የሙሉቀን ተስፋው የአገር ውስጥ ዜናዎች – በመቀሌ ዩንቨርሲቲ, የጪልጋው አደጋ

የመቀሌ ጉዳይ!

ሙሉቀን ተስፋው

ተማሪዎች ካፌ ሲሔዱ ይደበደባሉ፤ ትናንት አዲሃቂ ግቢ ዛሬ ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ግቢ ውስጥ ምግብ ለመመገብ ሲሔዱ ተማሪዎች ተደብድበዋል፡፡ ከሁሉቱም ግቢዎች ያነጋገርኳቸው ተማሪዎች ምግብ ወደ ዶርም በመውሰድ ብቻ እየተመገብን ነው ብለውኛል፡፡ ከግቢ ውጭ መውጣት አይቻልም፡፡
በከተማ አማርኛ የሚናገር ሰው ጉዳት እየደረሰበት ነው፤ አንድ ሰው አማርኛ የተናገረ ሰው በደረሰበት ጉዳት እጁ ተቆርጧል፤ ሆኖም በስህተት ጉዳት የደረሰበት ትግሬ እንደሆነ ነው የነገሩኝ፡፡ አንድ አስከሬን ዩንቨርሲቲው ግቢ በር አካባቢ የተገኘ ሲሆን ጥበቃዎችም አናውቅም ብለዋል፡፡

 

የጪልጋው አደጋ፤

ሙሉቀን ተስፋው

ዛሬ ጠዋት በጭልጋ ወረዳ ኳቢየር ሎምዬ ቀበሌ ላይ ከሱዳን ነዳጅ ጪኖ በዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ታጅቦ ሲመጣ በዐማራ ጎበዝ አለቆች እንዲወድም ተደርጓል፤ የብአዴኑ አፈ ቀላጤ እንዳለው ከዘረፋ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ የጥቃቱ ዋነኛ ዓላማ የዐማራ ሕዝብ ትግል መቆም የማይችል መሆኑን ማሳየት ነው፡፡
ጎበዞቹ ያጀቡት የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት መሆናቸውን ያወቁት በመጨረሻ ላይ በመሆኑ ማዳን አልቻሉም፤ በዚህ የሦስት ፖሊሶች ሕይወት ጠፍቶባቸዋል፡፡

 

ቀለብ ስዩም

ቀለብ ስዩም በግፍ የተፈረደባትን እስር አመክሮ ከተቀነሰላት ጨርሳለች። ሆኖም ግን አገዛዙ ለዐማራ ተወላጆች አመክሮ ይቀንሳል ወይ?

 

 

 

 

 

 

አማራ ነን !

Temesgen Tesema

የግዮን ባለጸጎች፤ የቤተ አማራ ባለ እርስቶች፣
ከአገር በፊት አገር የሆን የኢትዮጵያ መስራች ህዝቦች ።
አማራ ነን ነባር ህዝቦች፤ ባለ ታሪክ ባለ ገድል ፣
ጊዜ አቅንቶን የማንበድል ፤ ዘመን ገፍቶን የማንጎድል ።

የዳ’ኣማት ባለ አሻራ -የአክሡም ዙፋን አልጋ ወራሽ ፣
ቅድመ አለም መንግስት ወጣኝ ፤ ቅድመ አለም ጥበብ ጠንሳሽ ።
አማራ ነን ስልጡን ህዝቦች ፤ የሐ፣ ሮሐን የተጠበብን ፣
ሀውልት ያቆምን፤ መቅደስ ያነጽን ድንጋይ ፈልጠን አለት ጠርበን ።

የግዮን ባለጸጎች፤ የቤተ አማራ ባለ እርስቶች፣
ከአገር በፊት አገር የሆን የኢትዮጵያ መስራች ህዝቦች ።
አማራ ነን ነባር ህዝቦች፤ ባለ ታሪክ ባለ ገድል ፣
ጊዜ አቅንቶን የማንበድል ፤ ዘመን ገፍቶን የማንጎድል።

አማራ ነን ነጻ ህዝቦች ታሪክ በአምዱ የዘከረን ፣
ቅኝ ገዥ ያልደፈረን ፣ ባዕድ ጠላት ያልበገረን ።
አማራ ነን ትምክህተኞች ታሪክ ጠቃሽ ገድል ነቃሽ ፣
ያገር አጥር ፣ያገር አውጋር፣ ነፍጥ አንጋቢ ፣መራዥ ተኳሽ ።

የግዮን ባለጸጎች፤ የቤተ አማራ ባለ እርስቶች፣
ከአገር በፊት አገር የሆን የኢትዮጵያ መስራች ህዝቦች ።
አማራ ነን ነባር ህዝቦች፤ ባለ ታሪክ ባለ ገድል ፣
ጊዜ አቅንቶን የማንበድል ፤ ዘመን ገፍቶን የማንጎድል።

በተፈጥሮ ኩል የደመቅን የውብ ህዝቦች ቤተ ተውኔት ፣
አማራ ነን ለጋስ ህዝቦች በፍቅር የኖርን በቼርነት ።
በዕምነት በግብር የታነጽን፤ ፋትሃዊ ፍርድ አዋቂ ፣
በአበው ቁና ግፍ ሰፋሪ በአበው ስሪት ደም አድራቂ ።
እንደ ንብ አብረን የታተርን ፤ እንደ አንበሳ የተከበርን፣
አማራ ነን ስልጡን ህዝቦች ተዋህደን ገዝፈን የኖርን ።
ከአገር ዘርፈን የማንከብር ቅርስ አውድመን የማንለማ ፣
አማራ ነን ኩሩ ህዝቦች ባለ ራዕይ ባለ አላማ ።
የግዮን ባለጸጎች፤ የቤተ አማራ ባለ እርስቶች፣
ከአገር በፊት አገር የሆን የኢትዮጵያ መስራች ህዝቦች ።
አማራ ነን ነባር ህዝቦች፤ ባለ ታሪክ ባለ ገድል ፣
ጊዜ አቅንቶን የማንበድል ፤ ዘመን ገፍቶን የማንጎድል።
ነፍጠኛ ባቆማት አጸድ ፤ ነፍጥ ባጸናት አድባር ፣
አበው በደም በዋጇት አርበኞች ባቆዯት አገር ።
ነፍጠኝነት ወንጀል ሆኖ ባበው ስሪት የተቀጣን ፣
ቀብረው የጫኑብንን አለት ሰንጥቀን የወጣን ።
የግዮን ባለጸጎች፤ የቤተ አማራ ባለ እርስቶች፣
ከአገር በፊት አገር የሆን የኢትዮጵያ መስራች ህዝቦች ።
አማራነት ያቆራኘን ፤ ነፋጠኝነት ያዋሃደን ፣
አማራ ነን አዲስ ትውልድ ግፍ አምጦ የወለደን ፣
ዘርን ከዕልቂት ለመታደግ ፤ ግፍን በግፍ ለመመከት ፣
የዘር ሞትን ዳግም ላንሞት ፤ ተሹመናል በአማራነት ።
አማራነትት ተላብሰን አማራነትን ተኩለን ፣
ነጻ ህዝቦች እንደነበርን ፤ ነጻ ህዝቦች እንሆናለን።

 

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.