የኢትዮጵያን ስም ወደ ኩሽ የመቀየር የኦነጋውያኑ ስም የመቀየር ዘመቻ የመጨረሻ ርምጃና ሀገር የማፍረስ ተልእኮ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ማሳሰቢያ፦ ይሄ ጽሑፍ የሚመለከተው ይሄንን ነውረኛ ተግባር የፈጸሙትንና አስቀድሞም ሲፈጽሙ የነበሩትን በኦሮሞ ሕዝብ ስም የሚነግዱትን ቅጥረኛ ኦነጋውያንን እንጅ የኦሮሞን ሕዝብ አይደለም፡፡

መቸስ ይሄንን የጥፋት ተግባር ምን ብየ እንደምገልጸው አላውቅም! ሉተራውያን ጀርመኖች ገና ዛሬ አይደለም ኦሮሞዎችን መጠቀሚያ በማድረግ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ጥረት ማድረግ የጀመሩት፡፡ በ19ኛው መቶ ክ/ዘ አውሮፓውያን አፍሪካን በቅኝ ግዛት ከተቀራመቱበት ዘመቻ ጋር በተያያዘ ጀርመናዊው ሉተራዊ ሰላይ ሚሽነሪ (መልእክተኛ) ዮሐን ክራፍ ነው ግንኙነቱን የመሠረተው፡፡ ዮሐን “ጋሎችን ከያዝን ምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካን ያዝን ማለት ነው!” ብሎ ያምን ስለነበረ የኦሮሞን ሕዝብ በመያዝ ምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካን የጀርመን ቅኝ ግዛት ለማድረግ ያላደረገው ጥረት አልነበረም፡፡ “ጋላ ማለት ስደተኛ ማለት ነውና ሌላ ስም ያስፈልጋቹሀል!” ብሎም ሕዝቡን ኦርማ ወይም ኦሮማ ከኢትዮጵያ ገንጥሎ መውሰድ የፈለገውን የሀገራችንን ክፍል ደግሞ ኦርማንያ የሚል ስም አውጥቶ የጀርመን ቅኝ ግዛት ለማድረግ ይጥር እንደነበረ ታሪኩ ያስረዳናል፡፡

እያደር በዮሐን ክራፍ ፀረ ኢትዮጵያ የተሰበኩት የኦሮሞ ተወላጆች ከዚሁ እሱ ካወጣላቸው ስም ኦርማ ወይም ኦሮማ እና ኦርማንያ ኦሮሞ እና ኦሮሚያ የሚባሉ ቃላትን ሊያወጡ ቻሉ፡፡ ዮሐን ክራፍ እንዳሰበው ኦሮሞን ተጠቅሞ ምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካን የጀርመን ቅኝ ግዛት ማድረግ ባይችልም በርካታ ኦሮሞዎችን አሳስቶ የዕኩይ ዓላማው ተከታይ በማድረግ እነኝሁን ሰዎች ደግሞ ከጀርመን የመናፍቃን የእምነት ድርጅት ጋር የማስተሳሰሩ ሥራ ግን ተሳክቶለታል፡፡ ለመሳካቱም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁንም ያሉ ውጤቶችን ማየቱ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡

አሁን ደግሞ ብለው ብለው የሀገራችንን አካባቢዎች ስም እየቀያየሩ አዳዲስ ስም መስጠታቸው አንሶ ጭራሽ የኢትዮጵያን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከማሰረዝ ደረጃና ከዚህም ባለፈ የሀገራችንን ስም ሳይቀር አስቀይረው ከቻሉ ሴማውያንን አግልለው ሀገሪቱን የራሳቸው ብቻ ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ ተገንጥለው የራሳቸውን ሀገር መመሥረት ድረስ የደረሰ እንቅስቃሴ እስከማድረግ ሊደርሱ ችለዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ እነኝህ ሁሉ የኦነጋውያን የቅጥረኝነት አስተሳሰቦችና እንቅስቃሴዎች ምን ያህል መረጃና የዕውቀት ድርቅ ያጠቃው የደናቁርት፣ የባንዶችና የንኮች ይቅር የማይባል ነውረኛ ተግባር መሆኑን በሚገባ የምናረጋግጥ ይሆናል፡፡ ከጉዳዩ ግዝፈት የተነሣ በርካታ በሚገባ መብራራት የሚገባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው ጽሑፉ መርዘሙ አይቀርምና እንድትታገሱ እጠይቃለሁ፡፡ ከዚያ በፊት ግን፦

ይሉኝታ ቢሶች ሆይ! ሁሉም ነገር እኮ ልክ አለው፤ አይደለም እንዴ? ምን አለበት ጥጋብ፣ ዝርፊያ፣ ግፍ፣ ውንብድናቹህን በልክ ብታደርጉት??? መቸስ እንደሰው ሁለት እጅ ሁለት እግር ወዘተ. አላቹህና ምንአለ ታዲያ እንደ ሰው እፍረት ቢኖራቹህ??? አሁን እንዲህ በአሳፋሪና ነውረኛ ማንነት ተውጣቹህ ራሳቹህን እንደሰው ትቆጥራላቹህ??? ነው ወይስ እንዴት ነው የሰው ጭንቅላት የላቹህም እንዴ? ቅንጣት የምታክል እፍረትና ይሉኝታ ጠፋባቹህ እኮ! ምን ይሆን ለእናንተ የሚያሳፍራቹህና ነውርም የምትሉት ነገር???

ሰሞኑን የሀገራችን የኢትዮጵያ ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲሰረዝና ኩሽ በሚል ቃል እንዲተካ የማድረግ ነውረኛ የደንቆሮ ሥራ በአንድ የመናፍቃን ካህን ነኝ በሚል በንቲ ኦጁሉ ቴሶ በተባለ ሰው እና በጀርመን የመናፍቃን እምነት ድርጅት የሉተርን መነሣት 500ኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በሠሩት የጋራ ሥራ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ45 ጊዜያት በላይ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ሰርዘው ኩሽ ኩሽ በሚል ቃል ተክተው የራሳቸውን “መጽሐፍ ቅዱስ” አዘጋጅተው ማሳተማቸውን የሚገልጽ ከሰውየው ጋር የተደረገ ቃለምልልስ ድረ ገጽ ላይ አግኝቸ አንብቤ ነበረ፡፡

ሰውየው ይሄንን ለማድረጉ የሰጠው ምክንያት “ኢትዮጵያ የሚልን ቃል የከተቱት ግሪኮች ናቸው መጽሐፍ ቅዱስን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ሲተረጉሙ ኩሽ የሚለውን ቃል ኢትዮጵያ ወደሚል የለወጡት እንጅ ዕብራይስጡ የሚለው ኩሽ ነው!” የሚለውን አንዱ ምክንያቱ እንደሆነ ይናገርና ሁለተኛ ምክንያቱ ደግሞ “ኢትዮጵያ ማለት ጥቁር ማለት ስለሆነ ክብርን የሚነካ የሚያዋርድ (Derogatory) መጠሪያ በመሆኑ፣ ግሪኮችም መጽሐፍ ቅዱስን ሲተረጉሙት ጥቁሮችን ለማዋረድ ብለው ኩሽ የሚለውን ስም በኢትዮጵያ እንደቀየሩት ባደረኩት ጥናት ስለደረስኩበት ነው!” ይላል፡፡

