የዐረና ሊቀ-መንበር አቶ ብርሃኑ በርሀ: በቀዳማይ ወያነ ፖሊስ ጣብያ:

Arena-Tigray-logo3አቶ ብርሃኑ ትላንት ምሽት እንደታሰሩ የሚታወስ ነው፡፡ አምዶም በፌስቡክ ገፁ ከፖሊሶች አንደበት የሰማውን መሰረት አድርጎ እንደነገረን “ወደቤትህ ለፍተሻ በመጣን ጊዜ ባለመክፈት በወንጀል የምትጠረጠር ግለሰብ እንድታመልጥ ተባብረሀል” የሚል ነው፡፡
ማምሻው ላይ የአቶ ብርሀኑ ባለቤት ወ/ሮ ለምለም ገ/ኪዳን ለቪኦኤ እንደገለፁት ደግሞ ባለቤታቸው የታሰሩበት ምክንያት አልተነገራቸውም፣ ከፖሊስ ጣብያውም ምንም ተጨባጭ ምክንያት አልተሰጣቸውም፡፡ አቶ ብርሀኑንም የታሰረበት ምክንያት በውል እንደማያውቅና ምንም እንዳልተነገረው ከአንደበቱ እንደሰሙ ተናገረዋል፡፡
አብዛኛዎቹ የዐረና አባላት ሲታደኑ፣ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉ፣ ሲገደሉ እስካሁን ብዙም የህ.ወ.ሐ.ት ብትር ያላረፈበት አቶ ብርሀኑ ብቻ ነበር፡፡ እንግዲህ ተቃዋሚ የተባለን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወደ እስርቤት ለማጎር ቆርጠው ስለመነሳታቸው ከዚህ በላይ ምን ምልክት እንሻለን?