነት እንመክራለን – ነገ። እናንተ ሰለመብራት፤ ስለመንገድ ተጨነቁ የደላችሁ ናችሁ – ዛሬ ። የ26 ዓመት ሙሽሮች። ግን የጫጉላ ጊዜያችሁ መቼ ይሆን የሚጠናቀቀው? ሁልጊዜ ሠርግ ነው የእናንተ ነገር፤ ሁልጊዜ ሽርሽር ነው …  እኛ ግን  … „ጽድቁ ቀርቶብን በወጉ በኮነን“ ነው። ቢያንስ ለባርነቱን ሰላሙን ስጡት„እዬም ሲደላ ነው“ እመቴዋ እማ የእኛ ዘመናይ። የእናንተ አልበቃ ብሎ በመላ ኢትዮጵያ አማራ እንዲሳደድ ነው የተደረገው … እንደ ቤተ – እስራኤላውያን … 2.5 ሚሊዮን ህዝብ ያመናችሁት ነው … ሌላውንም መሬት የቁጥር ተማሪ ከሆነች እሷው ትከውነው …. ምጽዕተ አማራ …

ጥሞና።

እኒህ የተጋሩ እናት ደፋር ከሆኑ¡ የእውነት አርበኛም ከሆኑ¡ ማባጨል ጌጣቸው ካልሆነ¡ መስቃ ድሪያቸው ካልሆነ¡ ካድሬነቱን ትትው ያወቃሉ ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠገዴ፣ ማይጸምሪ፣ አዳርቃይ፣ አዲረመጽ፤ ራያ፣ አሁን ደግሞ ግጨው ነገ ደግሞ ጎንደር ከተማ፤ የእነሱ እንዳልሆነ። ልጆቻቸው ለጉልበት ሥራ ነበር ወደ እኛ ይመጡ የነበሩት ወይንም ተፈጥሮ ጥሪኝኑ ስትሸሽግባቸው ቀን ለማሳለፍ። ስለምን ስለዛ አልተነፈሱም? የክፉ ቀናችን አጉራሻችን ጎንደር አስከፋነሽ በደልንሽ ይቅር በይን ስለምን – እኮ ስለምን አላሉም? ጎንደር የእነሱ ትዕቢት አልናፈቀውም እኮ። ጎንደር የእነሱን ከጫካ ገንባሌ ወደ ገበርዲን እና ፖርሳ ያደረጉትን ሽግግር ማዬትን አላሰኘውም? አይናፈቀውም የተጋሩ ትንፋሽ። ስለምን ሰለሚከረፋው ወራራ አልተሟገቱም „አኩሪዋ¡“ እናት? ስለምን ስለዛ የመሬት፤ የተራራ፤ የቅርስ፤ የተፈጥሮ ሃብት ስርቆት ግብግብ አላደረጋቸውም? መቼም ሌባ ልጅ አንገት የሚደፉበት እንጂ በአደባባይ ላይ ተወጥቶ የሚፎክሩበት፤ የሚያቅራሩበት፤ እንዲህ ቡራ ከረዩ፤ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚያሰኝ አይደለም። ለነገሩ በእንቁላሉ ያልተቀጣ … ልጅ ህይወቱ ስርቆት ናት። ነፍሱ እምነት ማጉደል ናት።

 

ግን ስለምን የሰው አንጡራ ሃብት ዘረፋ አልጠዘጠዛቸውም እኒህ እናት? ቀድሞ ነገር ፍቅር – ሰላም እኮ ጠበንጃ ደግኖ አይደለም። ጉባኤው ላይ እኮ ታዳሚው ጠበንጃ እና ትዕቢት ነበሩ። አይታያቸውም። የኦሮሞ ወገኖቹን አማራ እንዴት እንደተቀበለ አያስተውሉም? የኦሮሞ አባቶች አባ ገዳዎች እኮ ሲመጡ ብትራቸውን ይዘው ነበር የመጡት። በጠመንጃ በሠራዊት ታጅብው አልነበረም የመጡት። ጥጌ አንተ ነህ አምኘህ መጥቻለሁ፤ ያሻህ አድርገኝ ብለው እኮ ባዶ እጃቸውን ነበር የመጡት። ፋቲክን ተከተልኝ አላሉም። ምነው እነኛ የኦሮሞ አዛውንታት የታማኝነት አድባሮች ወደ ርሰተ ጉልታቸው መሠረት ወደ ሆነው ጎንደር ተመው በነበረ ታዩት ነበር ሐሤቱን። ፍቅር ልብስ አይደለም። ፍቅር ደም ነው። ፍቅር ውጪያዊ በኮስሞቲክ የሚሸበብ አይደለም የውስጥ ማንነት ነው።

የጎንደሩ ጉባውኤው አኮ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የጡንቻ ሙሉ ፓኬት ነበር። ትንፋሽ ተወጥሮ፣ መንፈስ ተንጠልጥሎ፣ የስጋት ግጥግጦሽ ፍርሃት ማጫ የተማታበት። ህዝቡን ማማን አልቻሉም እነ ተጋሩ ያመኑት ጠበንጃቸውን ብቻ ነበር። ለነገሩ ታማኝነትን የማያውቅ እንዴት ሌላውን ሊያምን ይችላል? ጎንደርን ሳያምኑት ነበር ወደ ጎንደር የሄዱት። ያደረጓትን ስለሚያውቁ። ይልቅ ቀደም ብዬም እንደ ተናገርኩት ጎንደር ከሚገኙት ተጋሩዎች ጋር ጥሩ ሃርሞኒ አድርጋችኋዋል። ሁለመናውን የሚቆጣጠሩት እነሱው አይደሉ … „እሚሉሽን ባልሰማሽ“ ነው … ንገሩን ባይ …

 

እናቴ እባከዎትን ጡር ይፍሩ። ቢያንስ ፈጣሪን?

 

ምን ጎንደር በዘመነ የትግሬ መሳፍንት ያልሆነው፤ ያልተዋረደው፤ ያለጣው ነገር አለና። ሥጋውስ አልቋል ለአጥነቱ ሰላም በሰጣችሁት። 40 አመታት ሙሉ ያለማቋረጥ የዋይታ ቤተኛ ነው – ጎንደር። የክርስቶስን ስቃይ – ህማማት የተቀበለ። የታቦር ተራራ። እናትዬ አሁንስ ተሸክሟችሁ ያለው እኮ ቻዩ፤ ሆደ ሰፊው፤ ታጋሹ፤ ሰብዕዊው ጎንደር አይደለምን? እህልና እውሃው ማን ሆነ እና?

 

ስንት ጊዜ ሰው ይገረማል? 

