የወልዲያ ወጣቶች ቤት ለቤት እየታሰሱ እየታደኑ እየታሰሩ ነው

የወልዲያ ወጣቶች ቤት ለቤት እየታሰሱ እየታደኑ እየታሰሩ ነው፡፡ ከተማዋ በመከላከያ ተወራለች፡፡ እንቅስቃው “ፀጥ ረጭ” ብሏል፡፡ በወልዲያ አካባቢ ያላችሁ ወጣቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስንል እናሳስባለን፡፡ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን፡፡

ከወልድያ አንድ ሬሳ ወደ መቀሌ በመግባቱ ምክንያት ከተማዋ ተናውጣለች ሱቆች ተዘግተዋል ብዛት ያላቸው ወጣቶች መቀሌ ሮማናት አደባባይ ከተማ ለይ ወጥተዋል ፊደራሎች አጥለቅልቀውታል ጥይት እና መትረየስ እየተተኮሰ ነው የሚያስፈራ ድባብ ነው ያለው ከተማው ላይ እስካሁን ሰአት ድረስ ብጥብጡ እንደቀጠለ ነው።

ወጣቶች አድማ በመውጣታቸው ምክንያት ፌደራሎች እና ሚልሻዎች እየተኮሱ ነው የሞቱ ሰዎችም አሉ እየተባለ ነው። ከየት እንደሆነ የማይታወቅ ቦታም ከባድ መሳርያዎች እየተተኮሱ ነው።ህዝቡ በንዴት በመውጣት ወያኔ ሌባ አስገደልከን ውረድልን በማለት የመንግስት መስርያ ቤቶች በዲንጋይ እየደበደበ ነው እየተከታተልን እንዘግባለን::

 

Is it a true story Tolisha?
አሁን የደረሰን መረጃ
መቀሌ ሮማናት አደባባይ ብጥብጥ ተነስቷል!!!
ከወልድያ አንድ ሬሳ ወደ መቀሌ በመግባቱ ምክንያት ከተማዋ ተናውጣለች ሱቆች ተዘግተዋል ብዛት ያላቸው ወጣቶች መቀሌ ሮማናት አደባባይ ከተማ ለይ ወጥተዋል ፊደራሎች አጥለቅልቀውታል ጥይት እና መትረየስ እየተተኮሰ ነው የሚያስፈራ ድባብ ነው ያለው ከተማው ላይ እስካሁን ሰአት ድረስ ብጥብጡ እንደቀጠለ ነው።
ወጣቶች አድማ በመውጣታቸው ምክንያት ፌደራሎች እና ሚልሻዎች እየተኮሱ ነው የሞቱ ሰዎችም አሉ እየተባለ ነው። ከየት እንደሆነ የማይታወቅ ቦታም ከባድ መሳርያዎች እየተተኮሱ ነው።

ህዝቡ በንዴት በመውጣት ወያኔ ሌባ አስገደልከን ውረድልን በማለት የመንግስት መስርያ ቤቶች በዲንጋይ እየደበደበ ነው

 

ወሎ !!
በራያ አራት የሰላም ባሶች ከትናት ማታ ጀምሮ በህዝብ እንደታገቱ ነው::
አንድ የአጋዚ ወታደሮችን ጭኖ የነበረ ኮድ 4 የመንግስት መኪና ላይ የወልዲያ ህዝብ እርምጃ ወስዶበታል::
ወሎ ውጥረት ላይ ነች ለወያነ አንገዛም በማለት ህዝባዊ እንቢተኛነቱ እንደቀጠለ ነው::

Image may contain: one or more people and outdoor

 

Image may contain: 1 person, closeup

ትላንት እየሳቀ እየተጫወተ ከቤተሰቦቹ ጋር በሰላም ምሳውን ተመግቦ የሚወደው ወልድያ ከነማ ክለብን ለመደገፍ አገር አማን ብሎ ወደ ስታድየም ያመራው መምህር ታምሩ በሪሁን በጉጉት ወደሚጠብቁት ቤተሰቦቹ ግን ሊመለስ አልቻለም የትግራይ ወያኔ ወታደሮች ጥይት በግፍ ህይወቱን ቀምተውታል።

የሰማዕቱ መምህር የቀብር ስነስርዓት ዛሬ በወልድያ መድሃኒአለም ይፈፀማል ተብሏል።

እያንዳንዷን የደም ጠብታ ታወራርዷታላቹ !
ነፍስህን በገነት ያኑራት ወንድማችን ፐቤተሰቦችህም መፅናናቱን ይስጥልን!