አይገርማቹህም? አሁን ይሄ ሰው ነው እንግዲህ የተማረ የሚባለው? ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ይሄ ሰው ብቻ ሳይሆን ሌሎች የታሪክ ሰዎች እንደሚሉትም “በፀሐይ የጠቆረ ፊት!” ማለት አይደለም እንጅ ቢሆን እንኳ እውነት አይደለም ወይ? እኛ ኢትዮጵያውያን ጥቁሮች አይደለንም ወይ? እኛ አፍሪካውያን የጠቆርነውስ አፍሪካ በምድር ወገብ ላይ ያለች ልሳነ ምድር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ፀሐያማ በመሆኗ አይደለም ወይ የጠቆርነው? ሳይንሱስ (መጣቁ) የሚለውስ ይሄንን አይደለም ወይ? እንጅ የሰው ልጅማ በሃይማኖትም ሆነ በሳይንስ (በመጣቅ) ምንጩ ከእንድ እናትና አባት የተገኘን አይደለንም ወይ? ፀሐይ ፊትን እንደሚያጠቁር ጠቢቡ ሰሎሞን ሲመሰክር “ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለሆንኩ አትዩኝ!” ብሏል መኃ. 1፤6 እርግጥ ሰሎሞን ይሄንን ያለው ንጉሥ ዳዊት የተሳሳተባት ውቧ የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ ኢትዮጵያዊት በመሆኗ ከሷ በመወለዱ ጥቁር ሆኖ ነው ይሄንን የተናገረው፡፡ ይሁንና እሱ መግለጥ የፈለገው የኢትዮጵያውያን ጥቁረት ከፀሐይ የተነሣ መሆኑን ነው፡፡

ታዲያ “ኢትዮጵያ ማለት በፀሐይ የጠቆረ ፊት ማለት ነው ይላሉ ግሪኮች!” የሚባለው ነገር ማለታቸው እውነት ከሆነ ስሕተቱ ምኑ ላይ ነው? አባባሉን በሌላ መንገድ ስንረዳው “ፀሐይ ነው እንጅ ያጠቆራቹህ እንደኛ ናቹህ!” ማለት አይደለም ወይ? ታዲያ ይሄ የግሪኮች አባባል አመክንዮአዊና ክብርን የጠበቀ አባባል ነው እንጅ እንዴት ሆኖ ነው ክብረነክና አዋራጅ ስድብ የሚሆነው??? ስለዚህ እነ በንቲ ኦጁሉ ጥቁርነትን ስድብ እንደሆነ ያስባሉና ጥቁር በመሆናችን ከሰው ወይም ከነጮች ያነስን እንደሆንን ያምናሉ ማለት ነው? እንዴት ዓይነት ደናቁርት ቢሆኑ ነው እንዲህ ሊያስቡ የቻሉት??? እኔ ግን ይህ ተግባር ኢትዮጵያን በመጉዳት ብቻ የተወሰነ አይመስለኝም፡፡ ጥቁር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይሄንን ያህል ትልቅ ቦታ መያዙ ያቃጠላቸው ዘረኛ ነጮች ጥቁር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ቦታ ለማሳጣት የሸረቡት ሴራም እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡

እኛስ ጥቁር በመሆናችን ከነጭ እናንሳለን ብለን አናምንምና አለማነሳችንንም ይልቁንም መላቃችንንም አሁን ኪነብጀታ (ቴክኖሎጂ) በተራቀቀበት ዘመን እንኳ እነሱ ሊሠሩት የማይችሉትን ሥራ ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት የቅዱስ ላሊበላ አብያተመቅደሳትን ከወጥ አለት ፍጹማዊ በሆነ የምሕንድስና ጥበብ ገንብተን፣ እንደነሱ መስረቅ ሳያስፈልገን ከሽዎች ዓመታት በፊት የራሳችንን ፊደላትና ቁጥሮች ፈጥረን፣ ከ1500 ዓመታት በፊት ከነሞዛርትና ቬትሆቨን እጅግ በቀደመ ዘመን የተራቀቀ ዜማ ከነ የዜማ ምልክቱ (ኖታው) ደርሰን፣ ከሽዎች ዓመታት በፊት በሥነ ፈለክ ጥናት ተራቀን የዘመን አቆጣጠርን ቀምረን፣ እነሱ በተለያየ ጊዜ አንዱ ሌላውን ቅኝ እየገዛ እርስበርሳቸው በባርነት የተገዛዙ ሲሆኑ እኛ ግን ተነግሮ በማያልቅ መራር መሥዋዕትነትና ጀግንነት ነጻነታችንን አስጠብቀን ነጻ ሀገር በማቆየታችን ወዘተረፈ. አድርገን በሥራችን አሳይተናልና አስመስክረናልና ቆዳችን በመጥቆሩ ጠጉራችን በማረሩ ከነጮች እናንሳለን ብለን አናምንም ጨርሶም አናስብምና ኢትዮጵያ በሚለው ስም አናፍርም፣ የማንነታችን መገለጫ ስማችንም ነው፡፡ ስለሆነም ማንም ንክ ደንቆሮና የማይመለከተው የነጫጭባ ጥርቅምና ቅጥረኛ ሁሉ ስማችንን እንዲቀይር ፈጽሞ አንፈቅድም!!

ሰውየው “እኛን ለማዋረድ ለመስደብ አስበው ነው ግሪኮች ኢትዮጵያ የሚል ስም የሰጡን!” የሚለው ነገር ፍጹም ሐሰት መሆኑን የሚያረጋግጠው በዚያ ዘመን ግሪኮች እኛን ኢትዮጵያንን “በደል አበሳ ኃጢአት የሌለባቸው፣ የአማልክቶቻችን አቻዎች ናቸው!” በማለት ከሰው የተለየን እንደሆንን አድርገው ይቆጥሩን የነበረበት ዘመን መሆኑ ነው፡፡ በግሪኮች አስተሳሰብ ዩቶጵያ (Utopia) ማለት ልዩ የሆነ ማኅበረሰብ የሚኖሩባት ገነት የሆነች ምድር ማለት ነው፡፡ እነ ሆሜር እነ ሄሮዱቶስ እነ ቶማስ ሙር ፈላስፎቻቸውና ጸሐፍቶቻቸውም የሚያምኑትና የሚያስቡት ይሄንን መሆኑ ይታወቃል፡፡ እውነታው ይሄ ሆኖ እያለ የሌለ ወይም ያልነበረ ነገርን ፈጥሮ ለግል ወይም ለቡድን ጠባብ ዓላማ ለመጠቀም መጣር ምን ያህል አሳፋሪና ነውረኛ ተግባር መሆኑን እነኝህ ሰዎች ሊረዱ የሚችሉ አለመሆናቸውን ሳስብ የሚሰማኝ ሐዘን ከባድ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ስለሚለው የሀገራችን ስም የሀገራችን ታሪክ ግን የሚለው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 1856-1800 ድረስ ለ56 ዓመታት ያህል ሀገራችንን ባሥተዳደረው ንጉሣችን ኢትዮጲስ የተነሣ ሀገሪቱ ኢትዮጵያ መባሏን፣ አቢስ በተባለው ንጉሣችንም የተነሣ በዓረቦች ሀገሪቱ አቢሲኒያ ሕዝቧ ደግሞ አበሻ ወይም ሐበሻ (የአቢስ ሕዝብ) መባላችንን ነው የሚናገረው፡፡