ስንት ወገን የወልቃይት የጠገዴ አባወራ እና እማ ወራ፤ ወጣትና ጉብል የአፈር ስንቅ የሆኑት፤ የካቴና እራት የሆኑት፤ የባዶ ስድስት ቤተኞች፤ በጢስ ታፍነው፤ በሳት ተንገብግበው ስንት ወገኖቻችን ነው ያለቁት? 40 ዓመት ሙሉ ጎንደር በትግራይ ምክንያት ጥቁር እንደለበሰች ነው። ጎንደር ከነተጋሩ ሥርዓት ውጪ ጠላት የላትም። ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሆነባት በሞቷ ይደነሳል፤ ይጨፈራል፤ የጎንደር ህዝብ እያበላ – እያጠጣ፤ ተጎነብሶ ያገለግላል ለጌቶቹ¡ …. ለጎንደር እርቁ ቀርቶበት ባርነቱ ፈቅዳችሁለት ሰላሙን በሰጣችሁት። ህጻናትን በባሩድ ባልቀቀላችሁ። ልጆቹን ልቅም አድርጋችሁ ወስዳችሁ ማዕከላዊ አሳሩን የክርስቶስን ስቃይ ታሳዩትአላችሁ፤ የቀሩትን በምግብ ብክልት በዬተገኙበት ቦታ ሁሉ ታድነው ለአፈር ስንቅ ሆነዋል፤ ሌሎቹ ደግሞ በቢላዋ ጫካ ገድላችሁ ትጥላላችሁ? ኧረ የእናትውስ የጉድ ነው! ከሰው ተፈጠራችሁ ለማለት ይከብዳል። ብናኝ ፈርሃ-እግዚአብሄር የነሳችሁ የጉድ ቁንጮዎች፤ አያድርግብኝ እንጅ እኔ እናንተን ብሆን እግሬን ከመቀሌ አላነሳትም ነበር። በፍጹም በህልሜ እንኳን አላስበውም። በምን የእውነት አቅም።  በዬትኛው የስብዕዊነት አቅም?… በዬትኛው የሃይማኖት ጥንካሬ? እንዴት ይሆናል? ቀራንዮ ጎለጎታ ያደረጋችሁትን መሬት ላይ እርቅ …. አቤት ያንት ያለህ ነው … እፍረተ ቢሶች … አሁን ሽም ሽር እየሰማን ነው። ለእኛ ያው ነው። ከዝንጀሮ ቆንጆ ነው። አንዱ ፈርዖን ቢነቀል ሌላዋን ፈርዖኒት ተክቶ ነው። ሄሮድስ ሲሞቱ አባይ የሄሮድስነቱን ቦታ ተኩ … ለእናንተ ይመቻችሁ። ለእኛ ግን የጨለማ ሽግሽጎሽ ነው። የመከራ ጥርኝ ነው። ከጭራቅ ጭራቅ ማማረጥ አይቻልም። አዲሱ ቶን ቀለማሙን ኢትዮጵያዊነት የሙጥኝ ማለት እንደሚሆን እንውቃለን፤ ሥማችሁንም እሰከመቀዬር ልትሄዱ ትችላላችሁ፤ መርዝ መርዝነቱን አይለቅም በፈለገው ውሃ ውስጥ ቢከዘን። ኢትዮጵያዊነት በውስጣችሁ አልነበረም የለምም።

 

ግፍና እግዚኦታው።

 

በትግራይ ዘመንተኞች የተወረሩት የጎንደር እና የወሎ ግዛቶች አስተዳደሩ ተከድኖ ይብሰል፤ እዬዳሁ ለመኖርም ፈቃድ የለም። አማርኛ ቋንቋ ተናጋራችሁ/ አማርኛ ዘፍን ሰማችሁ ተብለው ምን ፍዳ ላይ እንዳሉ አያውቁም „እኔ ኮራሁባቸው የተባሉት እናት?“ ሎቱ ስባሃት ለጸሐፊው። የመንፈስ እከክ ይሉታል ይህን መሰል ግብዝ ግንዛቤ። ለመሆኑ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ የሚወለዱ የወልቃይት እና ጠገዴ እናት ልጆቻቸው አባት አልቦሽ ሆነው ሴቶች ተገደው እዬተደፈሩ፤ የሥነ – ልቦና ጥቃት እዬተፈጸመባቸው፤ በጉስቁል በእናቱ ሥም የሚጠራ ስንት ልጅ ነው ጎንደር  ያላት? ይህ በፋሽስት ጣሊያንስ ሆኗልን? „አማረ ነኝ“ ስላለ ብቻ እኮ ነው፤ ለዚህ ቨትረ ሥልጣን ደሙን ገብሮ ያበቃን ወንድም ኮ/ደመቀ ዘውዴ አስራችሁ እያንገላታችሁት ያለው? ልጆቹን ስንቅ አልባ አድርጋችሁ በጭንቀት ማጥ ውስጥ በስጋት የከተታችሁት። የእናንተዎች ደግሞ በኮንፒተር ተደግፈው ይማራሉ – ሰላምን እየጨለጡ። ለመሆኑ ማተብ አላችሁን? ለመሆኑ ሃይማኖት አላችሁን? ለመሆኑ ይሉንታ አላችሁን? ለመሆኑ በዚህ ባልደረቀ የደም ጉዞ ስለነገ ስላልተወለዱት የትግራይ ህጻናት አስባችሁ ታውቃላችሁ? በሰላም ጥያቄ ያቀረቡትን፤ እነ አቶ አታላይ ዛፌ፤ እነ ንግሥት ይርጋ፤ እነ  መብራቱ ጌታሁን፤ እነ አቶ ጌታሁን አደመ ሰረጸ፤ እነ አቶ አለነ ሻማ በላይ፤ እነ አቶ ነጋ ባንተይሁን ምንድን ናቸው ሰዎች አይደሉንም? ማነው አሁን ወንዶችን እስር ቤት እዬሰለበ/ እያንኮላሸ ልክ እንደ እንሰሳ፤ ሴቶችን እዬደፈረ ያም አልበቃ ብሎ ጥፍር ሴት እስረኛ የሚነቅል የእርስዎ የማህጸን ፍሬ አይደሉምን? ንግሥት ይርጋ የእርስዎ ልጅ አይደለችምን? ቀን ያሳለፈለዎት የልጅ ልጅ ናት ንግሥት ይርጋ ማለት  ስለምን ስለ እሷ አይሟገቱም? ወንዶችስ ወንድሞቾዎት አይደሉንም? …

ሐምሌ አቦዬ የ12ኛ ክፍል ፈተና ይሰጥ በነበረበት ወቅት ምንም የማያውቁ ህጻናት ተዘግቶባቸው በቦንብ ሲቃጣሉ እኒህ አናት የት እንዲያው የት ነበሩ? ባለሐሤቱ ጸሐፊ ለዚህ መልስ አለዎትን? ይህ ስለሆነ ነው ጸሐፊው ፍንክክን ብለው ጉሮ ወሸባዬ የሚሉት። አበሰኩ ገበርኩ …. አድነኝ ከእንዲህ ዓይነት ማተበ ቢስነት … ሆነ ኢ-ሰብአዊነት …. ከሰደበኝ የነገረኝ … ከገደለን የነማህበረ ሳዖል ዘመን የርስዎ ዕይታ ይሸታል – ይከረፋልም።

አዬ እናትነት አንጀቴ ስንት አዬን እቴ¡  

መቼስ ባህርዳር ላይ አንድ የጠገበ ተጋሩ 50 ወጣቶችን በደቂቃ ሲመትራቸው በባሩድ የት ነበሩ?። ጎንደር የተዘረፈው – ተዘርፎ፤ የተጋፈፈው – ተጋፎ፤ የተሸነሸነው – ተሸንሽኖ ሥን – ልቦናን ለመተርተር መቀሌ ላይ የተከፈተው የቅማንት ቢሮስ ስለሱስ ምነው አንድ አላሉም እኒህ የተጋሩ ቅምጥልጥል?

