መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ የ”ኢትዮጵያ” አየር ኃይል ባህርዳር ከተማ ላይ ተይዞ ግንቦት 7ን ልትቀላቀል በማለት 10 አመት ፈረዱበት (ጌታቸው ሽፈራው)

መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ የ”ኢትዮጵያ” አየር ኃይል ውስጥ የበረራ አስተማሪና የሄሊኮፍተር አብራሪ ነበር። ከትውልድ ቦታው ብዙው የማይርቀው ባህርዳር ላይ ያዙትና “ግንቦት 7ን ልትቀላቀል እየሄድክ ነው” ብለው አሰሩት። 10 አመት ፈረዱበት።

ከእስረኛው ነጥለው ጨለማ ቤት አሰሩት። ሌላ ዞን ካለ እስረኛ ጋር በማይገናኝበት ሁኔታ ታስሮ ቂሊንጦ ተቃጠለ። የተቃጠለው ዞን2 እና ዞን 3 ነው። መቶ አለቃው ታስሮ የነበረው ከሁለቱ ዞኖች ውጭ ያለ ጨለማ ቤት!

መቶ አለቃ ማስረሻ ባልነበረበት ጉዳይ ሸዋሮቢት ተወስዶ ተሰቃይቷል። ጣራ ላይ ተሰቅሏል። የተሰቀለበትን ገመድ ድንገት በጥሰው መሬት ላይ ጥለውት ለብዙ ጊዜ ወገቡን ታሞ ነበር። ስድቡ፣ ዘለፋና ድብደባው የከፋ ነበር።

በመጨረሻም ባልነበረበት ቦታና ጉዳይ ዋናው አንተ ነህ ተብሎ 1ኛ ተከሳሽ ሆኗል። እስከ ሞት በሚያስቀጣ የሀሰት ክስ!

መቶ አለቃ ማስረሻ ጨለማ ቤት ታስሮ በተፈጠረ ክስተት ተዋናይ ነበር ተብሎ ሲከሰስ የሚጠቀስበት “ማስረጃ” የሚያሳዝን ነው። አንድ ክስ ላይ “ነሃሴ 27/2008 ማታ ማስረሻ ሰጤ ዞን 2 ዱርዬዎቹን ሰብስቦ……” ይላል። ያኔ መቶ አለቃ ማስረሻ ዞን 2 አልነበረም!

ግን ሀሰት የማጥቂያ መሳርያ ሆናለችና፣ በሀሰት ያስራሉ! በሀሰት ይከሳሉ! የሀሰት ማስረጃ ያቀርባሉ! በሀሰት ይፈርዳሉ!

@ጌታቸው ሽፈራው

ተዋቸው ቸኮል ይባላል። በ”ሽብር” ተከሶ ቂሊንጦ ይገኛል። ፌደራል ፖሊስ ሲያስር የእስረኛውን ጓዝ ጭኖ ነው ወደ ማዕከላዊ የሚወስደው። ደብድበው “አልተበላሸሁም” የሚያሰኙት ይመስል የተበላሸ ኮምፒውተርና ስልክ እንኳ አይተውም።

ገንዘብ ከተገኘማ ወደኋላ ማለት የለም። የኤርሚያስ ፀጋዬ ቤት 8500 ብር በገዛ ፈቃዳቸው ወስደዋል። ከዛው ቤት ውስጥ ከነበረው ፍሬው ተክሌ ኪስ 2000 ብር ወስደዋል። መጠየቅም አይቻልም።

በፖሊስ የተያዘ ዕቃ ወይንም ገንዘብ ይመዘገባል። በኢግዚቢት ካልተያዘ ለታሳሪው ይሰጣል። በፌደራል ፖሊስ አካባቢ ከዚህ ውጭ የሆኑ አሰራሮች አሉ። በተለይ ከተፈታ የተያዘበትን ስልክም እንዳይጠይቅ ይደረጋል። ቢጠይቅም በቀጠሮ ተማርሮ ይተወዋል። አዲስ አበባ ፖሊስ የስንቶቹ ስልክ ቀርቷል!

ተዋቸው የተባለ ተከሳሽ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል እንዳመለከተው፣ በኤግዚቢትነት ያልተያዘ 30 ሺህ የኢትዮጵያ እንዲሁም 20 ሺህ የሱዳን ብር ተይዞበታል። ህገወጥ ነው አልተባለም። በኤግዚቢትነትም አልተያዘበትም።

ተከሳሹ እንደሚለው ተከሶ ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ሲሄድ ከተያዘበት ብር ላይ 1200 ብር አንስተው ሰጥተውታል። “የወጭ” ያሉት ይመስላል። ሌላው በማረሚያ ቤት ይደርስሃል ተብሎ ነበር። አልደረሰም። ምን አልባት፣ “ወደ ቂሊንጦ ብሩን ለማድረስ ጥረት ስናደርግ ግንቦት ሰባት ጎተራ አካባቢ ጠብቆ ሽብር ፈጥሮ ዘረፈን” ብለው ሌላ ሰው ይከሱና፣ “ድርጅትህ ነው የወሰደው” ሊሉት ይችላሉ።

ተዋቸው ከአሁን ቀደም ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ የነበር ቢሆንም መፍትሄ እንዳላገኘ ገልፆአል።

በነገራችን ላይ፣ ኢትዮጵያ ከደቡብ አሜሪካ የሚመጣ አደንዛዥ ዕፅ እንዲሁም ምዕራብና መካከለኛው አፍሪካን ምንጩን ያደረገ የዝሆን ጥርስና አልማዝ ወደ ኤሲያ የሚዘዋወረው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ነው። እነዚህን ወንጀሎች የሚመረምረው ደግሞ ማዕከላዊ ነው። እቃዎቹ የሚቀመጡት ማዕከላዊ ነው። ከዛስ ወደየት ይሄዳሉ የሚለውን የሚያውቁት የማዕከላዊ ሰዎች ናቸው።

 

ቂሊንጦ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት የቂሊንጦ እስር ቤት ኃላፊዎች ወከባ እየፈፀሙባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አመልክተው የነበር ቢሆንም የሚፈፀምባቸው በደል ተባብሶ ቀጥሏል ተብሏል።

አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት( ፎቶው ላይ በግራ በኩል የሚታዩት) ከዞን 3 አዲስ ወደተሰራው ዞን 5 ተቀይረው ጠያቂ ተከልክለዋል ተብሏል።

ሁለቱ መነኮሳት ዞን 3 ታስረው የነበር ሲሆን አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም (ከፎቶው በቀኝ በኩል የሚታዩት) ቀደም ብሎ ወደ ዞን 2 ተቀይረዋል።

See More

Image may contain: 3 people, people standing

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.