ሰውየው መጀመሪያ ላይ ወደጠቀሰው ምክንያት ስመለስ አዎ እርግጥ ነው ዕብራይስጡ የሚለው ኩሽ ነው፡፡ ኩሽን አስቀርተው ኢትዮጵያ በሚል ቃል የተኩትም ሰብዓው ሊቃናት በመባል የሚታወቁት ከክርስቶስ ልደት ሁለት መቶ ሐምሳ ዓመታት በፊት የኦሪት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ ወይም ግሪክ የተረጎሙት በጥሊምስ በምርኮ የወሰዳቸው ዕብራውያን ሊቃናት ናቸው፡፡ ልብ በሉ ግሪካውያን ሳይሆኑ ዕብራውያን ወይም እስራኤላውያን ሊቃናት ወይም አለቆች ናቸው፡፡

እነ ፓስተር በንቲ ኦጁሉን ለስሕተት የዳረጋቸው የገዛ ራሳቸው ያልበሰለ ያልጠራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤያቸው ነው፡፡ ይሄ የተዛባ፣ ያልበሰለ፣ ያልጠራ፣ ጥራዝ ነጠቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤያቸው እነ ፓስተር በንቲን “አፍሪካ የኩሻውያን እጣ ክፍል፣ ሀብት፣ ሀገር ናት!” ብለው እንዲያምኑ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል፡፡ ስለዚህም “ሴማውያኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ እንግዶች፣ መጤዎች በመሆናቸው የኢትዮጵያ ባለቤትነት የኩሻውያን እንጅ የሴማውያን አይደለም!” ብለው በጽኑ ያምናሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የሀገሪቱን ስም ወደ ኩሽ ከመቀየር ጀምሮ የሀገሪቱ ረጅም ታሪክ፣ ነገሥታቱ ሁሉ የኩሻውያን እንደሆነ እንዲቆጠር እየጣሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ እንዲሆን እንደሚሠሩም በዚሁ ቃለ ምልልስ በይፋ ተናግረዋል፡፡ የገረመኝ ነገር አፍሪካ የኩሽ ናት በሚለው እሳቤ ኢትዮጵያ የሚለውን ኩሽ በሚለው ሲቀይሩ ግብጽ የሚለውንም ኩሽ ሳይሉ ለምን እንደተውት ነው የገረመኝ፡፡

አሁን በእነሱ ቤትኮ አማራን ሴማዊ አድርገው በአማራ ላይ መመጻደቃቸው፣ አማራን ባዕድ ማድረጋቸው ነው እኮ! ነገር ግን ተሳስታቹሃል እውነቱ እንዲያ አይደለምና፡፡ አማራ ኩሻዊም ነው ሴማዊም ነው እንጅ ሴማዊ ብቻ ወይም ኩሻዊ ብቻ አይደለም፡፡ አማራ የተፈጠረው አገው ከአራት ሽህ ዓመታት በፊት ጀምሮ እራሱን ለውጭው ዓለም ተጋላጭ አድርጎ ከነገደ ዮቅጣን ጋር በፈጠረው መስተጋብር የተፈጠረ ማኅበረሰብ ነው፡፡ በዚህ ሒደት ከተሜው አገው አማራ ሆኖ ወጣ ገጠሬው አገው ደግሞ አገው እንደሆነ ቀረ፡፡ ይህ ሁኔታ አንዴ ብቻ ተከስቶ የቀረ ክስተት አይደለም፡፡ በየዘመኑ በተደጋጋሚ የሆነና አሁንም ድረስ እየሆነ ያለ ሒደት ነው፡፡ ለዚህም መረጃው አማርኛ የሥነ ጽሑፍ ቋንቋ ሲሆን ፊደል ላልነበራቸውና ግዕዝ ውስጥ ለሌሉት ኩሻዊ ድምፆቹ ማለትም ለእነ ሸ፣ ቸ፣ ኘ፣ ኸ፣ ዠ፣ ጀ፣ ጨ ድምፆቹ ፊደል ቀርፆ እራሱን ለአገልግሎት ማብቃቱ ነው፡፡ እንጅ እነ ፓስተር በንቲ እንደሚመስላቸው አማራና አገው የተለያየ ደም ያላቸው አይደሉም፡፡ ባጭሩ አማራ ማለት ነባሩ አገው ሲደመር መጤው ነገደ ዮቅጣን ነው፡፡ እናም እነ የቅዠት ቋቶች፣ የንክ ጥርቅሞች ሆይ! እባካቹህ ቢያንስ ልታደርጉ የምትፈልጉትን ነገር ጠንቅቃቹህ ለማወቅ ሞክሩ? አስቀድማቹህ ልትጓዙበት የምትፈልጉትን መንገድ ይወስዳቹህ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ ሙከራ አድርጉ፡፡ ዓይናቹህን ጨፍናቹህ የእውር ድንብስ ጉዞ አትጓዙ ገደል ትገባላቹህ፡፡

አሁን ጥያቄው “ይሄ እነ ፓስተር በንቲ ኦጁሉ የሚሉትን ነገር የሚደግፍ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ ወይ?” የሚለው ነው ትልቁ ጥያቄ፡፡ “አፍሪካ የኩሾች ናት!” የሚለውን አባባላቸውን የሚደግፍ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተገኘ አባባላቸው ተጨባጭና መሠረት ያለው ይሆናል፡፡ ከሌለና ለዚህ አስተሳሰባቸው የዳረጋቸው የተሳሳተ ወይም የተዛባ ያልጠራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤያቸው ከሆነ ደግሞ በድንቁርናቸው ሊያፍሩ የሚገባ ይሆናል፡፡

ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንሒድ፦ እርግጥ ነው አንድ ነገር አለ ከጥፋት ውኃ በኋላ ኖኅ (ልብ በሉ ኖኅ አልኩ እንጅ እግዚአብሔር አላልኩም) ለሦስቱ ልጆቹ ለሴም ለካምና ለያፌት ዓለምን ከፋፍሎ ሰጥቷቸዋል ዘፍ. 10፤1-31 ለሴም ዛሬ እስያ ብለን የምንጠራውን ዘፍ. 10፤21-31 ፣ ለረገመው ለካም ደግሞ ዛሬ አፍሪካ ብለን የምንጠራትን አኅጉር እና መካከለኛውን ምሥራቅ ዘፍ. 10፤6-20 ፣ ለያፌት ደግሞ ዛሬ አውሮፓ ብለን የምንጠራውን ልሳነ ምድር ዘፍ. 10፤2-5 አከፋፍሎ ሰጥቷቸዋል፡፡ እንግዲህ ጉዳዩ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ ኩሽ አፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ የደረሰው የካም ልጅ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ብቸኛ ልጁ ግን አይደለም፡፡ ከሱ ሌላ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን የሚባሉትም ልጆቹ ናቸው፡፡