የአንባ ጊዮርጊስ እናት የሳቸው ዘሮች ጭፍጨፋ አልበቃ ብሎ፤ ከሱዳን በመጣ ወታደር እንደዛ ፍጹም በሚዘገነን አኳኋዋን እነዛ ታዳጊ ህጻናት ሲጨፈጨፉ፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ የተሰደደችበትን የመከራ ጊዜ ያሳስባል። እነዛ ከእድፍ፤ የተጣፈ ልብስ ያልተላቀቁት የአንባ ጊዮርጊስ እናቶች ወንድ ህጻናት ልጆቻቸውን ይዘው ጫካ ሲሰደዱ፤ ሬቻ ላይ በቀን 600 ወገን ሲረግፍ? ኧረ ጉድ ነው ለመሆኑ እኒህ „የሚኮሩ እናት¡“ ተብለው መወድሱ የተነበበላቸው የተጋሩ እናት ዓይናቸውስ መንፈሳቸውስ የት ላይ ነበር?  ወለጋ ላይ ወ/ሮ ታደሉ ልጃቸው ተገድሎ በሬሳው ላይ ተቀመጥው ሲደበደቡ ከቶ እኒህ እናት የትኛው ፕላኔት ላይ ነበሩ? ያን ጊዜ እኮ ሴት ነኝ የሚል ሁሉ መድፉን ጥሶ አደባባይ መውጣት ነበረበት፤ ሌላ ቦታ አይቻልም የትግራይ እናቶች ግን ቢያንስ ቤተ እግዚአብሄር ላይ ተገናኝተው ከአምላካቸው ጋር በአደባባይ በመከሩ? ማይ ጣይቱ ለይስሙላ ነበርን? ግን አልሆነም።

ከታላቋ ትግራይ ከልዕልት ቀዬ በስተቀር ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቀፍድዳ ሴት ልጆች ሲደፈሩ፤ የህዝብ አንጡራ ሃብት በዘመቻ ሲጋዝ፤ የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች የበቀል የጽዋ ማወራራጃ ሲሆኑ ግን እነኝህ ሴቶች/እናቶች ለማለት አቅም ይኖራል? በደል ይረሳል ወይንስ በዕጥፍ ያርሳል? አዎን የጎንደሩ ጉባኤ በእጥፍ በግፍ ያረሰን ነበር ።

እነኛ 20 ሺህ  የአማራ ወጣት በአንድ ወር ውስጥ ካለ በቂ መጠለያ – ህክምና – ምግብ አሳሩን ሲከፍል፤ ት/ቤቱ ሁሉ እስር ቤት ሲሆን፤ ማታ ማታ በዱላ ብዛት ያ ቀንበጥ እዬሞተ የትሜና ሲቀበር፤ የጎንደር ቅዳሜ ገብያን ያህል የህዝብ ሃብት፤ ጉሮሮ፤ የሀገር ቅርስ ከትግራይ ተነስተው ቤንዚንና ክብሬት ይዘው ሲቃጠል – ሲነድ፤ ሺዎች መጠጊያ አልባ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በግፍ ድርብ ሲታሰሩ – ሲማገዱ፤ እስር ቤቱን የሞላው እኮ የስሜን ጎንደር ወጣት – ጎልማሳ – አዛውንታት እኮ ናቸው። አሳዳጁ – ዳኛው – ፈራጁ – ህጉ –  ገዳዩ – ደብዳቢው – ጥፍር አፍላቂው – ደፋሪው – መስቃ ተናጋሪው – አንኮላሺው ደግሞ ትግሬ ነው። ምነው ፈጣሪ በሠራው ፍጡር መከራ ባንጨፍር? ኧ ትግራይ ላይ ያለኸው ማተብ የት ይሆን ያለኸው? ኧረ ትግራይ ላይ ያለኸው ሽበት ተጠዬቅ? ኧረ ትግራይ ላይ ያለኸው ገዳመ ደብረ ዳሞ ተጠዬቅ?

ጎንደር እኮ ከቀበሌ ገበሬ ማህበር በታች ናት። የሪጅን አቅም ለሆን እንኳን የተሳናት።

https://www.youtube.com/watch?v=iyEjZ0bGM94

ኢትዮ-ቴሌኮም በጎንደር ከተማ ሪጅን ባለማቋቋሙ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም፡-ደንበኞች“

 

ባለጊዜዋ እመቤት ….

አያወቁም የጋይንት ገበሬ እናንተን ቁሞ እንደሚያበላ። አያውቅም የሰቲት ሁመራ ካሽ ክሮፕ መዋለ ንዋይ ለትግራይ ልማት እንደሚውል። ዛሬ እኮ የአዲግራት አጠቃላይ ሆስፒታል ለህሙማን በነፃ ነው ህክምና የሚያደርገው። ጠበቃ ለሌላቸው ደግሞ ከዬትኛውም የትግራይ ቦታ ይሁን ጠበቃ ቀጥሮ ይከራከርላቸዋል። አዲግራት የኢትዮጵያዊቷ ሲዊዝ ናት። „#EBC የአዲግራት ዩንቨርስቲ በሚሰጠው ነፃ የህግና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን 25.11.2017“ ዘግቦት አዳምጫለሁ። በማን አንጡራ ሐብት ነው ይህን ያህል መንጠባረሩ? ጋንቤላ ላይ መሬት ላይ ነጠላቸውን አንጥፈው ህሙማን ባሊህ ባይ የላቸውም። የሆስፒታሉ ግንባታውም ቁሞ ቀር ሆኗል። ሃብቱ የጋንቤላ ተዝርፎ ግን ትግራይ ላይ ለዛውም አዲግራት ነፃ የህክምና አገልግሎት ለሁሉም በሽተኞች ይሰጣል። ይህም ብቻ ሳይሆን ሆስፒታሉ ጠበቃ አቁሞ ለባለጉዳዮች ይከራከርላቸዋል። ጠበቃ ማቆም ለማይችሉ የታላቋ ትግራይ ዜጎቹ። ያው ያለው ዜግነት ትግራዊነት አይደል።

አባቶችን የሃይማኖት እንኳን አያዩም የሚደርስባቸው ፍዳን አይሰሙም? እንደዚህ ዘመን የሃይማኖት አባቶቻችን የእስልምናም ሆነ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተሰደው ያውቃሉን? አሁን እስር ቤት የሚደርሰው የደናግሉ ስቃይ – ምን አደረጉ እነኝህ የዋልድባ ቅዱሳን። ምን ሠሩ? በጸለዩ – ግርማ ሌሊቱንና የቀን ሐሩሩን ታግሰው በሰገዱ፤ በፆሙ ስለእኛ ስለምን ይሆን የሚሰቃዩት? ስለምን እኮ ስለምን? ኧረ እግዜሩን ፍሩ ዕምነቱ ካለ? ኧረ አላህን ፍሩ ሃይማኖቱ ካለ ወጣቱን አታንገላቱት – ለህክምና አብቁት? ሊሆን የሚገባው እኮ አካኪ ሳይሆን ጥጋባችሁን ተግ አድርጋችሁ፤ ስለግፈኛች ልጆቻችሁ ሱባኤ ነበር ልትይዙ የሚገባው። እግዚአብሄርን ለምኑት በጽናት የሰው ልብ፤ የእናትነት አንጀት እንዲሰጣችሁ። ስለ ሰብዐዊነት ግድ እንዲሰጣችሁ። ስለ ተፈጥራዊነት እንድታስቡበት። ለምኑት የሁሉን ፈጣሪ … እናትነት ጸጋችሁ እኮ በኗል ወርቅና ጨርቅ ላይ ነው ነግሦ ያለው …

