መቀሌ -ወልዲያ ከተሞች (ሙሉቀን ተስፋው)

1. በመቀሌ ከተማ የነበረው አመጽ ዐማራ ፍለጋን ነበር፤ ሌሊት በባውዛ ቀንም በብርሃን ዐማራ ፈለጉ፡፡ የዐማራ የሆነ ነገር ጠፋ፡፡ በአባት ወይም በእናታቸው ዐማራ የሆኑ ዜጎች ሁሉ ራሳቸውን ለማዳን ተደብቀዋል፡፡

በመቀሌ ጎዳናዎች አማ የሚል ታርጋ ያላቸው መኪናዎች ተፈልገው ታጡ፤ ከዚያ አአ የሚል ታርጋ ያላቸው የእነርሱው ቱጃሮች የሚይዟቸውን መኪናዎች ጠረማመሷቸው፡፡ አንዳንድ የግል ባንኮች ዐማራዊ ወይም ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሀብት ናቸው በሚል ተደበደቡ፤ የሚገርመው ግን ከዚህ ድብደባ የሥርዓቱ ደጋፊ ባንኮች (ለምሳሌ ዳሸን) ጪምር ተጠቂ መሆኑ ነው፡፡

የመቀሌ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ውጭ መውጣት አይችሉም፡፡ ግቢ ተዘግተው ነው ያሉት፡፡
**********
2. በወልዲያ የነበረውን ፍትሐዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተላላኪው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ‹‹ዝርፊያ›› ማለቱን ተከትሎ አንዳንድ የሕወሓት ሰዎች አራግበውታል፡፡ የወልዲያ ወጣቶች በትክክል ለሌለውም የዐማራ አካባቢ ትምህርት የሚሆን ነገር ፈጽመዋል፡፡ መጀመሪያ ታገሱ ከዚያም ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚገባቸውን ቅጣት መስጠት ነበረባቸው፡፡

ወጣቶች የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑ ሰዎችንና ድርጅቶችን ማጥቃት ቢቻል ግን (በተለይ በሥራ ቀን ቢሆን ይጠቅማል) ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንጅ ወንጀል አይሆንም፡፡ ይህ በደሴም፣ በኮምቦልቻም፣ በጎንደርም ቢሆን የሚበረታታ ተግባር ነው፡፡ ከፊት ለፊት የሚገድሉን ሰዎች (በዘረፋና በሙስና የተገኘ) ፀጋ ተከምሮ ሌላው የሚራብበት ሥርዓት ማብቃት የሚችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡
**********
3. ዛሬ የወልዲያ ከተማ ትግርኛ ብቻ በሚናገሩ ወታደሮች ተጥለቅልቃለች፡፡ እነዚሁ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች በግል የተጣሏቸውን ሰዎች ሁሉ እያስለቀሙ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ነገር የበለጠ ነገሮችን ከማወሳሰብ የዘለለ ጥቅም እንደሌለው አቶ ንጉሡ ለአለቆቻቸው ቢነግሯቸው መልካም ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.