እንግዲህ የኦነጉ ፓስተር እነ በንቲ ይሄንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት ያደረገ ነገር ግን የተዛባ ወይም ጥራዝነጠቅ ግንዛቤ ያለው ሰው “አፍሪካ የኩሽ ናት!” ያላቸውን ሩብ ወይም ጎደሎ እውነት ይዘው ነው “እኛ ኩሻውያን ነን ነባር (indigenous) ሕዝቦችና የምድሪቱ ባለቤቶች!” እያሉ የሚገኙት፡፡ ከጥቅሱ መረዳት እንደምትችሉት ግን አፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ በአባቱ ላይ በማፌዙ ከተረገመው አባታቸው ከካም የወረሱት የምጽራይምም፣ የፉጥም፣ የከነዓንም ምድር ነው እንጅ የአንዱ ወንድማቸው የኩሽ ብቻ አይደለም፡፡

ኦሪት ግልጽ አድርጋ ይሄንን እያለች እያለ ዕብራውያኑ አፍሪካ የካምና የልጆቹ እንደሆነች፣ የአንዱ የካም ልጅ የኩሽ ብቻ እንዳልሆነችና ወንድሞቹና ልጆቻቸው እንደወረሷት እያወቁ የኩሽ ብቻ እንደሆነች ሁሉ ለምን ኩሽ ብለው እንደጠሯት የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በአንድ አጋጣሚ በተፈጠረ ስሕተት ተለምዶ የቀረ አጠራር ሳይሆን እንዳልቀረ እገምታለሁ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል እነዚያ ሰብዓው ዕብራውያኑ አለቆች ኦሪትን ወደ ጽርዕ ሲተረጉሙ ኩሽ የሚለው ሥያሜ ስሕተት መሆኑ ስለገባቸው ኢትዮጵያ በማለት ሊተኩት የቻሉት፡፡

ሌላም ምክንያት ነበራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ኩሽ ኩሽ እያለ የሚጠራው አካባቢ በዚህ ዘመን አንሳ ብትታይም ቀድሞ በነበራት ሰፋ ያለ የቆዳ ስፋቷ ሀገራችንን ኢትዮጵያን የሚያመለክት እንጅ ኩሽ በሚለው ቃል በምናብ እንደሚታሰበው ቀሪውንም የአፍሪካ ክፍልና ሕዝብ የሚመለከት ባለመሆኑ ነው አፍሪካን ለመጥራት ኩሽ ብለው የሚጠሩትን ቃል ትተው ኢትዮጵያ በማለት ለመተካት የተገደዱት፡፡ ለምሳሌ እንጥቀስ ዘፍ. 2፤13 “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከባል!” ይላል፡፡ እንደምታውቁትም ግዮን ወይም በዘመናዊ ስሙ ዓባይ የሚመነጨውና ምድሯን አካብቦ ግብጽ የሚገባው ከዚህም ሜዲትራኒያን የሚቀላቀለው ከኢትዮጵያ ወጥቶ ነው፡፡ ሱዳን የምትባልን ሀገር የፈጠሯት አሁን ቅኝ ገዥዎች ናቸው እንጅ በአክሱም ዘመንም ቅኝ ገዥዎች እስከከፈሏት ድረስ የኢትዮጵያ አካል ነበረች፡፡

ኢትዮጵያ የሚለውን ዕብራውያኑ አፍሪካን ለመግለጽ በሚጠቀሙበት ቃል በኩሽ ብትተኩት ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዐረፍተ ነገር ትርጉም አልባ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ግዮን ምሥራቅ አፍሪካን እንጅ የአፍሪካን ምድር ሙሉ የሚያካብብ ወንዝ አይደለምና ነው፡፡ እነ ፓስተር በንቲ ኦጁሉ “አይ ኩሽ ብሎ የዕብራውያኑ መጽሐፍ የሚጠራው ኩሽ የሠፈረበት ስፍራ ማለትም ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራውን አካባቢ ነው እንጅ መላው አፍሪካን አይደለም!” የሚሉ ከሆነም ኩሽና ልጆቹ በዚህ አካባቢ ለመስፈራቸው መረጃቸው ምንድን ነው? ይሄንን የሚያረጋግጥ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ላይም ሆነ የታሪክ መጻሕፍት ላይ የለምና ነው፡፡

ሌላኛው ምሳሌ ደግሞ እንደሚታወቀው በብሉይ ኪዳን ወይም በኦሪቱ ዘመን በዓለም ላይ እግዚአብሔርን ያመልኩ የነበሩ ሕዝቦችና ሀገራት መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ የመሰከረላቸው ሀገራትና ሕዝቦች ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ እነሱም እስራኤልና ኢትዮጵያ ወይም የእስራኤል ልጆችና የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስና ታሪክም ይሄንን በሚገባ ያረጋግጣሉ፡፡ አሞጽ 9፤7 “የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር!” ይላል ቃሉ፡፡ በዚህም መሠረት ነው ወይም በኦሪቱ እግዚአብሔርን እናመልክ ስለነበረ ነው በሐዋርያት ሥራ 8፤26-40 ላይ እንደተገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ማለትም በጅሮንድ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ሊሰግድ ኢየሩሳሌም የተገኘውና ሊሰግድ በሔደበት ጊዜም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ የተገኘው፡፡ እንዲሁም ኢትዮጵያ ኢየሩሳሌም ውስጥ ከሦስት ሽህ ዓመት በፊት ጀምሮ የቅዱሳት መካናት ይዞታ ሊኖራት የቻለው፡፡

ሌሎቹንም ኢትዮጵያን የሚያነሡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ብትመለከቱ የሚያወሩት ስለኛ ስለ ኢትዮጵያውያን ነው እንጅ በተቀረው የአፍሪካ ክፍል ያሉትንም የተቀሩትን ሕዝቦች የሚጨምሩ አይደሉም፡፡ ከታሪክና ከትውፊትም እስከዛሬም ድረስ ካሉ መረጃዎች፣ ሥርዓተ አምልኮዎችና የቃል ኪዳኑን ታቦት ጨምሮ ከሌሎችም ንዋዬ ቅድሳት በግልጽ እንደምንረዳው በኦሪትና በሐዲስ እግዚአብሔርን ሲያመልክ የቆየ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጅ የተቀረው የአፍሪካ ሕዝብም አይደለም፡፡

እናም እውነታው እንዲህ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ኩሽ በሚል ቃል ብንተካው “መላው የአፍሪካ ሕዝብ እግዚአብሔርን አምላኪ ሕዝብ ነበር!” የሚል ፍጹም የተሳሳተና እውነት ያልሆነ መልእክት ልናስተላልፍ ነው ማለት ነው፡፡ እውነት ነው ወይ? ነው ጥያቄው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ማስዋሸትና መረጃ ማዛባት አይደለም ወይ ውጤቱ የሚሆነው? ይሄንንስ ማድረግ እውነታንና መረጃን ከማዛባት አኳያ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ተግባር አይደለም ወይ?

ከዚህም በተጨማሪ እነ ፓስተር በንቲ ሊያውቁት የሚገባው ነገር አፍሪካ ውስጥ ከ15 በላይ የቋንቋ ቤተሰቦች ያሉ መሆናቸውን ነው፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ አራት የቋንቋ ቤተሰቦች አሉ ከኩሻዊና ሴማዊ ሌላ ኦሟዊና ናይሎሳሃራን የሚባሉ የቋንቋ ቤተሰቦች አሉ፡፡ ኦሟዊ የሚባሉት በኦሞ ወንዝና በደቡባዊ ስምጥ ሸለቆ መሀከል የሚነገሩ 28 ዓይነት የተለያዩ ቋንቋዎች ሲሆኑ፡፡ ናይሎ ሳሃራን የሚባሉት ደግሞ ጋንቤላና ቤንሻንጉል አካባቢዎች የሚነገሩ 19 የተለያዩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡ አሁን እንግዲህ እንደነ በንቲ የተዛባ አስተሳሰብ የእነኝህ ጥቁር አፍሪካውያን ቋንቋዎች ኩሻዊ አይደለምና ነባር ሕዝቦች አይደሉም ሊሉ ነው ወይ?