እርግጥ ነው የአዲግራት ዩንቨርስቲ በሚሰጠው ነፃ የህግና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን ሰብዕዊነቱን ወድጀዋለሁ፤ ይህ ሰብዕዊነት ሌሎች ኢትዮጵያ መሬቶች ላይ ቤተ ተጋሩ ይህን ያደርጋሉ ወይ ስለሚለው ግን … ዳሽ ነው። መሃንነቱ በቀረላቸው? የተሳሰተ መዳህኒት መሰጠቱ በቀረላቸው፤ መግደሉ ብቻ ሳይሆን ግድያው ከወቀሳ፤ ከዘለፋ፤ ከማንቋሸሽ ጋር መሆኑ በታገሰላቸው አብሶ አማራን

የአማራ እናት ዛሬ ከብት የሚያቆም ጉብል ከብት ጠባቂ የላትም – መክናለች፤ ወንዱም ተንኮላሽታል፤ ለመታጨት የደረሰች፤ ማጫ የሚማታላት ባለ ጋሜና ታሪ የላትም። አልሰሙም አማራ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄደው ጥናት በዓይን ህመም/በትራኮማ/፤ በትምህርት፤ በጤና አጠባበቅ በሁሉም ዘርፍ የመጨረሻው ስለመሆኑ። እስር ቤቱን እኮ በአማራ እና በኦሮሞ የተሞላ ነው።

አዎን ሞት ለአማራ ድህንት ለትግራይ። አዎን መከራ ለአማራ ብሥራት ለትግራይ። ስቃይ ለአማራ – ትፍስህት ለትግራይ። መሰደድ ለአማራ ፋሲካ ለትግራይ። ቆላማው የአማረ ቦታ በወባ በሽታ እንዲያልቅ ተፈርዶበት የወባ ማጥፊያ ድርጅት ተዘግቶ ወደ ትግራይ ተዛውሯል። ኧረ ስንቱ … ሰማይና መሬት ቢቀጣጣል የነገረ ትግራይን ናዚዝም ተጽፎ … ተጽፎ… ተነግሮ… ተነግሮ አያልቅም  ….

የዛሬ ዓመት 20 ዓመት ዕድሜ ያሰቆጠረ የወያኔ ተፎካካሪ የተጋሩ አንድ ድርጅት ለፊርማ መጀመሪያ በ6 ቁጥር ተጀምሮ 50 እንኳን ፊርማ ውጪ ሐገር ማሰባሰበብ አልቻለም። 30 ላይ ነበር የቆመው። ሰሞኑን በታዬው የመቀሌ የአረና ሰላማዊ ሰልፍም 6 ነበሩ።  የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል „ሐገርን እግዚአብሄር ካልጠበቀ ወታደሮች /ሠራዊቱ በከንቱ ይደክማሉ“ ። ዛሬም እንደ ትናንቱ ማላገጥ፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ ማባጫል፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ መሳላቅ፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ ማዳዳጥ የነገን እንጃ ነው ….

አቤት! የተከሳሾቹ ብዛት ….

ሌላው የገረመኝ በዚህ ተከሳሾቹ ኢሳት እና አርቲስት ታማኝ በዬነ መሆናቸው ነው። ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ። ቀድሞ ነገር አቶ ታማኝ ብሄር ወይንስ ጎሳ አለውን? የለውም። እሱ እኮ ብሄርአልቦሽ ነው። እንዲያውም በአማራ ተጋድሎ ሰሞናት አንድ የሥጋ ዘመዱ ነኝ፤ ላልኖር ወይንም ልታሰር እችላለሁ አልገባውም ታማኝ እያለ የሚጽፍ ወንድም ነበር። አቶ ታማኝ አይደለም አማራነቱን ጎንደሬነቱ እራሱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ የሚያወቀው ፈጣሪ ነው። ሁለት ጊዜ እዚህ ሲዊዝ መጥቶ አይቸዋለሁ። እኔ ያዬሁት ጎንደሬዎች ወደ እሱ ሄደው ግንባራቸውን ሲያስመቱ እንጂ እሱ ጎንደሬያዊ ስሜቱ ሆነ ፍላጎቱ ኖሮት ቀርቦ ችግራችሁ ምንድን ነው? እንዴት ናችሁ? ሲል አላዬሁትም። ሌላው ቀርቶ አርቲስት ታማኝ በዬነ ሌሎች የአካባቢያቸውን ሰው ደግፈው፤ እረድተውና ከብክብክብ የማውጣት አቅማቸው አንቱ ነው። እሱ ደግሞ ከዚህ ውጪ ነው። ለዚህም ነው ከእሱ ውጪ ሌላ ዓዬነ – ገብ ጎንደሬ  ከእሱ ከእራሱ ውጪ ልናይ የማንችለው። አርቲስት ታማኝ በዬነ ልዩ የሆነ የጎንደር ጌጥ አይደለም። ይልቁንም አርቲስት ታማኝ የኢትዮጵያና የኢሳት ጌጥ ነው ቢባል የተሻለ ይመስለኛል። ብቻውን ነው ሲሮጥ የነበረው። የመንፈስ ተተኪዎችን በዙሪያው በተጠና እና በታቀደ ሁኔታ የማሰባሰብ አቅም የለውም። አጥር አልሠራም። የተጨነቀበትም አይመስልም። ይህ በእሱ ብቻ ሳይሆን በዛች ባልታደለችው ጎንደር የተፈጠሩ እትብተኞች ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የአማራ ሊቃናትም ችግርም ነው። አቦ አባ ዱላ ገመዳ ደግሞ መሠረታቸውን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ የማይቻለውን ችለው ሲያደርጉ እንደ ነበረ የፖለቲካ ተንታኙና ጋዜጠኛው አቶ ኤርምያስ ለገሰ በዝርዝር አስረድቶናል። ልብ ያላቸው ይህን ይሠራሉ። ሁሉንም ሳይጎዱ – ሁሉንም ሳያስከፉ።