 

 

 

 

ወልዲያ ወልዲያ ኦ ወልዲያ! ያሳዝናል! ያሳፍራል!!

* ጎንደርና ባህርዳር ላይ ተቀባብሎ ወልዲያ ላይ ስለባረቀው ጥይት ጥቂት እናውራ*

ወልዲያ ላይ የሆነው፣ የተፈፀመው “ተራ የእግር-ኳስ ክስተት”፣ “ሊያጋጥም የሚችል ተራ የደጋፊዎች ግጭት” ተብሎ ሊታለፍ የሚችል አይደለም። ሁኔታው ኳስን ሰበብ ያደረገ፣ የኳስ ግጥሚያውን እንደ መሳርያ ሊጠቀም ተዘጋጅቶ የጠበቀ፣ ከኳስ በላይ የሆነ አሳፋሪ፣ አስነዋሪ ፍፃሜ ነው። 
እንደ እውነቱ ከሆነ ነገርየው ወልዲያ ላይ ባረቀ እንጂ የተጠመደው ሌላ ቦታ ላይ ስለመሆኑ ብዙ አመላካች ነገሮች አሉ። እስቲ ይህንን እንይ፤

-ገና በጧቱ በብዛት ከሌላ የክልሉ አካባቢዎች (በብዛት ከጎንደርና ባህርዳር) ተሰባስበው የመጡ ወጣቶች የመቐለ ከተማ የእግር-ኳስ ቡድን ካረፈበት ሆቴል (ላል ሆቴል) አመሩ። በቦታው የመቐለ ደጋፊዎች ተጨዋቾቻቸውን እያዩና ቁርስ እየበሉ ነበር። በነሱ ላይ የድንጋይ ናዳ ማዝነብ ጀመሩ። አካባቢው ላይ ከፍተኛ ግርግር ተነሳ። ፖሊስ ከአካባቢው ደርሶ ሁኔታውን ለማረጋጋት እየሞከረ ነበር፤

– በደቂቃዎች ውስጥ ላል አካባቢ የተጀመረው የተቀነባበረ ብጥብጥ በነዚሁ ወጣቶች ሌላኛው የብጥብጥ ክንፍ እየተመራ ወደሁሉም የወልዲያ አካባቢዎች ተዛመተ- ፒያሳ ፣ አዳጎ ፣ አዲስ መንደር ፣ ጎንደር በር ወ.ዘ.ተ በወልዲያ ከጫፍ እስከ ጫፍ የተጋሩ ንብረቶች፣ መኖርያ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች እየተለዩ የጥቃት ሰለባ ሆኑ፤ ንብረቶች ወደሙ፣ ተዘረፉ፤ በበርካቶች አካል ላይ ጉዳት ደረሰ።

– እስካሁን ባለው ሁኔታ የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል፤ በርካቶች የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው የመቐለ ከተማ ደጋፊዎች ደግሞ ወልዲያ ሆስፒታል ላይ ሕክምና እየተደረገላቸው ነው።

– መንገድ ላይ የነበሩ የመቐለ ከተማ ደጋፊዎች እንዲመለሱ ሆነዋል ፤ ወልዲያ የደረሱና የነዚሁ ወሮበሎች የጥቃት ሰለባ የሆኑ ደጋፊዎች በፖሊስ እየታጀቡ ወደ አላማጣና መቐለ እንዲሄዱ ሆኗል ፤

– ትላንት አመሻሻሹ ከ3- 4 ሰዐት መቐለ ሮማናት አደባባይ ላይ በቁጣ የነደዱ የመቐለ ከተማ ደጋፊዎች ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፤ ሰልፉ በፖሊስ በሀይል ተበትኗል። ሰልፉ ዛሬ በስፋት የማድረግ ሐሳብም አለ፤

ሲጠቃለል፤ ባህርዳርና ጎንደር ላይ ተቀባብሎ ወልዲያ ላይ የባረቀው የጥቂት ነውረኞች የተቀነባበረ አስነዋሪ ጥቃት የኢትዮጵያ ሕዝብ በመላ በተለያዩ መንገዶች (ሰላማዊ ሰልፍን ጨምሮ) በአንድ ድምፅ ሊያወግዘው ይገባል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.