የሚገርመው ነገር በሥነ ልሳን ጥናት (linguistics) ኦሮምኛ በአፍሮ ኤዥያዊ ቋንቋ የሚመደብ ቋንቋ መሆኑ ነው፡፡ ኦሮምኛ ብቻ ሳይሆን ከናይሎ ሳሃራን ቋንቋዎች በስተቀር ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቋንቋዎች በሙሉ ኩሻዊውም ሴማዊውም ኦሟዊውም በአፍሮ ኤዥያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡ እንደዘርፉ ተመራማሪዎች ምንጫቸውም እስያ መሆኑ ይታመናል፡፡ የዋሀኑ እነ ፓስተር በንቲ መሰላቸው እንጅ ኩሻዊ በመባል የተሠየሙ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ከኩሽ ጋር የተዛመዱ ወይም የኩሽ ዘሮች ማለትም አይደለም፡፡ ይህ ሥያሜ በ19ኛው መቶ ክ/ዘ የቋንቋ አጥኝዎች በገዛ ፍላጎታቸው ለተወሰኑ የቋንቋ መደቦች ያወጡት ሥያሜ ነው እንጅ አጥኝዎቹ ይሄንን ሲሉ ኩሻዊ ቋንቋ ተናጋሪዎች የካም ልጅ የኩሽ ዘሮች ናቸው!” ለማለት አይደለም፡፡

በመሆኑም እነ ፓስተር በንቲ ከናካቴው የማያውቁትን የማይዛመዱትን ባሕል፣ ማንነት፣ ሃይማኖትና ሃይማኖታዊ ባሕል የራስ ለማድረግ የጣሩት ጥረት አስቂኝና አሳፋሪም ነው፡፡ ይሁን ከተባለም በኩሻዊነታቸው የሀገራችን ታሪክና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምስክርነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸው አሻራው፣ ማንነቱ፣ ቅርሱና ባሕሉ ያላቸው አገውንና ቅማንትን ነው እንጅ ኦሮሞ ምን አገናኝቶት ምንስ አግብቶት ይመለከተዋል? በስመ ኩሽነት እንዴት ሆኖ፣ በምንስ ሒሳብ ነው የአገው ታሪክ የኦሮሞ ሊሆን የሚችለው? በስመ ሴምነት የዓረብ ወይም የእስራኤላውያን ታሪክ የጉራጌ ታሪክ ይሆናል ወይ? የወንድሜ ስኬት የወንድሜ እንጅ ለኔ ምኔ ነው? እራሴን ተጣጥሬ ሰው ማድረግ ይኖርብኛል እንጅ የሱ ስኬት ለኔ ምን የሚፈይድልኝ ነገር አለ? እኔ መሀይምና ደሀ ሆኘ እያለሁ የሱን ምሁርነትና ሀብት የራሴ አድርጌ ብቆጥር ምሁርነቱና ሀብቱ የኔ ይሆናል ወይ? እንዲህ ማሰቤስ ጤናየ በእጅጉ የተቃወሰ መሆኑን አያረጋግጥም ወይ?

እናም እነ ፓስተር በንቲ ሆይ! የታሪክና የሀብት ዝርፊያ ሱሳቹህና የበታችነት የሥነልቡና ሕመማቹህ የዚህን በሚያህል አሳፋሪ በሆነ ድርቅና ቅሚያና ድንቁርና ውስጥ ዘፍቋቹሀልና ይሄ ችግራቹህ አሳብዶ ጨርቃቹህን ሳያስጥላቹህ መፍትሔ ብትፈልጉለት መልካም አይመስላቹህም? ወደዳቹህም ጠላቹህ የናንተ ታሪክና ማንነት ከቤናዲር ሱማሌ ተነሥታቹህ የግራኝ አሕመድ ድል የፈጠረላቹህን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ስፍራዎችን ወሮና በየጊዜው ተስፋፍቶ ከመያዝና በባሕላዊ ባዕድ አምልኮ ተተብትቦ ከኖረ ጎሳነት የዘለለ ሆኖ አያውቅም አለቀ፡፡ ምን ለማጠጋጋት ብትጥሩ፣ ምን ፈጠራ ብትደርቱ የትልቅ ሰው ልብስ ለጨቅላ ሊገጥመው እንደማይችለው ሁሉ የአማራ ወይም የአገው ታሪክና ማንነት ፈጽሞ ለእናንተ ሊገጥምና ሊሆን አይችልም አከተመ፡፡

ኦሮሞ በዚህች ሀገር ውስጥ እንደጎሳም ሆነ እንደብሔረሰብ ከ16ኛው መቶ ክ/ዘ በፊት ህልውና ኖሯቹህ አያውቅም፡፡ እነ ፔድሮ ዴካቪልካም፣ እነ ፍራንቼስኮ አልቫሬስ፣ ዓረቡ የግራኝ አሕመድ ዜና መዋዕል ጸሐፊ ሲሀብ አድዲን አሕመድ በ16ኛው መቶ ክ/ዘ ቅድመ የግራኝ ወረራና በወረራው ወቅት ስለነበረው የሀገራችን ነባራዊ ምኅዳር (demography) በአካል ተገኝተው ብጥር አድርገው ከጻፏቸው መጻሕፍት እንደምንረዳው ኦሮሞ ወይም ጋላ የሚባል ጎሳ ወይም ብሔረሰብና ኦሮምኛ የሀገር፣ የከተማ፣ የመንደር፣ የወንዝ፣ የጋራ ሸንተረር ሥያሜ አንድም ያልነበረ መሆኑን ነው፡፡