የሆነ ሆኖ አርቲስት ታማኝ በዬነ አማራነቱንም ቢሆን የሚያውቀው እሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በተጨማሪም አማራ ነኝ ማለትም ሆነ አማራ ነኝ አለማለትም መብት ነው። ምንድ ነው ያለው ጋዜጠኛ በፈቃዱ ማንነቴ „ድህነት“ ነው አይደለም ያለው። ሐገሬም የተወልድኩባት „አዲስ አበባ“ ናት ነበር ያለው ከብራና ራዲዮ ጋር በተለዬ ሁኔታ ከዬኔታ ሙሉቀን ጋር በነበረው የውይይት ቆይታ። መብት ነው ሆንኩኝ አይደለሁም ለማለት። ወለጋ መወለድ ኦሮሞ እንደማያደርግ ሁሉ ጎንደር መወለድ በራሱ አማራ ሊያደርግ አይችልም። ይህ ሁሉም አካባቢ ያለ አምክንዮ ነው። አርቲስት ታማኝ በዬነ „አማራ ነኝ“ ብሎም አያውቅም። አማራ ነኝ ሳይል የአማራ ተጋድሎ አነሳሽ፤ አነቃቂ፤ አቀንቃኝ ሆነ ቤተኛም ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ሎጅኩ አያስኬድም። አልደከመበትም። በአማራ ተጋድሎ የነበረውን ዝንባሌ ቅርበትም በትጋት ስንከታተለው ነበር። እጅግ አሳሳቢ እና ውጋት የበዛበት ተጋድሎ ስለነበረ። በሚዲያ አቅም እንኳን አንድም ቀን „የአማራ ተጋድሎ“ በሥሙ ተጠርቶ ሲዘገብ አልተደመጠም – ልጅ ታማኝ በደከመለት፤ በተንከራተተለት ሚዲያ። „ባለቤቱን ካልፈሩ አጥሩን አይነቀንቁም“ እንደሚባለው ሆኖ። ይልቅ „መሬት /እስራኤል/፤ SBS /አውስትርልያ/ ፤ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ /አሜሪካ/፤ በሚገርም ሁኔታ በትጋትና በባለቤትነት፤ በተቆርቋሪነት ፍጹም በሆነ ስሜት ህብር ራዲዮ /አሜሪካ/ የድምጻችን ይሰማ BBN ኢትዮ ዩቱብም በሚገባ የእኔ ብለው ታታሪዎችን፤ ይመለከታቸዋል ያሉትን ሁሉ አወያይተዋል። አመክንዮውንም አብሰለውታል። ለአማራ ተጋድሎም በቂ ዕውቅና ከአክብሮት ጋር ሰጥተውታል። እነኝህ ሚደያዎች አመክንዮውን አልይህ ብለው አልገፈተሩትም። ወቅቱን አድምጠዋል። ከወቅት ጋር አልተላፉም። ከድህረ ገጽም ሳተናው እና ዘሃበሻ ብቻ ነበሩ የአማራ ተጋድሎ ደጋፊዎቹ፤ በቁርጥ ቀኑ እና በፈተናው የተገኙት፤ ለተጋድሎውም ዕወቅና በመስጠት አረገድ ሆነ ለዛች መከረኛ ማገዶዋ ጎንደር በመንፈስ የአይዞሽን ስንቅ የቀለቡት። ይመስገኑ – ይከበሩ። ታሪክ የማይረሳው ረቂቅ የተግባር ሰናይ ከዋኞች ናቸው እና። ጸሐፊዎችንም አላገለሉንም።

በዛን ጊዜ እልሁ፤ ጥቃቱ አይደለም ሰውን ቁሞ የሚሄደውን የሞተ ሬሳ የሚቀሰቅስ ነበር የግለቱ ክርፋት። እኔ እራሴ እልሁ እና ቁጭቱ ነበር ድብቅ ብዬ ከተቀመጥኩበት ገዳሜ ወጥቼ የምለውን ያልኩት። ዘገርድያን ሳይቀር ጎንደርን ሚዲያ የሌላት ከተማ ሲል ነበር የዘገበው። ይህ አይቆጠቁጥም? ይህ አያንገበግብም? ከዚህም በተጨማሪ ጎንደር ላይ በነበረው ገድል ዙሪያ የነበረው ሙግትም ቀላል አልነበረም። ሰበር ዜናዎች እና ዕድምታውም አስጨናቂ ነበር። በአውሮፕላን የሚያስጨፈጭፍ ነበር። ስለሆነም በጽኑ እንከታተለው ነበር። ለመሆኑ እኛ የገፋነውን መከራ ማን ጥቁር ቀሚሱን ሊለብስልን ኖሯል? ጎንደር የነበራት አንድ ዓይነ እሱ ብቻ ስለነበረ ሁሉንም በተደሞ አዳምጠናል። ነገር ግን የአርቲስት ታማኝ በዬነ መንፈሱ ከአማራ ተጋድሎ ጋር የተቆራኘ አልነበረም „ከነፃነት ሃይል“ ጋር እንጂ። ተጋድሎው በግራ ቀኝ በወጀብ ሲናጥ ሁነኛ አልነበረውም። ተቆርቋሪ አልነበረውም። ታታሪ ወጣቶች የነበረባቸው ፍረጃም ይህ ነው አይባልም። እንኳንስ አማራና ትግሬ እያለ ፕሮፖጋንዳ ሊነዛ ቀርቶ። እሱ በደከመበት ኢሳት እኮ ነው „የትግራይ ድምጽ“ ያለው ትግርኛ ተናጋሪዎች የሥራ ዕድል እና የታወቂነት ማክዳም እንደ ተጠበቀ ሆኖ። „ለተራበ ትቼ ለጠገበ አዝናለሁ“ እንዲሉ … እንጂ የአማራ ድምጽ አይደለም ኢሳት ያለው። አርቲስት ታማኝ በዬነ መረጃ የማሰበሳብ ጥሩ ተስጥዖ ስላለው እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊ አጀንዳዎች ወይንም ዘውገዎች ነገረ የአማራ ጉዳይ በእሱ ህሊና ያላው ቦታ በ1/80 ደረጃ ያያቸው ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እንደተጠበቁ ሆነው። ሲሰራማ እንደሌሎቹ እሞገትላቸው እንደ ነበሩት ወገኖቼ ጉዲት እስክባል ድረስ ተማግጄለታለሁ … እሱ ከቁጥር ባያስገባውም ከመጤፍ ባይቆጥረውም።

ብቻ በምን ሂሳብ ተዘዋውሮ በጥናት በተመሠረተ፣ ዳታዊ መረጃን በከወነ፤ እጅግ በሚመስጥ ቅንነትና ፖለቲካዊ ጨዋነት አማራዊ ጉዳትን ውስጡ ካደረገ፤ ከቦታው እዬተገኘ ፍዳውን የእኔ ካለ ከዬኔታ ሙሉቀን ጋር „አማራ ነኝ“ ያለለው አርቲስት ታማኝን ለአማራ ተጋድሎ ቅርበት ተመዛዝኖ እንደታዬ አላውቅም። በፍጹም ሁኔታ የተሳሳተ መረጃ ነው። የተሳሰተ ግንዘቤም ነው። ድፍን የጎንደር  ህዝብ እኮ ያውቀዋል ውጪም ያለው ሀገር ውስጥም አለው። በሚገባ በተደሞ ታዝበነዋል። ከዚህ በላይ መሄድ አልፈልግም።

