የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እና ቄሮ መልዕክቶች አልተጣጣሙም፣ ተማሪዎች ለችግር ተዳርገዋል (ጌታቸው ሽፈራው)

~ ህዳር 19 ሌሊት፣ ህዝብ እየሞተ ማንም መማር እንደሌለበት፣ በዚህ ሁኔታ እማራለሁ የሚል ካለ እርምጃ እንደሚወሰድበት የሚገልፁ ወረቀቶች በየዶርሙ በቄሮ ስም ተበትነዋል።

~ህዳር 20 ጠዋት የኦሮሞ ተማሪዎች በየዶርሙ እየዞሩ ሌሎች ተማሪዎች ግቢው ለቀው እንዲወጡ አድርገዋል። እንዲወጡ ከመጠየቅና ከማስጠንቀቂያ ያለፈ የተፈጠረ ችግር ስለመኖሩ አልተገለፀም።

~ ተማሪዎች ከግቢ ውጡ በተባሉበት ወቅት ዩኒቨርሲቲው ለቀው እንዳይወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ተማሪዎች ወደ ሐረር እንዳይሄዱ መሰናክል ፈጥሯል። ተማሪዎቹን የተባበሩ ሾፌሮች ለቅጣት ተዳርገዋል። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች በተለይም ወንዶች በእግራቸው ወደ ሐረር ለመሄድ ተገደዋል።

~ የአካባቢው ማህበረሰብ ተማሪዎችን አስጠልሎ ሰንብቷል። የኦሮሞ ተማሪዎች በአካባቢው የተጠለሉ ተማሪዎች ወደ ግቢ ይመለሳሉ በሚል በየሰፈሩ እየዞሩ ወደቤተሰባቸው እንዲሄዱ ጠይቀዋል። ከተጠለሉበት በኃይል እናስወጣለን በማለታቸው የአካባቢው ህዝብም ያስጠለላቸውን ተማሪዎች አይዋጡም በማለቱ አለመግባባቶችም ተፈጥረው ነበር ተብሏል።

~ ህዳር 21 አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ተማሪዎችን ሰብስበው አነጋግረዋል ቢባልም የተለወጠ ነገር የለም።

~ ህዳር 23 የኦሮሞ ተማሪዎች 6 ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ማንም ትምህርት እንደማይጀመር በቄሮ ስም በተበተኑ ወረቀቶች አስታውቀዋል።

ቅድመ ሁኔታዎችም:_

#ከቤትንብረታቸው የተፈናቀሉ ኦሮሞዎች በአጭር ጊዜ መፍትሄ እንዲያገኙ፣ በወሰን አካባቢ ያለው ግጭት እንዲቆም

#ሰራዊቱ ከዩኒቨርሲቲና ከአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ወጥቶ ወደካምፕ እንዲመለስ

#ልዩኃይል በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው ሽብር እንዲያቆምና ፌደራሊዝሙ እንዲከበር

#የፖለቲካእስረኞች እንዲፈቱ

#የፖለቲካተቋማት (ከዩኒቨርሲቲ) ግቢዎችን ለቀው እንዲወጡ

#የትምህርትጥራትን ሰበብ በማድረግ የሚደረገው ፕሮፖጋንዳ ይቁም፣ የትምህርት ጥራት የሚመጣው በአዲስ እስትራቴጅ እንጅ በ Exit Exam አይደለም የሚሉ ናቸው።

~ በዚህም መሰረት ማንኛውም ተማሪ እስከ ህዳር 24 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ግቢውን ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ጠይቀዋል። አብዛኛው ተማሩ ወደ ቤተሰቡ ስለተመለሰ ከተማ ውስጥም ሆነ ግቢ አካባቢ የተገኘ ተማሪ እርምጅ እንደሚወሰድበት ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

~ ወደ ግቢ መመለስ የሚቻለው የሶስቱ ካምፓስ ተማሪዎች ተወያይተው ጥሪ ከተላላፈ በኋላ ነው ተብሏል፣ ትናንት በተበበነ ወረቀት።

~ በተቃራኒው፣ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹ ከግቢ መውጣት እንደሌለባቸው፣ ከግቢ የወጡ ተማሪዎች ከህዳር 21 እስከ ህዳር 26 ወደ ግቢ ተመልሰው ከህዳር 27 ጀምሮ በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ ማስታወቂያ አውጥቷል።

~ተማሪዎች ወደ ግቢ ሲመለሱም ከአሁን በኋላ ምንም ይፈጠር ምን ግቢ ጥለው እንደማይወጡ ፎርም እንዲሞሉ ይደረጋል እየተባለ ነው።

~ የትራንስፖርት ገንዘብ የሌላቸው፣ ቤተሰቦቻቸው ሩቅ የሆኑ ተማሪዎች በየ ቤተ እምነቶች ተጠልለው ይገኛሉ። የኦሮሞ ተማሪዎች ከህዳር 24 ጀምሮ በአካባቢው የተገኘ ተማሪ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል። በመሆኑም ወደ ቤተሰቦቻቸው ያልተመለሱና በችግር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች እጣ ፈንታ አሳሳቢ ሆኗል።

ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተላለፈ ነው! ዩኒቨርሲቲ ግቢም ሆነ ከተማ ውስጥ የተገኘ ተማሪ እርምጃ ይወስድበታል ተብሏል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.