ኦሮሞ ከ16ኛው መቶ ክ/ዘ በኋላ መግባቱን ካሉን ታሪካዊ መረጃዎች በተጨማሪ የኦሮሞ አባገዳዎች ስለራሳቸው ይናገሩት ከነበረው አፈታሪክና ከባሕላቸው ውስጥ ካለው ትውፊታዊ መዝሙራቸውም መረዳት ይቻላል፡፡ በሶማሌዎችና በባንቱዎች ከላይና ከታች እየተወጉ ሲሰቃዩበት ከነበሩበት ቤናዲር ሱማሌ ለቀው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ከተቀመጡባትና እንደገነት ከሚቆጥሯት ወላቡ ስለነበራቸው የሰላም፣ የደስታ፣ የፍስሐ ዘመን ከሚያወዳድሰው ትውፊታዊ መዝሙራቸው ይሄንን እውነታ መረዳት ይቻላል፡፡ ሶማሊያ ገብተው ረዘም ላለ ዘመን እዚያ ከመቆየታቸው አስቀድሞም ማዳጋስካር እንደነበሩ ይነገራል፡፡ ይሄንንም ታሪክ የታሪክ ጸሐፍት ጽፈውታል፡፡ ጥቂቶችን መጥቀስ ካስፈለገም፡፡ 1ኛ. የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት አቶ ይልማ ደሬሳ ስለ ኦሮሞ ጥልቅ መረዳት ካላቸው አባገዳዎች ያገኘሁት መረጃ ነው ብለው “የኢትዮጵያ ታሪክ በ16 መቶ ክ/ዘ” በሚለው መጽሐፋቸው፣ 2ኛ. ተክለ ጻድቅ መኩሪያ “የግራኝ አሕመድ ወረራ የሚለው መጽሐፍና የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ”፣ 3ኛ. አለቃ ታዬ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ” ፣ 4ኛ. አባ ባሕርይ የዓይን ምስክር በመሆን ስለ ኦሮሞ አገባብና ባሕላቸው በጻፉት መጽሐፍ፣ 5ኛ. ዐፄ ልብነ ድንግል በግራኝ ሲሸነፉ ለፖርቹጋሎች ባቀረቡት የእርዳታ ጥሪ መሠረት አብሮ መጥቶ የነበረውና የኢትዮጵያ ጳጳስ ካልሆንኩ ብሎ ከዐፄ ገላውዴዎስ ጋር የተጋጨው ቤርሙዴዝ ሀገሩ ሔዶ ስለ ኢትዮጵያ በጻፈው መጽሐፍ፤ እነኝህ ጸሐፍት ኦሮሞ ወደ ኢትዮጵያ ገባ የሚሉበትን የተለያየ ዘመን ያስቀምጡ እንጅ ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ መምጣቱን ያረጋግጣሉ፡፡

ተ/ጻድቅ መኩሪያ በመጽሐፋቸው ላይ “ኦሮሞ የገባው በ16ኛው መቶ ክ/ዘ ከግራኝ ወረራ በኋላ ከሆነ ከዚያ በቀደመው ዘመን እነ አዛዥ ጫላ፣ አነ ላሎ፣ እነ አጋፋሪ ቱሉ ከግራኝ አሕመድ ወረራ በፊት በእነ ዐፄ ዓምደ ጽዮን፣ በእነ ዐፄ ልብነ ድንግል ታሪከ ነገሥትና ዜና መዋዕሎች ላይ እንዴት ሊገኙና ስማቸው ሊጠቀስ ቻለ?” ሲሉ ይጠይቁና ኦሮሞ ከ16ኛው መቶ ክ/ዘ በፊት እንደገባ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ የተጠቀሱት ግለሰቦች በዚያ ዘመን እዚህ ሊገኙ የቻሉበት ምክንያት ግን ኦሮሞ ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለነበረ ሳይሆን ኦሮሞ ከነበረበት ሞቃዲሾ አቅራቢያ ወይም ከቤናዲር እየተነሣ ለከብት ዝርፊያና
ለወረራ ይመጣ ስለነበር በእንደዚህ ዓይነቶቹ አጋጣሚዎች
ተማርከው የሚቀሩት ግለሰቦች በታማኝነታቸውና በጉብዝናቸውም ሞገስ እያገኙ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን
እንደታየው በጦርነት ተማርከው መጥተው ለአዛዥነትና ለሥልጣን እንዲበቁ እንደተደረጉት እንደነ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴና ሌሎች እነኝህም ተመሳሳይ ዕድል ገጥሟቸው በዚያ ዘመን ሊገኙ ስለቻሉ ነው፡፡

ከነኚህ የታሪክ መዛግብት ምስክርነት በተጨማሪም ዛሬ ኦሮሞ ሰፍሮ ባለበት ከታች እስከ ላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ግራኝ ያፈራረሳቸው በርካታ የጥንታዊ አብያተክርስቲያናትና ገዳማት ፍርስራሾች ያሉ መሆናቸው ነው፡፡ ይሄ ሊስተባበል የማይችል ተጨባጭ መረጃ ነው፡፡ ግራኝ አሕመድ ነባሩን ሕዝብና መንግሥት ወደ ሰሜን እየገፋ እየጠረገ ነጻ ባደረገበት ወቅት ነው ገብተው ለመስፈር የበቁት፡፡ የቀረውንም በቱርኮች በዓረቦች በፋርሶችና በሕንዶች ተዋጊዎች ታግዞ ሀገሪቱን ለ15 ዓመታት ባደቀቃት አረመኔያዊ የግራኝ አሕመድ ወረራ የተዳከመውን ሕዝብና መንግሥት በመውጋት ነው ኦሮሞዎች አሁን የያዙትን የሀገራችንን ክፍል ነባር ስማቸውን እየቀየሩ ዳሞትና ቢዛሞና ዳሞት የነበረውን ወለጋ፣ ጠፈርጋ የነበረውን አርሲ፣ ደዋሮ የነበረውን ሐረርጌ፣ ላኮመልዛ የነበረውን ወሎ፣ እናርያ የነበረውን ኢሉባቡር፣ ባሊ የነበረውን ባሌ፣ ገሙ የነበረውን ጅማ፣ ግራርያ የነበረውን ሰላሌ፣ ደዋሮ የነበረውን ጭሮ፣ ቤተ ጊዮርጊስ የነበረውን ወረኢሉ፣ ቤተ አማራ የነበረውን ወረኢመኖ፣ አንጎት የነበረውን ራያ ወዘተረፈ. እያሉ የቀየሩት፡፡ እስከ ጃንሆይ ጊዜ ድረስ እነዚህ ነባር ስሞች ብዙዎቹ ያገለግሉ ነበር፡፡

እነሱ በርትተው በመጣራቸው ግን ዛሬ አዲሱን የኦሮምኛ ሥያሜዎቻቸውን እኛንም ሳይቀር አስለምደው ዛሬ ሀገሩ ሁሉ ከድሮውም የእነሱ የነበረ እስኪመስል ድረስ በኦሮምኛ ሥያሜዎች ሊሞሉት ቻሉ፡፡ ይሄንን ሁሉ አግባብ ያልሆነ ድርጊታቸውን በዝምታ ስንመለከትላቸው ጊዜ ዛሬ ደሞ ብለው ብለው የሀገራችንን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ አጠፋን ካሉ በኋላም ጭራሽ የሀገራችንን ስም ለመቀየር መነሣታቸውን እንደምታዩት የኦነጉ ፓስተር ሳያፍር “….ባንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የኢትዮጵያ ጥናት እንዳለ እሰማለሁ። መጨረሻ ላይ ይሄም ይቀየራል!” በማለት እየነገረን ነው፡፡ ይሄ ሰው በቃለምልልሱ ላይ ባነሣቸው አንዳንድ ኦነጋዊ አስተሳሰቦች ላይ ጥቂት ልበልና ጽሑፌን ልቋጭ፡፡

ፓስተር በንቲ ኦጁሉ ምን አሉ፦ “አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ካርታ ዳር ድንበር የተቋቋመው ፤ የተመሰረተው ፤ በዳግማዊ ሚኒሊክ የአቢሲኒያው ንጉሥ ነው። የደቡብን ኩሾችና ሌሎችንም በቅኝ የያዘውና አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ግዛት የፈጠረው!” አሉ፡፡

እነ ፓስተር በንቲ ነጭ አምላኪዎች ናቸውና እስኪ ነጮች ስለ ኢትዮጵያ ወይም አቢሲኒያ ግዛት ያሉትን እንጥቀስላቸው፦

“….እነዚህ የአበሻ ሕዝቦች ሰፊ ግዛት አላቸው፡፡ ከቀይ ባሕር ዳርቻ ከምጽዋ ከሱአኪንና ከአርቂቆ ተነሥቶ ግዛታቸው እስከ ሞቃዲሾና ሶፋላ ይደርሳል፡፡ በምዕራብም በኩል ግዛታቸው የሚዋሰነው ከኑባውያንና ከሌሎችም ሕዝቦች ጋር ነው!” ኦልፎንሶ አልቡ ከርክ 1503ዓ.ም.