ኢሳትም እንደ አቶ ታማኝ ብሄር አልቦሽ ነው። እንዲያውም ድምጽ አልቦሽ ናችሁ ተብሎ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በኢሳት የተጋሩ ድምጽ አለ፤ የፕ/ኢሳያስ አፈወርቂ ካቢኔ ልዩ ሃይል ወይንም የኮማንድ ፖስት ብቸኛው አለኝታ ቲፒዴኤም እንዲሁ ድምጽ ነበረው፤ እንጃ አሁን ይቀጠል አይቀጥል አላውቅም። ስለዚህ ሁለቱም አርቲስት ታማኝ በዬነ ይሁን ኢሳት ሊወቀሱ፤ ሊነቀሱ ከቶውንም አይገባም በነገረ አማራ የተጋድሎ አመክንዮ። ሥማቸውም በአማራ ዙሪያ ሊነሳ በፍጹም አይገባም። በሌላ በኩልም ለአማራ ተጋድሎ በእነሱ የጥረት ውጤት ነው ሊባል አይችልም። በአዎንታዊም ሆነ በአልታዊ ጎኑ ሁለቱንም ማንሳት አግባብነት በፍጹም ሁኔታ የለውም። „ላም ባልወለበት ኩበት ለቀማ ነው“  የሚሆነው። ለነገሩ  የአማራ ተጋድሎ ታታሪዎች ሲታሠሩ ክሳቸው በግንቦት ሰባቶች/ ሻብያዎች አይደል የሚባሉት። ግን ጭብጡ አይገናኝም። ግንቦት7 ሆነ ሻብያ ለአማራ ስሜት ቅርብ አይደሉም። በፍጹም። ጅማ ላይ፣ ባሌ ላይ፣ ሐረር ላይ፣ አርሲ ላይ፣ አፋር ላይ፣ የሚታሠሩ ወገኖች ግንቦት / ሻብያ አይባሉም፤ በእነዛ አካባቢዎችም ግንቦት 7ም አለሁኝ – ተከሰትኩ ብሎ አያውቅም። ስለምን ግንቦት ሰባት የአማራ ድርጅት ተደርጎ እንደሚወስድ ግራ ያጋባል። ግንቦት 7 የትኛውንም ብሄረስብ አይወክልም፤ ከንባታውን ይሁን አፋሩን … እኔ እንደሚሰማኝ ብሄር አልባ ነው … ለጉራጌውም ግድ አይሰጠውም፤ እንደ ሌሎች ብሄረሰቦች ነው የሚያው “ለዴሞክራሲ“ ነው አጀንዳው።

የሆነ ሆኖ ያለው ዕውነት አማራ በዞጉ እንዲደራጅም አይሹም። የአማራ ሊቃናትም ቢሆኑ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ናቸው። አይፈልጉትም „አማራ ነኝ“ ብሎ መውጣቱንም ሆነ መደራጀቱን። የአማራ ሊቃናት አማራ ነኝ ብሎ መውጣት የሚያሳፍራቸው እና በእጅጉም የሚጸዬፉት አመክንዮ ነው። ያፍሩበታል። ይሸሹታል። ቁሞ የሚጠብቅ አምክንዮ እንደሌለ እንኳን ሊገነዘቡት አልቻሉም። ሥጋ ተሸሽቶ የሚቻል ከሆነ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። ጥግም ከተገኘ። አሁን የምንአዬው የወ/ሮ ሄሮዳዳይ አዜብ መስፍን ችግርም ይሄው ነው። አሁን ንጥሯን የትግራይ ልጅ አምጥተው ቁብ ያደርጓታል እነ ተጋሩ። ምን አልባትም አዲስ የሴት ጠ/ሚር። እስከ አሁነም ትክን እያሉ ነበር ወ/ሮ አዜብን ተሸክመው የኖሩት። ወ/ሮ አዜብ ደግሞ የትግራይ አለቅላቂ ነበሩ። እነ ተጋሩ አለቅላቂነታቸውን ቢቀበሉትም የእነሱ ደም እንዳልሆኑ ያወቃሉ – ጠንቅቀው። የተውሶ ልብስ ተመልሶ እንደሚሄድም አላስተዋሉትም የመሪነት ባልህልሟ ድሃዋ¡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን። እንቦጩስ በሳቸው ህልም ላይ ነው የተመመው … እንቦጭ አሉ።

ቤተሰባዊ ተወልጅነትን መተላለፍ ጦሱ ለልጅ ነው የሚተርፈው። ሌላው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከሚታወቀው ዞጉ በላይ በህዝብ አደባባይ ተጨማሪ የዚህም ዘር አባል ነኝ በማለት አቅም ማከማቸት ወይንም ጥግ ሲሻ አማራ ግን ዞጉን አንደ አባ ጨጓሬ ይፈራዋል። እራስን ማግለል፤ አራስን መጸዬፍ የት ሊያደርስ እንደሚችል ባይታወቅም፤ ራስን ሳያከብሩ ሌላውን አከብራለሁ ወይንም አቀርባለሁ ማለትም የሚቻል አይሆንም። ራስን በሰብዕዊነት መንፈስ ውስጥ ባለቤት ሳያድርጉ የሰብዕዊ መብት አቀንቃኝ መሆንም አይቻልም። ይሄ የሃቅ እንክብል ነው። የሆነ ሆኖ በአማራው አማራዊ ተጋድሎ ውስጥ ያሉት ጎርበጥባጣ ጉዳዮች የተጋሩ ብቸኛው አውራ ህልም ነው። ሄሮድስ መለስ ዜናዊ እኮ „አማራ ሳይሆን ሃሳቡ ብቻ ነው መወከል ያለበት“ ያሉት ይህም ማለት የአማራ ሥጋና – ደም ውህደት ሳይሆን አማራ በስማ በለው ነው ድርጅቱ መዋቀር ያለበት ነበር ያሉት። አድርገውታልም። ይህን መሰል እጅግ ሽንክና ማሽንክ የሆነ ቲወሪ ነው የነበራቸው ሄሮድሱ። ሁሉም ክተት ያለው በዚህ መንፈስ ውስጥ ነው ከሊቅ እሰከ ደቂቅ። የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የሴራ ፖለቲካ ሰለባ victim ነው የተሆነው። ስለሆነም አማራ ባሊህ አልባ፤ ተቆርቋሪ አልባ ዛሬ ካለው የመከራ ዳጥ ውስጥ ይገኛል። የሁሉም ሕልም ከሊቅ እስከ ደቂቅ አማራ በሥጋና – በደሙ ነፍሱ እረፍት እንድታገኝ አይፈልግም። ባልተወለዱት የምህረት ብጣቂ ለማኝ እንዲሆን ነው የሚታሰበው። እሱም ከተሳካ ጆሮ በብድር ከተገኘ።

አማራው ጀርመን ከዓለም የመዳህኒት ፈላስፋነት ጉብ ያደረጋት ሚስጢር አልገባውም። የአውሮፓ ሊቃናትም ሆነ ሥልጣኔያቸው መሠረታቸው ከአማራ የቀደመ ፍልስፍና የተነሳ ስለመሆኑም አልተረጎሙትም። አማራነት በሥጋ ሲአልፉ እንኳን ሳይፈርሱ ለዘመናት ለመቀጠል የፈጣሪና የመሬት ቃልኪዳን የተፈጸመበት ስለመሆኑም አላስተዋሉትም። በውነቱ አማራነት አንገት የሚደፉበት፤ ወይንም ቅስም እንኩት የሚልበት ተዋራጅነት አይደለም። አማራነት ሙሉ ሰብዕና ከብቁ አቅም ጋር የተላበሰ ማንነት ነው። ሊወደድ ሊከበር የእኔ ሊባል የሚገባ ንጡር ማንነት ነው አማራነት። የቤተሰቤ የደም ንጥረን ነገር ስለምን እክደዋለሁ – እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ቆሜ እዬሄድኩኝ? አማራ ነኝ በማለቴ ከቶ ምን ሊቀርብኝ? የክብር – የሹመት – የሽልማት – የመወድስ ልቅምቃሚ እና ልቅላቂ … ቀልድ።