“….የአበሾች ግዛት ሰፊ ነው፡፡ ቀይ ባሕር ዳርቻ ካለው ከትልቁ ወደባቸው ከቢሊ ተነሥቶ ወደ ውስጥ ሲጓዝ በአዳል ምድር አልፎ ሐድያ ሁሉ የእነሱ ሀገር ነው፡፡ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ አቅጣጫም እስከ ሞቃዲሾ ይደርሳል፡፡ ….አበሾቹ በጣም ሰፊና ሀብታም ሀገር አላቸው፡፡ ….እነዚህ ሕዝቦች ወሰናቸውን ለማስከበር ወደዳር ሀገር ወይም ወደ ወሰናቸው በሚጓዙበት ጊዜ የሚጓዙት ዛፍ እየመነጠሩና መንገድ እየሠሩ ነው፡፡ ….!” ፍራንቼስኮ አልቫሬስ 1520 ዓ.ም.

“…አበሾች ዙሪያቸውን በአረመኔዎችና በብዙ ጠላቶቻቸው የተከበቡ ሕዝቦች ቢሆኑም ግዛታቸው ግን ሰፊ ነው፡፡ ከነኳቸው ተዋጊ ሕዝቦች በመሆናቸው ዙሪያቸውን የከበቧቸው ጠላቶች በተነሡባቸው ጊዜ ከጠላቶቻቸው ጋር እየተዋጉና እያሸነፉ ይኖራሉ፡፡ የአበሻ ሰዎች ለማንም ባዕድ አንገዛም እያሉ ራሳቸውን ችለው የሚኖሩና ሀገራቸውን ከማንኛውም ባዕድ ገዥ እየተከላከሉ የሚጠብቁ ሕዝቦች ናቸው፡፡ …. ግዛታቸውም ቀይ ባሕርን ተሻግሮ እስከ ዓረብ ሀገር ድረስ ነው፡፡ ….!” ካርታ ዳስ ኖቫስ 1521 ዓ.ም.

እንግዲህ ባዕዳን የዓይን ምስክሮች ያዩትን እንዲህ ቁጭ አድርገውታል፡፡ እነ ፓስተር በንቲም እውነቱ ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ የሚሰርቅ፣ የሚዘርፍ፣ የሚያጭበረብር ሰው የግድ መዋሸት፣ ማምታታት፣ ማመናበድ ስላለበት ነው ይሄንን የሚያደርጉት፡፡ የኦነጉ ፓስተር ቀጠሉና ደሞ ምን አሉ፦

“….እስከ 1931ዓ.ም. ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ሕጋዊ እውቅና አላገኘም ነበር። ከ1931ዓ.ም. በፊት ሀገሪቱ አቢሲኒያ ነበር የምትባለው። እና አቢሲኒያውያን እራሳቸውን የሴም ሕዝብ ብለው ነው የሚጠሩት። ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ናቸው በ1931ዓ.ም. በመጀመሪያ ሕገመንግሥታቸው ውስጥ አቢሲኒያ የሚለውን ስም ጥለው ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ያጸደቁት!” ብሎ አረፈዋ ሰውየው ንክ አይደል እንዴ? ዓይን ባወጣና እርስ በእርሱ በሚጋጨው ዕብለቱ ያፍር መሰላቹህ?

ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ዐፄ ኃይለሥላሴ ናቸው 1931 አቢሲኒያ የሚለውን ትተው የተጠቀሙበት ከዚያ በፊት አልነበረም ለሚለው ነገር ፓስተር በንቲ የሚኖረው አውሮፓ በመሆኑ ለንደንና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች ቤተ ቅርስ (museum) ያሉትን ከዐፄ ኃይለ ሥላሴ በፊት የነበሩት ነገሥታቶቻችን ከአውሮፓውያኑ ነገሥታት ጋር የተፃፃፏቸውን “ሞዓ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ!” የሚል ማኅተም ያረፈባቸውን ደብዳቤዎችን አንብበው ያረጋግጡ እሽ አቶ ኦጁሉ? አንድ ነገር ግን ገረመኝ፡፡ አስቀድመው ግሪኮች ናቸው ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲተረጉሙ ኢትዮጵያ ያሉት እያሉ ሲንተባተቡ ቆይተው አሁን ደግሞ ዐፄ ኃይለሥላሴ ናቸው ሲሉ ትንሽ አለማፈራቸው፡፡ ፓስተር በንቲ ይሄንን ያህል የወረደና ደካማ የማስተዋል የማገናዘብ ችሎታ ይዘው ዶክተር ነኝ ሲሉ አለማፈርዎ ነው እኔን በጣም የደነቀኝ ነገር፡፡

የሐሳብ አንድ ሲደመር አንድን ማስላት የሚሳናቸው ፓስተር በንቲ እንደገና ደግሞ ተመለሱና ምን አሉ “….ግሪኮች ኢትዮጲስ አሉ፤ ምክንያቱም ሕዝብ ኢትዮጵያ ስለሚባል ግዛት አፈታሪክ ያወራ ነበርና። በትክክልም የኩሽ ስለነበረ ግዛት። ስለ ንግስት ሳባ ነበር የሚናገሩት። ኩሽ እንጂ ሴማዊት ስላልነበረች ሰው። ግዛቷም የኩሽ ግዛት እንጂ ኢትዮጵያ አልነበረችም። የአካዳሚክ ሰዎች ፤ ታሪክ አጥኚዎች፤ የሥነ መለኮት ሰዎች ይህን በደንብ መረዳት አለባቸው። ፖለቲከኞች ደግሞ እውነትን መያዝና ያለፉ ስሕተቶችን ማረም ይገባቸዋል!” በማለት አስጠንቅቀዋል አቶ በንቲ አይገርምም?

ዝም ብሎ በመጮህ የሚሆን ነገር አለ እንዴ ፓስተር በንቲ? ንግሥተ ሳባ ወይም ሳባ (በዚህ አጋጣሚ ሳባ የደቡብ ዓረቢያ ግዛት ስም ነው የሚሉ ሰዎችን ሰምቻለሁ፡፡ ከንግሥተ ሳባ በፊት ሳባ በሚል መጠሪያ ስም የተጠሩ ነገሥታት እንደነበሩን አያውቁም መሰለኝ) ፓስተር ማክዳን ኩሻዊት ናት ሲሉ ኩሻዊት ለመሆኗ ሴማዊት ላለመሆኗ መረጃዎ ምንድን ነው? ሁለቱንም ናት ቢሉ ትክክል በሆኑ ነበር፡፡ ምክንያቱም ነባሩ የአገው (የኩሽ) ነገድና ቀይ ባሕርን ተሻግሮ የመጣው ነገደ ዮቅጣን ተቀላቅለው ለመሠረቱት መንግሥት ማክዳ ወይም ሳባ 52ኛዋ ንግሥት ናትና ነው፡፡