ይልቅ የሚፈራውም ይሄው አቅም ሃሳቡ ሳይሆን እኔ አለሁ ብሎ ሥጋና ደሙ ከነክህሎቱ አማራው ከወጣ፤ ጥገኛ ሆኖ ወይንም ተሽብልሎ ሳይሆን እራሱን ችሎ ቢወጣ ገጣሚውን የፖለቲካ መመጣጠን ምስሉን ስለሚቀይረው ነው። ቅኔው ተዚህ ላይ ነው። ስለሆነም አማራው እራሱን ሆኖ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ሽፋን ውስጥ ተደቁሶ፤ ወይንም ተጨፍልቆ ወይንም ተፈጭቶ ወይንም ደቆ እሱ ቀልጦ ሌላውን እንዲያበራ ነው የሚፈለገው … „በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበት“ እንዲሉ … የሰሞናቱ አቶ አለምነህ የሚባሉት ሆነ የነዲያቆን ዳንኤል ስብከተ ካቴናም ይሄው ነበር፤ የዶር ተስፋዬ ደመላሽ አዝለኝ ቅኖናም እንደተጠበቀ ሆኖ … ምስለ ግዕባዕቱ ሄሮድስ መለስን የእርቃን ደጀሰላም የሚሳለም  እንዲሆን የታሰበ ነው። እርቃኑን የቆመ ፖለቲካ ….

ቀመሩ መከራን ወደ ውጪ መላክ እና ማስመጣት Export and Import የማይችል ከመሆኑ ላይ ነው።

ስለ እኔ እራህብ እኔው እንጂ ሌላው ሰው ሊያውቅልኝ በፍጹም አይችልም። ራህብ በስማ በለው አይሆንም። ፍጥረተ ነገሩ የመከራ ምንጩ፤ አነሳሹ ከውስጥ ከቁስል/ ከመግል ነው የሚነሳው። ችግር – መከራ – ስቃይ – ፍዳ – ጭቆና ቀመሩ መከራን ወደ ውጪ በመላክ እና በማስመጣት Export and Import አይቻልም። ከውስጥ ነው የሚመነጨው። በሌላ በኩል ከሞት ጋር፤ ከስቃይ ጋር፤ ከመገለል ጋር፤ ከፍዳ ጋር፤ የሚኖረው ህዝብ ለሰቃዩ – ለሃዘኑ – ለመካራው ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ልክም – ደንበርም – መጠንም መስፈሪያም – ያልተሰራለት የናዚዊ የፋሽስታዊ የተጋሩ አገዛዝ አይደለም የአማራን ተጋድሎ ከዚያም ያለፈ ሌላ ዕድምታ ቢኖረው በፍጹም ሁኔታ የሚገርም አይደለም። እዛ የተፈጠሩ ሴቶች እንደ ተጋሩ በደል እና ልክ ማጣት እንደ ዩዲት ቢሆኑ አይደንቅም። እስከ ደንበር መጨረሻው ድረስ ቢሄዱ ሊገርምም አይገባም። በደሉ ልክ የለውም። ጎንደርን እኮ ሶርያ ነው እነ ተጋሩ ያአደረጓት። ይህን ጉድ ተሸክመው ከነባይረሳቸው ነው እርቀ ሰላም የሚሉት እንፋቲክ ከሙት ጋር እርቅ ማደረግ የሚቻል ከሆነ …

የሰማይ ጦሮ …

ሁለመናን ይህን ያህል መግረፍ በውነቱ የሰማይ ጦር/ጦሮም ያሳዝዛል። አባይ ለግብጽ ጎንደር ለትግራይ አንድ ነው ዕድምታው። እነ ተጋሩ ምን አላችው እና ነው ቁልቋል፤ አሞሌ እና አሸዋ ብቻ ነው ያላቸው። አሞሌም ለከብት ነው። ከብቱ ይኑር አይኑር እሚውቁት እነሱው ናቸው፤ ለዛውም ካለ ግጦሽ መሬት አልባ ከብት ከረባ። አሽዋም ለመሬት ነው፤ ቢበዛ ለሸንበቆ። መቼስ ቁልቋል ተብልቶ አይዋል አይታዳር … „በማን ላይ ቁመሽ እግዜርን ታሚያለሽ“ አይሆንም፤ አብረን „ተቀበርን ሲባል¡“  ለእንሱ ተንስዑ ጎንደር ጠፋች። በበቀል ፋስ ጎንደር ተፈለጠች። በትዕቢት ገጀሞ ጎንደር ተከተፈች። እመቤቲቱ …. ግፍ ፍሩ! ልዕልቲቱ ጥሩ ይፍሩ!

ደግሞ ገራሚው ስብከተ ኢትዮጵያዊነት ነው። ሙሽራዋ ትግራይ ተሸልማ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እዬታረደ፤ እንዲህ እዬተሰቀለ፤ እንዲህ እዬተደበደበ፤ እንዲህ እዬተዘረፈ፤ እንዲህ እዬተቀጠቀጣ … ኢትዮጵያዊነት የለም። ትውልድ በጭካኔ እዬተራደ፤ አያምርም እነ ተጋሩ ስለ ኢትዮጵያዊነት ባለሟል ለመሆን። አቅም የላቸውም። ከእነሱስ አፋር ጋንቤላ ቢል ያምርባቸዋል። ተፈታተሽን አኮ። የትግራይ ነፃ አውጪ ብሎ መሥርቶ ኢትዮጵያዊነት? ኢትዮጵያ ካለወደብ መቅረቷ ብቻ ሳይሆን ለሱዳን የተሰጠው የመሬት ጸጋ በታሪክ ዬትኛውም ሐገርና ህዝብ መንግሥት አድርጎት አያውቅም። ይህ የ21ኛው ክ/ዘመን አሳፈሪ ክስተት ነው። እኒህ እናት ስለምን ለሱዳን ሽልማት በቀረበው መሬት ላይ እንዲህ ግብግብ አይሉም – ስለ አንድነት ከሆነ፤ ስለ ልዑላዊነት ከሆነ ተቆርቋሪንቱ … ግርንቢጦች። እዛ ደንበር ላይ ያሉት ህፃናት በአጋዚና በሱዳን ወታደሮች እንደሚመነጠሩ አልሰሙም? ጆሮ ሊገዛ ቢችል ገዝቼ ብልክላቸው እንዴት ደስ ባለኝ ነበር …. ለ እኒህ ዘመናይት …