ቀጠሉና ፓስተር “የዘር የጾታ እና ማናቸውም ዓይነት ልዩነት መታረም ነው ያለበት። ለምሳሌ ባሪያ ለጌታህ ታዘዝ የሚለው ነገር መቀየር አለበት። ጥቁር የተረገመ ነው ለማለት ካምና ትውልዱ ተረግመዋል የሚል ጽንሰ ሃሳብ አለ። ስለዚህ የጥቁር ሕዝብ ችግር ሁሉ የእግዚአብሔር እርግማን ነው። ይህ መቀየር መወገድ አለበት እንዳለ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ጥቁሩን ሕዝብ ረግሞታል ብየ አላምንም። ይልቅስ ተርጓሚዎች የጥቁሮች አባት ካምን የተረገመ ብለው ሲጠቅሱ በስሕተት የተሞላ አድሎአዊነታቸው ነው። ካምን የረገመው እግዚአብሔር የክርስቲያን አምላክ ሊሆን እንደማይችል አምናለሁ።ይህ ስሕተት ሆን ተብሎም ይሁን በሌላ ምክንያት ይደረግ ፤ የመጽሐፍ ቅዱስን ቅዱስነት ውድቅ አያደርገውም።ነገር ግን ስሕተቶችን ማረምና እውነተኛ በሆነ አሉታዊ መንገድ ማቅረብ የበለጠ መጽሐፍ ቅዱስን ያበለጽገዋል!” ይለሉ አቶ በንቲ፡፡

አቶ በንቲ መስተካከል ያለበት የእርስዎና የቢጤዎችዎ እንጭጭ ጭንቅላት ነው እንጅ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም፡፡ ሲጀመር የሌለ ቃል እየጨመራቹህ መጽሐፍ ቅዱስን ተሳዳቢ ያደረጋቹህት እናንተ እራሳቹህ ናቹህ “በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?” ኤር.13፤23 ይል የነበረውን “…ኢትዮጵያዊ እንደከሰል የጠቆረ ፊቱን…!” እያላቹህ ምሥጢሩንና ትርጉሙን በማታውቁት ነገር እየበረዛቹህ ተሳዳቢ ያደረጋቹህት እናንተ ናቹህ፡፡ ሲመስላቹህ ኢትዮጵያዊና ነብር ብቻ ናቸው እንዴ ቆዳቸውን መቀየር የማይችሉት? ሌሎች የሰው ዘሮችና ሌሎች እንስሳት ግን መቀየር ይችላሉ ማለቱ ነው የሚመስላቹህ? እንጭጮች ስለሆናቹህ፣ ምሥጢሩን ስለማትረዱትና ስለማታውቁት እናንተን የመሰላቹህ እንዲህ ለማለት እንደፈለገ አድርጋቹህ ነው፡፡ እነ እንጭጮ ሆይ! ለመሆኑ “ባርነት የጥቁሮች ነው!” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የትኛው ነው? አንድ ጥቅስ እንኳ ሊያወጡልኝ ይችላሉ? ዮሴፍን ወንድሞቹ ለግብጽ ነጋዴዎች በባርነት የሸጡት ዮሴፍ ጥቁር ስለሆነ ነው ወይ? እስራኤላውያን ግብጽ ለ230 ዓመታት በባርነት የተገዙት ጥቁር ስለሆኑ ነው ወይ አቶ በንቲ?

አየ መናፍቃን ብቻ እንዲያው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ይይላቹህ እንጅ የእናንተ ጉድማ ተወርቶም የሚያልቅ አይደለም፡፡ በአዲስና ቀላል አገላለጽ ምንንትስ እያላቹህ በየጊዜው ያልፈለጋቹህትን ቅዱስ ቃል እያስወጣቹህ፣ የፈለጋቹህትን የረከሰ ቃል እንዳሻቹህ እየደነጎራቹህ መጽሐፍ ቅዱስን ልብ ወለድ ድርሰት አድርጋቹህት አረፋቹህ፡፡ አሁንማ ጭራሽ ግብረሰዶማዊነትን የሚያወግዙ ጥቅሶችን አስወጥታቹህ የሚደግፉ ጥቅሶችን ጨምራቹህ ለማተም እንዳሰባቹህ እስከመናገር ደርሳቹሀል፡፡ ቃሉስ ያለው ይሄንን አይደል፦

“መንፈስ ግን በግልጥ። በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው!” 1ኛ. ጢሞ. 4፤1-2

“ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ፥ ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ፤ እንዲህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና፥ በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ልብ ያታልላሉ!” ሮሜ. 16፤17-18

ይብቃን ወገኖቸ የእነኝህ አጋንንት ጉድ ተወርቶ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ከመቋጨቴ በፊት ግን መልእክትና ማሳሰቢያ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፦

ሀገሪቱ መንግሥት የላትም እንጅ መንግሥት ቢኖራት ኖሮ ቤተክርስቲያንም ሰው የላትም እንጅ ሰውና ሥራውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ኃላፊነት የሚሰማው ሰው እንዲሁም ሲኖዶስ፣ የሊቃውንት ጉባኤ ወዘተረፈ የሥራ አስፈጻሚ አካል ቢኖራት ኖሮ ይሄ ነውረኛ የሉተራውያን ድርጊት በተሰማ ቅጽበት ውግዘትና ተቃውሞ አሰምተው ስሕተቱ እንዲታረም ማድረግ የሚጠበቅባቸውን ጥረት ሲያደርጉ በተስተዋሉ ነበረ፡፡ ነገር ግን እንደምታውቁት በቤተመንግሥትም ሆነ በቤተክህነት ያሉት ሰዎች ለዚህ ለሉተራውያንና መሰል ድርጊቶች ድጋፍ የሚሰጡ እንጅ የሚቃወሙ ባለመሆናቸው ይሄ ሊሆን አልቻለም፡፡ እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ሲፈጸሙ በሚያስገርም ሁኔታ እንዳልሰሙና እንዳላዩ በዝምታ የሚመለከቱበት ምክንያትም ይሄው ነው ሌላ አይደለም፡፡

በመሆኑም ወገኖች ሆይ! የእኛም ዝምታ ከባባድ ዋጋ እያስከፈለን በመሆኑና ለእንደዚህ ዓይነቶች ማንነታችንን፣ ጥቅሞቻችንን፣ ቅርሶቻችንን፣ ሀገራችንን ወዘተረፈ. ለሚያሳጡን ጥቃቶች አስፈላጊውን ምላሽ ሰጥተን ጥቅሞቻችንን ማስከበርና ከጥቃት መከላከል እንችል ዘንጅ በቤተመንግሥትና በቤተክህነት ውስጥ ያሉ ቅጥረኛ ተኩሎችን በተቻለ ፍጥነት ማስወገዱ ብቸኛ መፍትሔ በመሆኑ እዚህ ላይ እንድንተጋ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!! ይሄንን እንደ ዜጋና እንደክርስቲያን ማድረግ የሚጠበቅብንን ተግባር ማድረግ ካልቻልን ግን ለሚደርሰው ጥፋት ሁሉ በነፍስም በሥጋም ተጠያቂዎች መሆናችንን ጠንቅቀን እንድናውቅ! ከንፈር መምጠጥና ባዶ ቁጭት ከምንም አያድንም!!! ቆፍጠን በልና ቆርጠህ ተነሥ!!!

ድል ለቤተክርስቲያን!!! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.