አንድነት በኣዋጅ አይመጣም፤ ፍቅር በፕሮፖጋንዳ አይመጣም፤ ደም በመስቃ ንግግር፤ በመታበይ አይድርቅም። በፍጹም። አማራ ዘሩን እንዲፈልስ፤ አማራ የተሰረዘ ማህበረሰብ እንዲሆን ተግቶ ተጋሩ እዬሠራ ነው። ደግሞም ሆኖለታል። „የትግራይ ተራሮች የአማራ መቃብር“  አይደል ዘፈኑስ ትንቢቱስ።  … ትግራይ አኮ ዛሬ የሚወዳደራት አንድም ከተማ የለም። ቆሻሻ የማይጣልባት፤ ሲጋራ የማይጤስባት፤ የፖለቲካ እሰረኛ የሌለባት፤ እስረኛ የወንጀሉም ቢሆን ቀን በነፃ ተለቀው ካሻቸው ሄደው ማታ ለአዳር ብቻ እስር ቤቱ የተሻለ ኑሮ ስላለው በፈቃዳቸው ይመለሳሉ። ትግራይ ከቻይና ከብራዚል ተርታ ተሰልፋለች፤ ዓለምዐቀፍ ተሸላሚም ናት። … ምርጥ ዜጎች በዬትኛውም ቦታ ዳኛ፣ መሪ፣ ፈራጅ፣ የኢኮኖሚ ሊቅ፤ የወታደራዊ ሊቅ፤ የውጭ ግንኙነት ኤክስፐርት፤ የድህነነት ልሂቅ፤ የማህበራዊ ኑሮ አንበል፤ የጥበብ ዓይኖች ምን የቀረ ነገር አለና። በሁሉም ዘርፍ ጥላ ከለላ ተሠርቷል። ትግርይ ላይ የመንፈስ ልቅና ከሙሉ አገልግሎት ጋር፤ በመላ ኢትዮጵያ የሚጋዘው ንበረት ደግሞ ሌላው የዲታነት መሰላል …

እናቱ ወ/ሮዋ  ምንም ማንም ሳይደርስባችሁ የተረገጋውን የ26 ዓመት የጫጉላ ጊዜ እዬኮመኮማችሁ ነው። ልጆቻችሁን በሰላም እያስተማራችሁ፤ ውጪ እየላካችሁ፤ እዬዳራችሁ – እዬኳላችሁ የልጅ ልጅ እያያችሁ … ውብ የመዝናኛ ወቅት ላይ ናችሁ። በሁሉም የሙያ ዘርፍ ብቁ ልጆችን ትግራይ አፍርታለች። በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ከመጨረሳው የሃብት ጣሪያ የእናንተ ዘሮች ናቸው። ነጭ ለባሾች። ዘማናዮች፤ ስልጡኖች … ይደክማል …

የዕዳ ቋት

ለታላቋ ትግራይ ህልም የኢትዮጵያ ልጅ ሱማሌ ሄዶ ይሰዋል። በሌላ በኩል ያልተገባ ቅራኔ ለትውልድ በዕዳ ተቀማጭ ሆኗል። ይህ ደግሞ ዘለግ ያለው የዕዳ ቋት ነው። በማናቸውም አህጉራዊ ዓለምአቀፋዊ የሥራ ዕድሎች ሁሉ ቤተ – ተጋሩ ተኮፍሶበታል። ኢትዮጵያማ ምን አጥንቷ ቀርቶ ለአንድ ሳምንት የሚሆን እንኳን ጥሪት አልቦሽ ናት። እናማ እነ ናዚ ፋሽቶች … እፈሩ …. ልጅ አያወጣም። ቁሞ፤ ደረት ነፍቶ የሚያናግር አንድም የሰብዕ ተፈጥሮ የለም። ይህ ደግሞ ዘር አይበቅልም። መሬቱስ ያው  ጠፍ ነው፤ ደግሞ የአሁኑ ግፍ መንታ ወላዱን ማህጸኑን ጠፍ እንዳያደርገው፤ ወደ ራሳችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁን ውቀሱ … ድንጋይ ተሸክማችሁ ጎንደርን ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያን ይቅርታ ብትለምኑ እንኳን እግዜሩ የሚፈቅድላችሁ ከሆነ …

ይከወን መሰል ስለ እኒህ የተጋሩ ወ/ሮ መቼስ ሲሄዱ ማደር ነው … የግፉ ሸክም … የመስቃው ራዲዮ … ሲደመጥ …

… እናንተ በልዩ ጥበቃ ሥር ሆናችሁ 26 ዓመት ሙሉ የልባችሁን አድርሳችኋል። ሰርጉ – ልደቱ – የትምህርት ዕድሉ – ግንባታው – ታዋቂው ሰው/ ተፈላጊው ፍጡር መሆኑን – ሹመቱን  – የዓመቱ ምርጥነት ሽልማቱን – ጥሪቱ ምን የስለት/ ብርቅዬ ልጆች አይደላችሁ። ሌላው ደግሞ እዬሞተም – እዬተገደለም በጉልበቱ ተንበርክኮ ስለ እናንተ ብልጽግና ፍሰሃና ሐሤት ይደክማል። ይማስናል። ዛሬ ጋብቻው፤ አበልጅነቱ እኮ ጡፏል ከእናንተው ጋር። ልብሱ … ቁንዳላው ያው የእናንተ ጠረን መሆኑ እራሱ ይለፍ ያሰጣል። እዬን እኮ ነው ዲያቆናት ሥልጣነ ክህነትን አንዘግዝገው ጥለው ካድሬ ለዛውም የፋሽስት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሲሆኑ … ተዋህዶን አጠፋለሁ ብሎ ከተነሳ አራዊት ጋር በሃሳብ አብረው መጪ ሲሉ …

እስቲ አማራ በተባለው ክልል ማን እንደሚመራው ከልባችሁ ሆናችሁ አስተውሉት፤ ከንባታው፤ ሃድያው፤ ትግሬው፤ ኤርትራዊው ጉራጌው፤ ወላይታው ነው … በትግራይስ? መልስ አላችሁን? ትግሬ ያልሆነ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የጎሳ ፓርቲ  አባል ይሆናል? ኢትዮጵያ ላይስ መከላከያው፤ ደህነነቱ፤ ፖሊሱ፤ አዬር ሃይሉ፤ አዬር መንገዱ፤ ኢኮኖሚው፤ ኢፈርቱ ምን ያልተወረረ ነገር አለ? ቄራ ሳይቀር እስቲ …. እፈሩ …. ለነገሩ ይሉኝታ የሚባል አልሠራላችሁም …

  • ዶር. ተክለብርሃናን አብርሃ በአዲግራት ዩንቨርስቲ መምህር ናቸው። እንደ ዶሩ. ገለጻ በአዲግራት ዩንቨርስቲ 31 ሃኪሞች እና 6 የስፔሻሊስት እንዲሁም ተጨማሪ ባለሙያዎችን አክሎ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት በነጻ እንደሚሰጥ ገልጠዋል። በዩቨርስቲዎች የሚሰጠው ክህምና በምርጥ ሃኪሞች የተደገፈ ሲሆን፤ በሽተኞችም በአገልግሎቱ እንደረኩ ገልጸዋል። ዩንቨርሲቲው ከዚህ በተጨማሪ ምርጥ ጠበቃ አቁሞ የህግ አገልግሎት ለማያገኘው ወገኑ የህግ ድጋፍ በነጻ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልፆልል። ዶር ዘይድ ነጋሽ የዩንቨርስቲው አስተዳዳሪ አንደገለጹትም ዩንቨርስቲው በማናቸው ሴክተሮች የተሟላ እግዛና ድጋፍ በማደረግ ላይ እንደሆኑም አክለው አብራርተዋል። ዜናው በ25.11.2017 በነበረው የኢቢኤስ የቴሌቪዥን ስርጭት። /#EBC የአዲግራት ዩንቨርስቲ በሚሰጠው ነፃ የህግና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን …. 2.ደቂቃ ከ2. ሰከንድ /

 

ግፍ የማይፈራ „ሰው“ ህሊና አልተሠራለትም!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.